www.maledatimes.com በፍስሃ ዘውዱ ላይ የተፈጸመው ግድያ፣ የትግሬ-ወያኔ ቡድን የደረሰበትን የከፋ የዘረኝነት ደረጃ ማሣያ ነው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በፍስሃ ዘውዱ ላይ የተፈጸመው ግድያ፣ የትግሬ-ወያኔ ቡድን የደረሰበትን የከፋ የዘረኝነት ደረጃ ማሣያ ነው

By   /   February 8, 2015  /   Comments Off on በፍስሃ ዘውዱ ላይ የተፈጸመው ግድያ፣ የትግሬ-ወያኔ ቡድን የደረሰበትን የከፋ የዘረኝነት ደረጃ ማሣያ ነው

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 23 Second

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             አርብ ጥር ፳፱ ቀን ፪ሺህ፯  ዓ.ም.                        ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፱

 የትግሬ-ወያኔ ቡድን ከናዚ ጀርመን እና ከፋሽስት ጣሊያኖች የከፋ፣ የሚመራበትም ርዕዮተ-ዓለም ከቅል አንገት የጠበበ ዘረኛ ቡድን ነው። ቡድኑ «እናቴ ትግሬ ባልሆንሽ» የሚባልበት ጊዜ ይመጣል የሚባለውን ትንቢት አስፈጻሚ መሆኑን በዐማራው ነገድ ተወላጆች፣ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታዮች፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚፈጽማቸው ተግባሮች አፍ አውጥተው እየተናገሩ ነው። ዐማራን፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖትን፣ በጥቅሉ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን አጥፍቶ የትግራይን ሕዝብ ለማስጠፋት የተፈጠረ መከራ-ጠሪ እና አጥፊ መሆኑን ከሚያሣዩት አያሌ ማስረጃዎች መካከል ሰሞኑን «ፍስሃ ዘውዱ» የተባለውን ባለራዕይ ወጣት የገደሉበት ምክንያት ከበቂ በላይ ያስረዳል።

ከዜና ምንጮች የተሠራጩት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ፍስሃ ዘውዱ ዓይነ አፋር፣ ትሑት እና በመንፈሣዊ ሕይዎቱ የጠነከረ እንደነበር ያስረዳሉ። ፍስሃ የብሩሕ አዕምሮ ባለቤት ከመሆኑ የተነሣ በትምህርት ዘመኑ በደረጃ የሚቀድመው ተማሪ አልነበረም። የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀውም በከፍተኛ ውጤት መሆኑን አስተማሪዎቹ ምስክርነታቸውን መስጠታቸውን የኢትዮጵያ ሣቴላይት ቴሌቪዥን እና ራዲዮ አረጋግጧል። በዚህ ውጤቱም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የውኃ ቴክኖሎጅ መርኃግብር በመግባት ለአምስት ዓመታት የሚሰጠውን ትምህርት ለማጠናቀቅ የቀረው ጊዜ አምስት ወራት ብቻ ነበር። በትምህርት ቤት ቆይታው ባስመዘገበው እጅግ ከፍተኛ የሆነ ውጤት፣ ዩኒቨርሲቲው ከምረቃ በኋላ በመምህርነት ለማስቀረት ካጫቸው ተማሪዎች መካከል በመጀመሪያው ረድፍ የተሰለፈ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ፍስሃ አጥባቂ የኦርቶዶስ ተዋሕዶ ኃይማኖት አማኝ፣ የኢትዮጵያዊነት ዕሴቶች ተንከባካቢ እና አራማጅ፣ ብልህ እና ጎበዝ፣ እንዲሁም ለራሱ፣ ለቤተሰቡ እና ለአገሩ ብሩሕ ራዕይ የሰነቀ ወጣት ነበር።

ሆኖም የዚህን ወጣት ራዕይ እና ሕልም፣ ለአምስት ዓመታት ከጎኑ ቁጭ ብሎ ሲያስተውል የነበረው ብሥራት ኪሮስ የተባለው ተማሪ ዕውን እንዲሆን አልፈለገም። ብሥራት ኪሮስ የዐድዋ አውራጃ ተወላጅ ትግሬ መሆኑ ታውቋል። ይህ ግለሰብ ከፍስሃ ጋር ለ፭(አምሥት) ዓመታት አብሮት በአንድ ማዕድ የበላ፣ እንዲሁም በአንድ ክፍል አብሮት የተማረ ነበር። ሆኖም የትግሬ-ወያኔ ድርጅት አባል የሆነው ብሥራት ኪሮስ፣ በጠባብ የዘር ፖለቲካ ደዌ የተለከፈ በመሆኑ፣ «ትግሬ ያልሆነ ተማሪ፣ ያውም በእኛ በትግሬዎች አገር ባለ ዩኒቨርሲቲ፣ እኛን በትምህርት በልጦ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ መምህር ሆኖ መቅረት የለበትም» በሚል እርኩስ፣ ፍፁም ዘረኛ እና ፀረ-ዐማራ በሆነ እምነቱ ተነሳስቶ በማንአለብኝነት የመግደሉን አሣዛኝ መርዶ ሰማን። ይህንን መርዶ እኛ የሞረሽ-ወገኔ አባሎች የሰማነው እጅግ በሚዘገንን የመጠቃት እና «ወይ ትግሬ ለካ እንደዚህ ነበራችሁ» በሚል ስሜት ነው። የፍስሃ ዘውዱ ገዳይ፣ «ባንድ ደንጋይ ሁለት ወፍ» የሚባለውን ፈጽሟል፥ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታዩን እና የዐማራ ተወላጁን ፍስሃ ዘውዱን ገድሏል።

የፍስሃ ዘውዱ ወላጆች፣ ዘመዶች እና ጓደኞች፥ አይዞን እንበራታ! በደላችሁ በደላችን ነው። ሐዘናችሁ ሐዘናችን ነው። የፍስሃ ደም ግን በከንቱ ፈስሶ፣ ደመከል ሆነ አይቀርም። አያሌ ጀግኖችን እየተጣራ ነው። አያሌ ፍስሃዎችን ይወልዳል፣ ያስነሣል። ብሥራት ኪሮስ የተማመነበት ሥርዓት እና የሥርዓቱ አራማጆች የሆኑት የትግሬ-ወያኔ ቡድን አባሎች የመፋረጃ ቀናቸውን ራሣቸው እያሣጠሩት መምጣታቸውን የፍስሃ አገዳደል በጉልህ ያሣያል። ስለዚህ ጎልያድን በዳዊት ወንጭፍ መሬት ያገባ አምላክ፣ የሚሊዮኖችን ደም ያፈሰሰውን የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ዕድሜ የሚያሣጥርበት የፍርድ ቀን ሩቅ እንደማይሆን ጭላንጭሉ እየታዬ ነው።

የዐማራ ነገድ አባል የሆናችሁ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታይ የሆናችሁ፣ በጥቅሉ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ለብሔራዊ ጥቅሟ መከበር፣ እና ለሉዓላዊነቷ መረጋገጥ የቆማችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ሁሉ፥ የፍስሃ ዘውዱ ግድያ በሁላችንም ላይ የተፈጸመ ግድያ መሆኑን አውቀን የትግሬ-ወያኔን ለመፋረድ በአንድነት እንድንነሣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በፍስሃ ዘውዱ ስም ጥሪውን ያቀርባል።

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

ኢትዮጵያ በጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on February 8, 2015
  • By:
  • Last Modified: February 8, 2015 @ 6:56 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar