www.maledatimes.com ከወልድባ ወደ ዝቋላ ።።። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከወልድባ ወደ ዝቋላ ።።።

By   /   February 28, 2015  /   Comments Off on ከወልድባ ወደ ዝቋላ ።።።

    Print       Email
0 0
Read Time:8 Minute, 21 Second

Zemedkun Bekele

።።።ከወልድባ ወZemedkun Bekele added 6 new photos — with Enana ALemu.

መቼም በዚህ ዘመን የምንጽፍበትም ፣ የምንነጋገርበትንም የማያልቅ አጀንዳ ዓለማችን እየፈበረከች መስጠቷን ባለማቋረጧ ለዛሬም ዓለም ተወያዩበት ብላ በሰጠችን አጀንዳ ዙሪያ ኃሳባችንን እናቀርባለን ።

፨፨፨ የግብፅ መንግሥት ፨፨፨

በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተመሰረተን በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይዞታ ስር ያለን ገዳም በልማት ስም ለማፍረስ መንግሥቱ ቡልደዘር ይዞ ቀረበ ።

፨፨፨ የግብፅ ኦርቶዶክስ መነኮሳት ፨፨፨

ልማቱን ሳይቃወሙ ካልጠፋ ቦታ ለልማት የተመረጠው ሥፍራ እጅግ ጥንታዊና በቅርስነት እንኳን ቢያዝ ለሃገሪቱ ጭምር ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው ብለው ድርጊቱን ተቃወሙ ።

፨፨፨ የግብፅ መንግሥት ፨፨፨

በእንቢታው ጸና ። ባለሙያዎችን እና ቡልዶዘሮችን ወደስፍራው በመላክ መቆፈር ጀመረ ።

፨፨፨ የግብፅ ኦርቶዶክስ መነኮሳት ፨፨፨

ነገሩ በመንግሥት በኩል ቁርጥ መሆኑን ባወቁ ጊዜ ግን እርምጃ ወሰዱ ። በዘመናት ውስጥ 1600 ዓም ዘልቆ በእሳት ውስጥ ተፈትኖ በማለፍ ከዚህ እነሱ ካሉበት ዘመን የደረሰውን ገዳም ዓይናቸው እያየ ሲፈርስ መመልከቱን አልተቀበሉትም ። እናም ቡልዶዘሮቹ ሥራ ሊጀምሩ ሞተር ሲያስነሱ እነሱም ተነሱ ። በቡልዶዘሮቹ ፊት ከመሬት ተነጥፈው ተኙ ። አብረህ ፍጨን ፣ ጨፍልቀን ፣ ከአሸዋው ከአፈሩ ቀላቅለን አሉ ። እነዚህ አባቶች ከሳምንታት በፊት 21 ልጆቻቸውን በሊቢያ በረሃ በሜዲትራንያን ባህር አጠገብ በሰማዕትነት ሲያልፉ በማየት የሰማዕታቱን ታሪካቸውን በቤተክርስቲያኗ ስንክሳር ላይ ጽፈው መታሰቢያቸውን መዘክር የጀመሩበት ጊዜ መሆኑን በማሰብ እነሱም እንዳስተማሩዋቸው ልጆቻቸው ሰማዕትነትን ተመኙ ።

፨፨፨ የግብፅ መንግሥት ፨፨፨

የመነኮሳቱን የእምነት ጽናት ፣ ለሃይማኖታቸው ያላቸውን ታማኝነት ፣ ሞትና ዓለምን የናቁ ፣ እሳት ፣ ሰይፉንና ስለቱን የማይፈሩ፣ የሚሞቱ እንጂ የማይገድሉ የሰማዕታቱ ልጆች መሆናቸውን በሚገባ ያውቃልና ፕሮጀክቱን አቆመ ።

፨፨፨ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፨፨፨

ካልጠፋ ቦታ ለ700 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ይዞታ ስር በሚገኘው በታላቁ የዝቋላ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም ውስጥ የእሬቻን የአምልኮ ሥርዓት እፈጽማለሁ በማለት ወሰነ ። ወስኖም አልቀረም በብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ ጭምር ቀን ቆርጦና ወስኖ ዜናውን አስነገረ ።

፨፨፨ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መነኮሳት ፨፨፨

ቅዱስ ፓትራያርኩ አቡነ ማትያስ በደብዳቤ ፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕም በደብዳቤ ፣ የገዳሙ ማኅበረ መነኮሳት ግን በግንባር ተቃውሞአቸውን አቅርበዋል ። ቅዱስነታቸው እንደውም በሚድያ የክልሉ መንግሥት ያስተላለፈውን በጽኑ በመቃወም ማስተካከያና ስህተት መሠራቱን ጭምር በዚያው በሚድያ የክልሉ መንግሥት እንዲያርም አሳሰቡ ።

፨፨፨ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፨፨፨

በቅዱስ ፓትርያርኩ ፣ በሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ፣ በገዳሙ መነኮሳትና ፣ በኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን የቀረበለትን ሁኔታው አደጋ አለውና ይስተካከል የሚለውን የተማጽኖ ቃል ወደ ጎን በመተው ይባስ ብለው “እንደውም እናንተ መጣችሁብን እንጂ እኛ አልመጣንባችሁም ፣ ስትፈልጉ ወደ ክልላችሁ ሂዱ ፣ በዝቋላ እንኳን ሃውልት ማቆምና የእሬቻን በአል ማክበር አይደለም ውሻ አርደን መስዋዕት ብናቀርብ እንኳ መብታችን ነው ። የሚከለክለንንም እናያለን የሚል ዛቻ እየተሰማ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል ።

፨፨፨ የእኔ ፍራቻ ፨፨፨

ይህ ነገር እዚህ ላይ በእንጭጩ ካልተቀጨና ማረሚያ ካልተደረገለት በቀር ወደፊት በሃገራችን በኢትዮጵያ በሕዝቧ እና በእምነቶች መካከል ከፍተኛ የሆነ መቃቃርና ያለመተማመን ይፈጠራል ። ካልጠፋ ቦታ ባለቤቱን እንኳን ሰው ሰይጣን ራሱ የሚያውቀውን ቅዱስና ታሪካዊ ሥፍራ መተናኮል ለማንኛችንም አይበጅም ። በእስራኤል ብዙ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ሥፍራዎች በፍልስጤማውያን አረብ የእስልምና እምነት ተከታዮች ነው በክብር ተጠብቀው የሚገኙት ። በተለይ ጌታ በተወለደባት የቤተልሔም ዋሻ ፤ ቤተ መቅደሱ የሚገኘው በፍልስጤም ሲሆን ባለቤቶቹ ክርስተያኖች ናቸው ። ጠባቂዎችና ተንከባካቢዎቹ ደግሞ ፖሊስና ወታደሮቹ ጭምር ሙስሊሞች ናቸው ። እነዚህ ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን ልቀቁልን ፣ ጥፉ ከዚህ ፣ አይሉም ። ብለውም አያውቁም ።

ጌታ የተሰቀለበትን ቀራንዮ ፣ የተጠመቀበትን ዮርዳኖስን ሌሎችም ብዙ የክርስቲያን ይዞታዎች በእስራኤል አይሁዶች ሀገር ውስጥ ነው ያሉት ። አይሁድ ደግሞ ኢየሱስ የሚለውን ስም መስማት እንኳን የማይፈልጉ ናቸው ። አይሁድ ጌታን የገረፉት ፣ የሰቀሉት ፣ የገደሉት ፣ እነሱ መሆናቸውን በኩራት እየተናገሩም ቢሆን ። ክርስቲያኖችን ውጡልን ፣ ተመለሱ ፣ እዚህ ጋር ሙክራብ ሠርተን መስገድ መብታችን ነው ብለው ክርስቲያኖችን ተተናኩለው አያውቁም ። እንደውም ክርስቲያኖች የአምልኮ ስርአታቸውን ሲፈጽሙ የሚረብሻቸው ነገር እንዳይፈጠር ዘመናዊ መሳርያ በታጠቁ የተደራጁ ወታደሮች 24 ሰዓት ሙሉ ዓመት እስከ ዓመትጥበቃ ያደርጋሉ እንጂ ።

የእኛን ጉዳይ ግን አሁን በዝቋላ የተፈጠረውን ክስተት ማለትነው ነገሩን እንዲያው ዝም ብዬ በአትኩሮት ሳየው ” ጠብ ያለሽ በዳቦ ይመስላል “

የሆነው ሆኗል አሁንም ነገሮችን ለማስተካከል አልረፈደብንም ። ሁሉም ግን የሥራ ድርሻውን እና ኃላፊነቱን ይውሰድ ።

የክልሉ መንግሥት ፤

ነገሩን ያብርድ ፣ ቦታ ይቀየር ፣ ለዝቋላ ገዳም እና በክልሉ ለሚገኙ ገዳማትና አድባራት ጭምር አስፈላጊውን ጥበቃ ያድርግ ።

የፌደራል መንግሥት ፣

ጉዳዩ በብሔራዊ ቴሌቪዥን የተላለፈና የደብዳቤ ልውውጥም እየተደረገበት ህዝብ በተፈጠረው ነገር እየተወያየበት ያለ ጉዳይ ስለሆነ በጊዜ በጉዳዩ ጣልቃ በመግባት ሙቀቱን ያብርድ ደግሞም ያቀዝቅዝ ።

ቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ፣

በጀመሩት መንገድ በጉዳዩ ይግፉበት ፣ ከቅዱስ ሲኖዶሱም አባለት ከአባቶችዎም ጋር ይምከሩበት ፣ ገዳማውያኑንም ያጽናኑ ፣ ምእመናንንም እያረጋጉ ።

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ፣

የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ እንደመሆንዎ መጠን በተለያዩ ሥራዎች ከክልሉ መንግሥት ባለስልጣናት እና ሹመኞች ጋር የመገናኘት ዕድሉ ከሌሎች ሰዎች በበለጠ ስለሚኖርዎት ጉዳዩን ለክልሉ መንግሥት ኋላፊዎችና ለቅዱስ ሲኖዶስ አባለት ከማሳሰብ ቸል እንዳይሉ ። ገዳማውያኑንም ያረጋጉ ።

ገዳማውያን አባቶቻችን ፣

እስካአሁን ድረስም በብዙ መከራና ፈተና ውስጥ ማለፋችሁን ከደብዳቤዎቻችሁ ተረድተናል ። ማስፈራሪያና ዛቻዎችን ጭምር በመታገስ ከመጀመሪያው ጀምሮ ጉዳዩ ወደ ህዝብ እንዳይወርድ እና እዚያው በአጭሩ ተቀጭቶ እንዲያልቅ የሄዳችሁበት መንገድም ያስመሰግናችኋል ። አሁንም ከጸሎትና ከዕንባ ጋር ልመናችሁን ወደ አምላከ ገብረመንፈስ ቅዱስ ማሳሰቡን ቀጥሉበት ፣ እንዳታቋርጡ ። አደራ።

የገዳ ስርአትና የእሬቻ በአል አክባሪዎች፣

ሃገራችን ሰፊ ናት ። ካልጠፋ ቦታ ዝቋላ ተራራ ላይ ከገዳሙ ውስጥ በጸበሉ ሥፍራ ላይ ውጡ ያሉዋችሁን አትስሙዋቸው ። ለምን ብላችሁ ጠይቋቸው ። ደግሞ የኦሮሞ ሽማግሌ ረጋ ያለ ነው ። አስሬ ለክቶ አንዴ የሚቆርጥ ። ምክሩ እንደ እርጎ አንጀት የሚያርስም ነው። ምርቃቱም እንደዚያው ። የኦሮሞ አባቶቻችን ለልጆቻችሁ ” ለኪ ዲሳ ወኒ ኩኒ ዋንተኡሚቲ ። ረኮ ቀባ ጄዳቲ ጆሌ ኬሰኒቲ ሂማ ። ” ገለቶማ ።

እኛ ምእመናንም ፣

ነገሩን በጥንቃቄ እንመልከት ። ቤተክርስቲያን የምትለንን እንጠብቅ ። ጉዳዩን በትኩረት እንከታተል ። ስሜታዊ እንሁን ። ከየትኛውም ፀብ አጫሪ ድርጊት እንቆጠብ ። እንደ ርግብ የዋህ ፣ እንደ እባብም ብልህ እንሁን ። ከዚህ ሁሉ አልፎ የመጣውን ግን ናቡቴን መሆን እንጂ ሌላ አማራጭ አይኖረንም ። “የአባቶቼን ርስት አልሰጥም ” እንዳለ ናቡቴ ። 2ኛ ነገስ 20 ፣ 3

እኛ በገዳዮቻቸው ፊት እንኳን ቆመው ለገዳዮች ምህረትን የሚለምኑ የሰማዕታት ልጆች መሆናችንን አንዘንጋ ።

ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሃገራችን !!!

እንደተለመደው በጨዋ ደንብ እንወያይ ። የሌሎችን ስህተት የሚያርምና ገንቢ አስተያየትም እንስጥ ። በእኔ ጽሑፍ ላይ Comment እና Share ይበረታታል ይደገፋልም ። ለ Like ግን ብዙም ግድ አይሰጠኝም ። መልእክቱን ሳያነቡም ላይክ አያድርጉ ።

ዘመድኩን በቀለ ነኝ

የካቲት 20/6/2007 ዓም

አዲስአበባ— ኢትዮጵያደ ዝቋላ ።።።

አዲስአበባ— ኢትዮጵያ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on February 28, 2015
  • By:
  • Last Modified: February 28, 2015 @ 9:34 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar