www.maledatimes.com ቴድሮስ አድሃኖም ያራገቡት የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት የፈጠራ ወሬ መሆኑ ተረጋገጠ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ቴድሮስ አድሃኖም ያራገቡት የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት የፈጠራ ወሬ መሆኑ ተረጋገጠ

By   /   March 2, 2015  /   Comments Off on ቴድሮስ አድሃኖም ያራገቡት የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት የፈጠራ ወሬ መሆኑ ተረጋገጠ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 30 Second

የአውስትራሊያ መንግስት እና የሮተሪ ፋውንዴሽን በሪቱ ጃለታን አናውቃትም ገንዘብም አልሰጠንም አሉ
በአበበ ገላው
(አዲስ ቮይስ) ሰሞኑን የህወሃት መራሹ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአንድ የአውስትራሊያ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ውድድር አሸናፊ በመሆን እና አስደናቂ ውጤት በማምስመዝገብ 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በማሸነፍ ያገኘችውን ገንዘብ ለልማት ለማዋል ኢትዮጵያ ትገኛለች የተባለችን የ14 አመት ልጅ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድረ ገጾች ከማስተዋወቅ አልፈው በቢሯቸው ከልጅቷ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።
ሚኒስትሩ በሪቱ ጃለታ አህመድ ገና በለጋ እድሜዋ ይህን ያህል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለልማት በማዋሏ ለኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ ለዲያስፖራው አርአያ መሆኗን በይፋ አውጀው ነበር። ወጣቷ የሽልማት ገንዘቡን በሙሉ አባቷ አቶ ጃለታ አህመድ በተወለዱበት በምስራቅ ሀረርጌ፣ ጋራ ሙለታ፣ ትምህርት ቤት ልታሰራበት ማቀዷን ለጋዜጠኞች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝታ ከሚኒስትሩ ጋር በጋራ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ያደረገች ሲሆን ገንዘቡ የተገኘው ከፊሉ ከአውስትራሊያ መንግስት፣ ከፊሉ ደግሞ ከአውስትራሊያ የሮተሪ ክለብ መሆኑን ይፋ አድርጋ ነበር።
ይሁንና ሸልማቱን አዘጋጀ የተባለው ባደን ፓወል ኮሌጅ በመባል የሚጠራው የመንግስት ትምህርት ቤት ስለጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ ግራ በመጋባት ጉዳዩን ለምርመራ ወደ ፖሊስ መምራቱን ለማረጋገጥ የቻልን ሲሆን የአውስታራሊያ መንግስት እና ሮታሪ ፋውንዴሽን በበኩላቸው ለአዲስ ቮይስ በተናጠል በሰጡት መግለጫ እንዳረጋገጡት ለታዳጊዋ ምንም አይነት ገንዘብ አለመስጠታቸውን እንዲሁም ስለ እርሷም ሆነ ስለተባለው ውድድርና ሽልማት ሰምተው እንደማያውቁ አረጋግጠዋል።
የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይና ንግድ ሚኒስቴር በጹሁፍ በላከልን መግለጫ አንደገለጸው የአውስትራሊያ መንግስት በኢትዮጵያ ጋራ ሙለታ ትምህርት ቤት ለማሰራት 10 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ መባሉን አስተባብሏል። ሚኒስቴሩ አክሎም በኢትዮጵያ ለትምርት በቀጥታ ድጋፍ ባይሰጥም ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገሮች ጋር ተጠቃሚ በሆነችበት አለም አቀፍ የትምህርት የጋራ ትብብር (Global Education Partnership) በኩል ድጋፍ እንደሚሰጥ ጠቁሞ ኢትዮጵያ በትብብሩ በኩል በሚሰጠው የገንዘብ እርዳታ ተጠቃሚ ነች በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጄና ሃንድ አክለው ገልጸዋል።
በአውስትራሊያ የሮታሪ ፋውንዴሽን ስራ አስኪያጅ የሆኑት ብሩስ አለን በበኩላቸው ስለ ተሸላሚዋም ልጅም ይሁን ስለሽልማቱ ከዚህ በፊት ሰምተው እንደማያውቁ አስገንዝበው ድርጅቱ የተባለውን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ እንኳን ለልጅ ሊሰጥ ለራሱም የበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በቂ ገንዘብ እንደሌለው አስረግጠው ተናግረዋል። ስራ አስኪያጁ አክለው እንደገለጹትም ባለፈው አመት የበጀት አመት ሮተሪ በ አውስትራሊያ ያሰባሰበው ገንዘብ መጠን 5.6 ብቻ መ
ሆኑን ጠቁመው 10 ሚሊዮን ዶላር ለልጅቷ በሽልማት መልክ ሰጠ መባሉ በጣም የሚያሳዝን ክስተት መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው አመት ሮታሪ ኢንተርናሽናል በአለም አቀፍ ለትምህርት ነክ እንቅስቃሰዎች የሰጠው ገንዘብ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በቻ የበረ ሲሆን ይህም ገንዘንብ ለ66 ፕሮጄክቶች መከፋፈሉን ለማወቅ ተችሏል።
ከዚህ በፊት በአለም ላይ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቀውን ይህን “ታልቅ ውድድር” እና የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አዘጋጀ የተባለው የአውስትራሊያው የመንግስት ትምህርት ቤት1800 ተማሪዮችና 180 ሰራተኞች የሚሆኑ ያለከፍያ በበጎ አቃድ የሚሰሩ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን አመታዊ በጀቱ 12 ሚልዮን የአውስትራሊያ ዶላር ነው። ይህም ማለት የትምህርት ቤቱ አመታዊ በጀት ለ14 አመቷ ልጅ ሰጠ ከተባለው ሽልማት በ8 ሚሊዮን ዶላር የሚያንስ ሲሆን የሽልማት ገንዘቡን ትምህርት ቤቱ እንዴት እንዳሟላው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ይሁኑ ተሸላሚዋ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ማብራሪያ አልሰጡም።
ሌላው አስገራሚ ጉዳይ በሪቱ ሽልማቱን አገኝ በተባለው ያለፈው የበጀት አመት የአውስትራሊያ መንግስት በገዘብ እጦት ምክንያት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገሮች የሚሰጠውን እርዳታ መጠን ከ225 ሚሊዮን በ37በመቶ በመቀነስ ወደ 133 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በመቀነሱ በአለም አቀፍ ደረጃ ሲተች የበነረ ሲሆን የበጀት ቅነሳ ያደረገው ለልጅቷ ለመስጠት አለመሆኑን ግን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።
ይሁንና ይህ ጉዳይ በዙዎች ዘንድ ሆን ተብሎ ለስውር አልማ የዋለ የህወሃት ውስብስብ ተንኮል ጋር የተያያዘ ነው በማለት ጥራጣሪያቸውን በስፋት በመግለጽ ላይ ይገኛል ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on March 2, 2015
  • By:
  • Last Modified: March 2, 2015 @ 4:48 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar