ቀን፡ 24/04/07 ዓ.ም.
Date: 01/02/15 በስደት ላይ ያለው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ THE LEGITIMATE HOLY SYNOD OF THE ቁጥር: ጠቤክ/0104/2007
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH Ref. No: 0104/2015 መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት PATRIARCHATE HEAD OFFICE IN EXILE
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”ዮሐ3:16
ለሚመለከተው ሁሉ፤
ጉዳዩ፦ ከቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅናና መመሪያ ውጪ በቅርቡ “የቅዱስ ሲኖዶስ መተዳደሪያ ሕግ” በሚል ለየአብያተ ክርስቲያናት በሕገ ወጥነት የተበተነውን የተሳሳተ መልእክት ስለማሳወቅ ይመለከታል።
እንደሚታወቀው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የሚመራውና በስደት ላይ የሚገኘው ሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እነሆ፥ ዘርፈ ብዙ የሆኑ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በተደራጀና በተጠናከረ መልኩ ለሕዝባችን ለመስጠት እንዲችል የጠቅላይ ቤተ ክህነት መዋቅርን ዘርግቷል። የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የሆነውን ቅዱስ ሲኖዶስ አጠቃላይ ተቋማዊ ይዘት ለማጠናከርና ሁለንተናዊ እንቅስቃሴውን በቅርብ ለመርዳት ዘወትር በትጋት የሚሠራው ጠቅላይ ቤተ ክህነት በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያዊ ትውፊትን ጠብቀው፥ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በሚፈቅደው መሠረት ሁሉም በጋራ እንዲተዳደሩ ለማድረግ ቀኖና ሐዋርያትን፥ ጥንታውያን የቤተ ክርስቲያን ጉባኤያት ውሳኔዎችንና ድንጋጌዎችን፥ እንዲሁም ለሦስተኛ ጊዜ ተሻሽሎ በ1991 ዓ.ም የወጣውን ቃለ ዓዋዲና በስደት ዓለም የሚገኙትን አብያተ ክርስቲያናት በአንድነት ለመምራትና ለማስተዳደር ቀደም ሲል በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ የወጣውንና በከፊል ሥራ ላይ የዋለውን ውስጠ ደንብ ዋቢ በማድረግ ቀዋሚ የቅዱስ ሲኖዶስ መተዳደሪያ ሕግ ረቂቅ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል።
ስለሆነም ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም. በኦክላንድ መካነ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ባካሔደው ፴፱ኛው የርክበ ካህናት ጉባኤ ላይ የመተዳደሪያ ሕጉ ረቂቅ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ኃላፊነት ካህናትንና ም እመናንን ያካተተ ኮሚቴ ተቋቁሞ እንዲጠና እና አስፈላጊው እርማትና ማሻሻያ ተደርጎበት የመጨረሻው ረቂቅ ለጥቅምት ፳፻፯ ዓ.ም. ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ ወስኗል። ስለሆነም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰብሳቢነት ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ ሊቀ ጳጳስ፣ መልአከ አርያም ቆሞስ አባ ጽጌ ድንግል ደገፋው፣ አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡና መምህር አንዱዓለም ዳግማዊ ከካህናት እንዲሁም በቅርቡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከተቋቋመው የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ሦስት ተወካዮች አቶ ደጀኔ፣ ዶ/ር ሰሎሞንና አቶ ምርጫው በመሆን በመተዳደሪያ ሕጉ ረቂቅ ላይ ጥልቅ ጥናትና ሰፊ ውይይቶችን በማድረግ በጥቅምት ወር ፪፻፯ ዓ.ም በኮሎምበስ፥ ኦሐዮ በተካሔደው ዓመታዊው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል። በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስ የኮሚቴውን ትጋትና ያላሰለሰ ጥረት በማመስገን የኮሚቴው አባላቱ በጥር ወር 2007 ዓ.ም. በሎስ አንጀለስ ከተማ በአካል ተገናኝተው የመጨረሻውን ረቂቅ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያስረክቡና ቋሚ ሲኖዶስም ሰነዱን በሚገባ ተመልክቶ ከሸኚ ደብዳቤ ጋር በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ለሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት እንዲልክ ተወስኗል። ይህ በዚህ እንዳለ በቅርቡ ከቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅናና መመሪያ ውጪ እዲሁም ቅዱስ ሲኖዶስ ውክልና በአልሰጣቸውና ማንነታቸው በማይታወቁ ግለሰቦች “የቅዱስ ሲኖዶስ መተዳደሪያ ሕግ” በሚል ኅዳር 19ቀን 2007 ዓ.ም. በተጻፈ አራት ገጽ የመሸኛ ደብዳቤ ጋር በሕገ ወጥነት ለየአብያተ ክርስቲያናት የተበተነውን የተሳሳተ መልእክት አስመልክቶ ቋሚ
Tel: 310-621-4588 – Fax: 323-291-0733 – www.eotcholysynod.com-eotcholysynod2@gmail.com – P.O. Box 88117, Los Angeles, CA 90009 1
ሲኖዶስ ረቡዕ ታኅሣሥ 22 ቀን 2007 ዓ.ም ባደረገው ልዩ ስብሰባ በሰፊው ተወያይቶ ምእመናን በጉዳዩ ግራ እንዳይጋቡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አስቸኳይ ደብዳቤ ለአብያተ ክርስቲያናት እንዲላክ ተወስኗል።
ስለሆነም ይህ ደብዳቤ ከደረሳችሁ ጊዜ ጀምሮ በእጃችሁ የገባውን የስሕተት ሰነድ ውድቅ እንድታደርጉና ከሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው መመሪያ መሠረት በቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ ኃላፊነት የተሰጠው አካል በአዲስ መልክ የተዘጋጀውን የቅዱስ ሲኖዶስ መተዳደሪያ ሕግ በቅርቡ አጠናቅቆ ለቋሚ ሲኖዶስ ሲያስረክብ በሕጋዊ መልኩ የሚደርሳችሁ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን። በዚህ አጋጣሚ “የቅዱስ ሲኖዶስ መተዳደሪያ ሕግ” በሚል ከመሸኛ ደብዳቤ ጋር እውቅና በአልተሰጣቸው ግለሰቦች ለአብያተ ክርስቲያናት የተበተነው ቅዱስ ሲኖዶስ በማዘጋጀት ላይ ያለውን የመተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ እንዳለ በመገልበጥ/በመውሰድ የተሠራ ሥራ ስለሆነ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን እየገለጽን እንዲህ ዓይነቱን የአሠራር ብልሹነት በጋራ ለመከላከል እንዲቻል ለወደፊቱ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ወይም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ውጪ በማንኛውም አካል መልእክት ሲደርሳችሁ በቀጥታ ቅዱስ ሲኖዶስን/ጠቅላይ ቤተ ክህነትን በማነጋገር ለመረዳት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን።
“እግዚአብሔር አምላክ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሰላምና በአንድነት ይጠብቅልን!”
ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
ለመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
ለቋሚ ሲኖዶስ አባላት በያሉበት
Tel: 310-621-4588, Fax: 323-291-0733, www.eotcholysynod.org, eotcholysynod2@gmail.com, P.O. Box 7097, Los Angeles, CA 90007 2
Average Rating