www.maledatimes.com በየመን UNHCR ስደተኞችን ጥሎ ቢሮ ዘግቶ ወጣ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በየመን UNHCR ስደተኞችን ጥሎ ቢሮ ዘግቶ ወጣ

By   /   February 13, 2015  /   Comments Off on በየመን UNHCR ስደተኞችን ጥሎ ቢሮ ዘግቶ ወጣ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 22 Second

በየመን UNHCR ስደተኞችን ጥሎ ቢሮ ዘግቶ ወጣ

በግሩም ተ/ሀይማኖት

የመን ለስላሳ ምጥ እያማጠች ነው፡፡ ወይ አልወለደችው ወይ አላጨናገፈችው፡፡ ምጧ ልጆቿን በየአደባባዩ እንዲወድቁ እያደረገ ነው፡፡ እስከ አሁን በስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰ ምንም ችግር ባይኖርም መጻዒው ሂደት ግን ድቅድቅ ጨለማነቱን እያስተነበየ ነው፡፡ ከሳዕዳ የተነሱት የሁቲይን ሚኒሻዎች ዋና ከተማዋ ሰነዓን ከተቆጣጠሩ ሶስተኛ ወራቸው ነው፡፡ ስልጣን አልፈልግም የሚሉት ሁቲይኖች ስልጣን ላይ ያለው አካል የሚሰራውን ከኋላ ሆነን እንቆጣጠራለን ብለው ነበር፡፡ አረቡ አለም ላይ የተካሄደው አብዮት የሽግግር መንግስት ፕሬዘዳንት ያደረጋቸው አብዱረቡ ሀዴ መንሱር ማዘዝ፣ ማስራት አልቻልኩም ስልጣኔን በገዛ ፍቃዴ ለቅቄያለሁ ካሉ ሳምንት አለፋቸው፡፡ ፓርላማው ስልጣን መልቀቃቸውን ባያጸድቀውም የሽግግር መንግስት ለመመስረት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ተደጋጋሚ ስብሰባ አድርገዋል፡፡ የቀድሞው ፕሬዘዳንት አሊ አብደላ ሳላህ የሚመሩት ሙክተመር ፓርቲ በፓርላማ በኩል ጊዜያዊ ፕሬዘዳንት ምርጫ እንዲደረግ ቢፈልጉም የሁቲይን ባለስልጣኖች አልተቀበሉትም፡፡

ለዚህ ደግሞ እንደምክንያት የታየው በፓርላማ ውስጥ አብላጫው ወንበር እሳቸው በሚመሩት ሙክተመር ፓርቲ የተያዘ ስለሆነ ስልጣን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ያመራል በሚል ነው፡፡ በሞቫንቢክ ሆቴል የተካሄደው የፓርቲዎቹ ስብሰባ ከስምምነት እርከን ላይ አልደረሰም፡፡ ስለዚህ የፕሬዘዳንትነት ማማ ላይ ያወጣው ሰው ባለመኖሩ ስልጣኑ በእጄ ነው የመረጥኩትን እኔ ስልጣን ላይ አወጣለሁ በማለት ሁቲይኖች አሳወቁ፡፡

ነገሮች ከዚህ በኋላ እየከረሩም እያከራከሩም መጡ፡፡ ደጋፊና ተቃዋሚዎች በተለያየ ጎራ ሰልፍ መውጣት ጀመሩ፡፡ የጥይት ጩኸት ሳይለያት ለከረመችው የመን ሞቅ ደመቅ ብሎ ማስተጋባቱ ቀጠለ፡፡ በተለይ ከዋና ከተማዋ ሰነዓ ውጭ ያለው ሁኔታ ጥይት የሰው ገላ ቦድሶ ማለፍ የበዛበት ነው፡፡ ያለው ሁኔታ እየባሰ እንጂ እየቀነሰ ባለመታየቱ አሜሪካና እንግሊዝ ኤምባሲዎቻቸውን ዘግተው መረጃዎቻቸውን አጥፍተው ወጡ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ጽፈት ቤት UNHCR ቢሮውን ዘግቶ ስደተኛውን በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ጥሎ ወጣ፡፡ አሜሪካ ኤምባሲን ሰብረው ገብተው የፈለጉትን እቃና 20 አካባቢ መኪና መውሰዳቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ፡፡ ለራሳቸው ህይወት የፈሩት የስደተኛው ህይወትን ከምንም ያልቆጠሩት የ UNHCR ቢሮ ሰራተኞች የመናዊያኑ የቢሮው ሰራተኞች በየቤታቸው ሆነው ስደተኛውን እንዲያገለግሉ ትዕዛዝ አውጥቷል፡፡ ዋናው የስደተኞች ቢሮ ምን እያሰበ እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on February 13, 2015
  • By:
  • Last Modified: February 13, 2015 @ 7:37 am
  • Filed Under: Ethiopia

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar