www.maledatimes.com በቴዲ አፍሮ ሰርግ ላይ ጎሳዬ ተስፋዬ ባይገርምሽ ገና እወድሻለሁ በሚለው የቴዲ አፍሮ ዘፈን ሰርፕራይዝ አደረገው። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በቴዲ አፍሮ ሰርግ ላይ ጎሳዬ ተስፋዬ ባይገርምሽ ገና እወድሻለሁ በሚለው የቴዲ አፍሮ ዘፈን ሰርፕራይዝ አደረገው።

By   /   September 27, 2012  /   2 Comments

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 48 Second

በዛሬው እለት እየተከናወነ ያለው የቴዲ ሰርግ በከፍተኛ ድምቀት ከመከበሩሩም በላይ የአዲስ አበባ መንገዶች ተዘግተው የቴዲ አፍሮን ፎቶ ግራፍ በመያዝ እንወድሃለን ! መልካም ትዳር እነመኝልሃለን ! ድንቅ አርቲስት ነህ በሚሉ እና ሌሎችም ታላልቅ እና የውዳሴ ቃላት በማጀብ አድናቂዎቹ እና ወዳጆቹ የሰርጉን ሁኔታ በመንገድ ላይ አድምቀውለታል ። በተለይም የኢትዮጵያን ታላላቅ አርቲስቶች በመድረክ ላይ በመሆን በዘፈኖቻቸው ውዳሴአቸውን ያቀረቡ ሲሆን የተወሰኑ ዘፋኞችም ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ናቸው ።ይህንን ሪፖርት እስካጠናቀርንበት ሰአት ድረስ ጎሳዬ ተስፋዬ ባይገርምሽ ገና እወድሻለሁ የሚለውን ዜማውን የተጫወተለት ሲሆን ቴዲ አፍሮ በደስታ ሲቃ ሲተናነቀው ተስትውሎአል ።የተለያዩ ከባድ እና ታላላቅ ስጦታዎችም ተበርክተውለታል; በተያያዘ ዜና ወላጅ እናቱ  ራዬ በመድረክ ላይ ግጥም አቅርባለታለች፣ ሸዋንዳኝ በአሁን ሰአት ሸዋንዳኝ መድረክ ላይ እየተጫወተ ይገኛል ቀጣዩ ደግሞ አለማየሁ እሸቴ የሚዘፍን ሲሆን ታደለ ሮባ እና ዳዊት መለሰ እናራሱ ቴዲ አፍሮ ዘፈን እንደሚዘፍኑም ተገልጦአል ዳዊት መለሰ እና ታደለ ሮባ ለሁለተኛ ጊዜ መድረኩን ሊያጋፍሩት እንደሚችሉ ለማለዳ ታይምስ ከስፍራው የደረሰው ዜና ዘገባ ያመለክታል ።ከዝግጅቱ ስፍራ ላሉት ታላላቅ አርቲስቶች የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ባደርግንላቸው የስልክ ጥሪዎች ብዙዎቹ ምላሽ ለማድረግ እንዳልቻሉ እና በስራው እና በጫጫታው ምክንያት ብዙም መረጃ መቀባበል እንዳልቻሉ ጠቁመው በአሁን ሰአት ይህንን መረጃ ለሚከታተሉ ሁሉ ደስታችን በጣም የላቀ ስለሆነ ደስ ይበላችሁ ሲሉ ገልጸዋል ከአንድ ሰአት በኋላ መልሰን ጠቅለል ያለ ሪፖርት ይዘን እንመለሳለን ብለውን ተሰናብተውናል ።ለማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል አዲስ አበባ 

Gosaye Sings at Teddy Afro Wedding at Hilton Hotel

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

2 thoughts on “በቴዲ አፍሮ ሰርግ ላይ ጎሳዬ ተስፋዬ ባይገርምሽ ገና እወድሻለሁ በሚለው የቴዲ አፍሮ ዘፈን ሰርፕራይዝ አደረገው።

  1. በቴዲ አፍሮ ሰርግ ላይ ጎሳዬ ተስፋዬ ባይገርምሽ ገና እወድሻለሁ በሚለው የቴዲ አፍሮ ዘፈን ሰርፕራይዝ አደረገው።

    No Amharic equivalent for ‘surprise’?

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar