www.maledatimes.com እየከፋ በመጣው የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ የጋራ አቋም መግለጫ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እየከፋ በመጣው የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ የጋራ አቋም መግለጫ

By   /   February 15, 2015  /   Comments Off on እየከፋ በመጣው የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ የጋራ አቋም መግለጫ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 55 Second

 

ከፖለቲካ ሲቪክ የሃይማኖት ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች

 

«ለውጥ በማይቆም ተሽከርካሪ የሚጓዝ አይደለም፤ የተከታታይ ትግል ውጤት ነው። ነጻነት የምንፈልግ ሁሉ ጀርባችንን ቀና አድርገን መታገል አለብን። ራሳችን ካልፈቀድንለትና ካልተሸማቀቅን፤ ማንም ሰው እንደ ከብት ሊጋልበን ከቶ አይችልም” ነበር ያሉት ዶር ማርቲን ሉዘር ኪንግ ጁኔር ።

 

በማንኛውም አገር ቢሆን፣  ነጻ የሆነ የዜና አገልግሎት የማያገኝ፤ ተቆርቋሪ የፖለቲካ ወይንም የማህበረሰብ ወይንም የሲቪክ ድርጅት እና በነጻነት የሚንቀሳቀስ የመገናኛ ብዙሃን አገልግሎች የሌለው  ሕዝብ መብት የለውም። መብቱ በመንግሥት የተከለከለ ግለሰብ ሆነ ቡድን፤ ማህበረሰብ ሆነ ሕብረተሰብ ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው እድገት አይጎናፀፍም።

 

ሕወሃት/ኢሕአዴግ ለሃያ አራት ዓመታት በበላይነት ሲገዛት የቆየችዋ ኢትዮጵያችን  ፍትህ፤ ነጻነት፤ ሰብአዊ መብት፤ የሕግ የበላይነት  የማይታይባትና  አምባገነናዊ ስርዓት የሰፈነባት ሃገር ሆናለች። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ የመድበል ፓርቲ ስርዓት የምትከተል መሆኗ በሕግ መንግስቱ ቢደነገግም፣ በተግባር የታየው ግን ከገዝው ሕወሃት/ኢሕአዴግ ነጻ የሆኑ ድርጅቶችን ሁሉ የማጥፋት ሂደት ነው። የአገሪቷን ሕግ ሆነ የምርጫ ቦርድን አሰራር  በጣሰ መልኩ፣ በቅርቡ በአገሪቷ ጠንካራ የሚባለውን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)  አመራርን በማገድ ራሱ ያቋቋማቸዉን ተለጣፊ መሪወች መሾሙ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ  በምርጫ የማያምንና፣ ብቻውን ለሚቀጥሉት ሃያ፤ ሰላሳ አመታት በጉልበት ለመግዛት እንደወሰነ አመላካች ነው። የዜጎችን የመደራጅትና የመሰባሰብ ሰባአዊ መብትም የረገጠ ነው።

 

በአንድነት ፓርቲ ላይ ከታየው የሕወሃት/ኢሕአዴግ ያገጠጠ ኢፍትሃዊ እርምጃ በተጨማሪ፣ በሌሎች የፖለቲካና የሲቪክ ማሀብራት ላይ አፈናዉና የመብት ረገጣው ተባብሷል፡፡በህጋዊነት የሚንቀሳቀሱ ድርጀቶች ሁሉ ህልውናቸው አደጋ ላይ ነው። ዜጎችን ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሰረት ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ ይደበደባሉ። ጋዜጠኞች የሰባዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሃይማኖት መሪዎች ይታሰራሉ።

 

ሕወሃት/ኢሕአዴግ  በሚያራምዳቸው የተሳሳቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ዜጎች  ባስከፊ በድህነት እና የኑሮ ዉድነት ስቃይ ዉስጥ እንዲዘፌቁ አድርጓቸዋል። የስራ እድል ማጣት፤ የተፈጥሮ ሃብት ከኢትዮጵያዊያን ተነጥቆ ለጥቂቶች ሃብት ማካበቻ መሆን፤ የጎሳ አድልዎ፤ ጉቦ፤ ሙስና፤ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከሕግ ውጭ ማሸሽ፤ በኢትዮጵያዉያን መካከል ስርዓት ወለድ የሆነ የጎሳና የኃይማኖት መለያየት በአገራችን ትልቅ ቀዉስን እና ዉስጣዊ አለመረጋጋትን ፈጥሯል። ከመቼዉም ጊዜ በላይ አገራችን ትልቅ አደጋ ላይ ትገኛለች።

 

መንግስት የሕዝብ አገልጋይ ሊሆን ይገባዋል። ህወሃት/ኢሕአዴጎች ግን በመንግስት ወንበር ላይ ተቀምጠው ህዝብን ማገለገል ሳይሆን ህዝቡን እየከፋፈሉትእና  እያሰቃዩት ነው። ለሃያ አራት አመታት በህዝብ እና በሀገር ላይ እጅግ ብዙ በደል ፈጽመዋል።  ይህን ለማስቆም ኢትዮጵያዉያን ቆርጠንና  ደፍረን፣  አገር አቀፍ በሆነ ደረጃ መነሳት ይኖርብናል። በውጭና በውስጥ የምንገኘው ለውጥ እና ፍትህ ፈላጊ  ኃይላት፣ አብረን ተባብረን መስራት ግዴታችን ሆኗል። ሕወሃት የሚፈልገው በየተራ ለማጥቃት እንዲያመቸው በተናጥል የሚደረግን  ትግል ነው። ትግሉ የመኖር ያለመኖር፤  የህልውና ጉዳይ ስለሆነ አብሮ ተያይዞ መነሳት የወቅቱ መሪ ጥያቄ ነው።

 

እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተዘረዘረው ስብስቦች እንደዚህ ያለ ተከታታይ ግፍ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ሲካሄድ በአንድ ላይ ድምፃችን ማሰማት ግዴታችን ነው እንላለን። ስለሆነም፤

 

  1. በቅርቡ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላትን ህገወጥ በሆነ መንገድ የገዝው ቡድን መሳሪያ በሆነው የምርጫ ቦርድ አማካንነት ከሀላፊነታቸው በግዳጅ አባሮ በአባላት ያልተመረጠ ግለስብ በመሪነት መሾሙን አጥብቀን እናወግዛለን። ለዚህ በስርአቱ ለተሾመ ግለሰብም፣ እውቅና የማንሰጥ ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትብብር እንዲነፍገው እንጠይቃለን። የተለጣፊው ቡድንም፣ ሊወድቅ የተቃረበን የግፍ አገዛዝ ለማገለገል በወሰዳቸው አሳፋሪ ተግባራትም ተጠያቂ እንደሚሆን ለማሳሰብ እንወዳለን።
  2. ስርአቱ በመኢአድ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባትና በቀጣይ የከፋፋይነት ስራ ድርጅቱን ለማዳከም የሚያካሂደውን ሁሉ ተገንዝበናል። ይህ የገዥው እኩይ ተግባር እውን የሚሆነው በከፊል በድርጅቱ ውስጥ ያሉትን ችግሮች በመመካከር ማስወገድ ሳይቻል ሲቀርና ለገዥው ቡድንም ጣልቃ መግባት መንግድ ሲከፍት እንደሆነ በመገንዘብ፣ ሁሉም የድርጅቱ መሪወችና አባላት ውስጠ ድርጅት ቅራኔወችን በውስጥ አሰራር፣ በመቻቻል፣ በሆደሰፊነትና በተለመደ ሀገራዊ ጨዋነት በመፍታት ሁሉም የድርጅቱ አባላት እንዲሰባሰቡና ታሪካዊ ሀላፊነታቸውን በጋራ እንዲወጡ  እናበረታታለን።
  3. ገዥው ቡድን በአንድነት ፓርቲ ላይ የማፈራረስ እርምጃ ሲወስድ የድርጅቱ አባላት ፣ ተስፋ ቆርጠው፣ ትግሉን እርግፍ አድርገው እንዲያቆሙ ወይም ሀገር ጥለው እንዲሰደዱ ለማድረግ ነው። ይህን በማድረግም አላንዳች ተቀናቃኝ ሁሉንም ተቆጣጥሮ በህዝባችን እና በሀገራችን ላይ የጀመረውን የግፍ አገዛዝ ለመቀጠል ነው። ሆኖም ሁላችንም እንደተመለከትነው አፍራሹን ህወሀት/ኢህአዴግን በሚያሳፍር ለውጥ ፈላጊውን ደግሞ በሚያኮራ መልክ በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ያሉ በዛ አሉ የአንድነት አባላት አሁንም ትግሉን ለመቀጠል ወደ ሰማያዊ ፓርቲ እየተቀላቀሉ መሆናቸውን እንገነዘባለን። በዚህ እጅግ ፈታኝ በሆነ ሰዓት ከድርጅት በላይ ሀገርንና ነጻነትን በማሰቀደም በወሰዱት ቆራጥ እርምጃ ያለንን አድናቆት እየገለጥን ወደ ሰማያዊ ያልተቀላቀሉ ጥቂት የአንድነት አባላትም የአንድነትና የዴሞክራሲ ሀይሎችን በመቀላቀል ትግላቻውን እንዲቀጥሉ እናበረታታለን።
  4. ሁሉም የአንድነትና የዴሞክራሲ ሀይሎች የህወሀት/ኢህአዴግን ቀጣይ አፈና መቋቋም የሚቻለው ተነታጥሎ ሳይሆን በጋራ በመቆም እንደሆነ በመገንዘብ አሁንም ትብብራቸውን አጠናክርው ትግላቸውን እንዲቀጥሉ እናሳስባለን። በአፋኙ የህወሀት/ኢህአዴግ ስርአት ስር ለሀገር አንድነት፣ለህዝብ መብት መከበርና ግፈኛውና ከፋፋይ ስርአት ተደምስሶ በምትኩ ለህዝብ ሙሉ መብት መከበር፣ ለሀገር እንድነትና፣ ዴሞክራሲያዊ ህገ መንግስታዊ ስርአትን ለመመስረት ለሚደረገው ትግል ያለንን አጋርነት በጋራ እናረጋግጣለን።

