www.maledatimes.com ወጣቱ የኢትዮጵያ ድምጻዊ በ64ኛው ኢሚ አዋርድ ላይ ተሳታፊ ነበር - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ወጣቱ የኢትዮጵያ ድምጻዊ በ64ኛው ኢሚ አዋርድ ላይ ተሳታፊ ነበር

By   /   September 25, 2012  /   3 Comments

    Print       Email
0 0
Read Time:7 Minute, 11 Second

በ64ኛው የኢሚ አዋርድን ተከትሎ ብዙ ታላላቅ አለም አቀፍ የፊልም ባለሙያዎች ፣ሙዚቀኞች ፣ሲኒማቶግራፈርስ እና የፊልም ኢንዱስትሪ ካምፓኒዎች እን ባለቤቶቻቸው የተሳተፉበት ትልቁን የዚህን አመት አዋርድ ወጣቱ ኢትዮጵያዊ በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛን አድናቆት እና እውቅና ያለውን በዘመናዊው ያዘፋፈን ስልቱ እና ከብዙ አርቲስቶች ጋር በፊቸሪንግ በመስራት የሚታቀው ሳሚ ካሳ (ሳምቮድ )የዚሁ እድል ተቋዳሽ እንደነበር ከስፍራው የደረሱን የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ ሳምቮድ በተለያዩ የሃሊውድ ቲቪ ሾው ፣ፊልሞች እና ማስታወቂያዎች ላይ የተሳተፈ ሲሆን በሃሊውድ የአክተሮች ዩኒየን አባል በመሆን (እስክሪን አክተርስ ጊልድ ) አባል በመሆን ስራዎቹን በመስራት እራሱን በማንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ሳምቮድ ከሰራቸው የቲቪ ሾው ድርጅቶች  ታዋቂው ስክረብስ ፣ አንታራዥ   ላይ በመሳተፍ ለመጀመሪያ ጊዜያት በመስራት ወደ ማህበሩ መቀላቀሉን ከዛሬ 3 አመት በፊት ለጠብታ መጽሄት  ዝግጅት ክፍል ላደረግነው ቃለመጠይቅ እንደገለጸ ይታወቃል ። በወቅቱም በጣም ከባድ እና ፈታኝ ሆኖ ለራሳቸው ዜጎችም ቢሆን አስቸጋሪ የሆነው ይኸው መንገድ ለእኔ እነዚህ ስራዎቼ ብዙዎቹን መንገዶች ሊጠረጉልኝ ችለዋል ሲል ጠቁሞን ነበር።  በአሁን ሰአት የተለያዩ የሃሊውድ ፕሮዳክሽኖች ሶፕአፕራ  ቦልድ አንድ ቢዩቲፉል  የተሰኘ ቲቪ ሾው ላይ እና በተለያዩ የፊልም ስራዎች ላይ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ። በተወሰነ መልኩ ከመድረክ በስተጀርባ በመሆን እንቅስቃሴዎቹን አሳይቷል ።በተያያዥነትም ሙዚቃዎቹንም ለማሻሻል እና በአለም አቀፍ ደረጃ ለማሳየት ጥረት እያደረገም እንደሆነ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሚሰራቸው የክሊፕ ስራዎች የጥራት ደረጃቸው  ለማየትም ችለናል ።ለዚህም ከዚህ በፊት ወደ ሰሜን አሜሪካ ይዞት ከመጣው አልበሙ “ተይ ተይ “ ዘፈኑ ተመርጦ በቢኢቲ ቻናል ከሆነው አንዱ በካሪቢያን ሙዚቃ ፕሮግራም ቴሌቪዥን ስርጭት (ዊክድ) በመጀመሪያ ደረጃ (ቶፕቴን ሊስት) ለስምንት ሳምንታት በማቅረብ  ከፍተኛ ተደማጭነትን እንዲያገኝ አድርጎለታል። ለዚህም ይህ የሙዚቃ ስራው በቢኢቲ የሙዚቃ አዋርድ ፕሮግራም ላይ እንዲጋበዝ አድርጎታል ።ባለፈው አመት በተሰራው በአሜሪካን አየር ፎርስ የፊልም ስራ ላይ የተሳተፈ ሲሆን የኢትዮጵያን ባህል እና እንቅሳቃሴም ትወናን እንደተወነ ገልጾልን ነበር ይህም የፊልም ቀረጻው ለአንድ ወር በሜክሲኮ ሲቲ እንደተከናወነም አክሎ ገልጦአል  ።በተለይም የሃሊውድ ጋድ ፋዘር ከተሰኘው ድንቅ አክተር አልፓችኖ ጋር በመሆን አጭር የፊልም ስክሪን እይታም አግኝቶ የሰራ ሲሆን ይህ ፊልም በሚቀጥለው አመት የሚለቀቅ ነው የፊልሙም ርእስ ስታንድ አፕ ጋይስ የተሰኘ ሲሆን ሌላው ትሩ ብለድ( እውነትኛ ደም )በሚሰኘው የኤችቢኦ  ቲቪ ሾው ስራዎችን ፕሮድዩስ በሚደረግበት ላይ የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል። በተለይ ሳምቮድ ከተለያዩ የፊልም ኤጀንቶች ፣ማነጀሮች ፣ፐብሊሲቶች እና ካምፓኒዎች  ጥልቅ ግኑኝነት ያለው ይህ ወጣት የወደፊት የኢትዮጵያ የፊልም ራእይ  ሊሆን ይችላል ተብሎ ይታሰባል ።በዚህ ወራትም ከሚለቀቁት አዳዲስ ቴክኖሎጂ ካፈራቸው መካከል ከጌም ካምፓኒ ጋር በመስራት በራሱ ስም አዲስ የጌም ጨዋታ በሚቀጥለው ወር ለገበያ እንደሚቀርብ የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል።በተለይም ለማለዳ ታይምስ በየወቅቱ የሚያደርሱትን የዚህን ወጣት ባለ ራእይ ስራዎችን አስመልክቶ በቅርበት አብረውን የሚሰሩን ባልደረቦቻችንን ሳናመሰግን አናልፍም ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

3 thoughts on “ወጣቱ የኢትዮጵያ ድምጻዊ በ64ኛው ኢሚ አዋርድ ላይ ተሳታፊ ነበር

  1. I’m happy on his accomplishment which will make all of us proud. It’s not achieved definitelywithout a hard work. which encourages to work hard young Ethiopians that’ll look up to him both in N. American and Ethiopia. I have never seen his work before but I looked him up after reading on your blog. I just hope Mr. Sam in the future will have black women portraite in a decent dance I found it detestable and unlike Ethiopian tradition to see women half naked and dancing in a very degrading manner. That’s my opinion I’m not to blamish or criticisehim in bad way but to give a constructive criticism. I hope, Mr. Sam understands the logic behind my thought and for the survival of our good culture. it’s one thing to entertain, but it’s another to be honerable musician who care about the impressionable kidds. Always it’s to all of us benefit the message we put out side carry a responsible message. If we say I’m just an entertainer and leave the responsibility on the parents uh..
    When I see why black music has to have something that portray women in undignified manner. Specially in rap music.

    I hope he won’t take it wrong way I just hope he want his sisters to be respected not others to think that’s the image of black women.

    Good Luck on your future!
    I wish you the best of luck!

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar