ቪዲዮውን ይመልከቱት…
ኢትዮጵያዊቷ ዱባይ ውስጥ በሞግዚትነት የምታሳድጋቸውን 4 ልጆች ባህር ለመስመጥ አድናቸው እርሷ የባህር ሲሳይ ሆና ቀረች፡፡
ሶፍያ ለረጅም …አመታት በዱባይ በሞግዚትነት ስትሰራ ኖራለች፡፡ አንድ አርብ ቀን የምትሰራባቸው ሰዎች እሷን ጨምሮ ማለት ነው ለመዝናናት እዛው ዱባይ ውስጥ ወደ ሚገኝ ባህር ዳር ይሄዳሉ፡፡ የሰላት ሰአት ሲደርስ ወንዶቹ ለመስገድ ወደ መስጊድ ሄደዋል፡፡ ሶፍያና በሞግዚትነት የምታሳድጋቸው 4 ልጆች ጨምሮ ሌሎች ሴት የቤተሰቡ አባላት እዛው ከባህሩ ዳር እየተዝናኑ ናቸው፡፡
ለሶላት ስግደት ያልሄዱት ሴቶቹ የቤተሰቡ አባላት ፈንጠር ብለው ተቀምጠዋል፡፡ ሶፍያና 4ቱ ልጆች ከባህሩ አጠገብ እየተጫወቱ ነው፡፡ አራቱም ልጆች ወደ ባህር ለመዋኘት ገቡ፡፡ በመሀል ላይ ይሰወሩባታል፡፡ ሁሉንም የልጆቹን ጥበቃ ሀላፊነት ሰጥተዋት ፈንጠር ብለው የተቀመጡት ሴቶች ሊደርሱላቸው አልቻሉም፡፡ ምክንያቱም መስመጣቸውን አላዩም፡፡ ሶፊያ ዘላ ወደ ባህር ትገባና አራቱንም ልጆች ተራ በተራ ታወጣቸዋለች፡፡ አሳዛኙ ነገር የተፈጠረው ከዚህ በኋላ ነው፡፡ ሶፊያ እነሱን ብታድንም እሷ አልዳነችም፡፡ አራቱን ልጆች እንደምንም ተሯሩጣ ካወጣቻቸው በኋላ ራሷን ከባርህ ውስጥ ለማውጣት ብትንደፋደፍም አቅም ስላጣች ራሷን ማዳን አልቻለችም፡፡ የባህር ሲሳይ ሆና ሬሳዋ እንኳን ሳይገኝ ቀረ፡፡
በተፈጠረው ነገር አሰሪዎቿ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቷዋል፡፡ አብራቸው በቆየችባቸው አመታት ለአሰሪዎቿ ልጆቻቸው መልካም እንደነበረች በዱባይ ቴሌቪዥን ሲቀርቡ ተናግረዋል፡፡ በደረሰው ነገር እንዳዘኑ ጭምር ገልጸዋል፡፡ ወደ የተወሰነው የቤተሰብ አባል ወደ ኢትዮጵያ ሄደው የሶፍያን ልጆች እንሚጠይቁና ሶፍያ በወር ትቀበለው የነበረው ደሞዝ በህይወት አስካሉ ድረስ ለልጆቿ በየወሩ እንደሚልኩ አሰሪዎቿ ቃል ገብተዋል፡፡ አሰሪዎቿ በዱባይ ቴሌቭዥን ላይ እንደተናገሩት
Average Rating