 

ነጻነት ዋጋ ያስከፍላል። ነጻነት ስለተመኘናት አትመጣም። የኛ እጅ ለእጅ መያያዝና መተባበር የአምባገነኖች ፍጻሜ መጀመርያ ነው። በመሆኑም በተጨበጡ ሥራዎች ዙሪያ ትብብራችንን እያጠናከረን፣ አገር ቤት ለሚደረገው ትግል ሙሉ ድጋፍ እያሳየን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አካል እንደመሆናችን የህዝባችን ነጻነት እስኪያረጋግጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሳንታክት በጽናት የምንታገል ስለመሆናችን ቃል ኪዳናችንን እናድሳለን።

 

  1. የሴቶች  የሰብዓዊ መብት ድርጅት
  2. የኢትዮጵያ ሽግግር ምክር ቤት
  3. የሰማያዊ ድጋፍ ማሀበራት
  4. የአንድነት የስዊዱን ድጋፍ ማህበር
  5. የአንድነት የለንደን ድጋፍ ማሀብር
  6. የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ
  7. ሞዓ አንበሳ
  8. የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስረኞች አንድነት ድርጅት በካናዳ (ሶሴፕ ካናዳ)
  9. ጋሻ ለኢትዮጰያ የሲቪክ ድርጅት
  10. ኢትዮጰያዊነት የሲቪክ ድርጅት
  11. ኢትዮ ሶሊዳሪቲ ሚኔሶታ
  12. የአንድነት የሰሜን አሜሪክ የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ኮሚቴ
  13. የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንገፐ (በስሩ የሚገኙት አባል ድርጅቶች ሁሉ
  • የኢትዮጵያሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ዴሞክራሲያዊ)
  • የኢትዮጵያመድህን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (መድህን)
  • ትግራይዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት)
  • መላኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መ.ኢ.ሶ.ን)
  • የኢትዮጵያሲቪክ ማህበራት ስብስብ በእንግሊዝ ሀገር
  • የኢትዮጵያየፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ (ኢፓእአኮ)
  • ኢትዮጵያሲቪል ኅብረተሰብ ደጋፊዎች በለንደን ኦንታሪዮ
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on February 15, 2015
  • By:
  • Last Modified: February 15, 2015 @ 12:26 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar