www.maledatimes.com የ” ወሳኙ ማዕበል” ዘመቻ 9ኛ ቀን ውሎ አበይት ክንውኖች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የ” ወሳኙ ማዕበል” ዘመቻ 9ኛ ቀን ውሎ አበይት ክንውኖች

By   /   April 5, 2015  /   Comments Off on የ” ወሳኙ ማዕበል” ዘመቻ 9ኛ ቀን ውሎ አበይት ክንውኖች

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 28 Second

የመረጃ ግብአት…

===================================

* በ9ኛ  ቀን በሳውዲ መራሹ  ” ወሳኙ ማዕበል !” የአየር ማጥቃት ዘመቻ በየመን  ሰማይ በተጠኑ ወታደራዊ የሁቲ አማጽያን ይዞታዎች ላይ አየር ድብደባው መቀጠሉን የዘመቻው መምሪያ ቃል አቀባይ ብ.ጀኔራል አህመድ አሲሪ ናቸው ፣ ጀኔራሉ በዚሁ መግለጫች በወደብ ከተማዋ በኤደንም የሁቲ አማጽያ አልበገርላቸው ካለው የአካባቢ ሚኒሽያ ጋር ውጊያ መግጠማቸውን አስረድተዋል

* ከሁቲ አማጽያንን ኤደንን እንዳይቆጣጠሩ በአካባቢው ሚኒሽያ በመሬት ቃታ እየሳበ እንቅስቃቀሴያቸውን ሲያሽመደምደው በሰማይ የህብረቱን ጦር በተጠኑ  ኢላማዎች ላይ እንዲያተኩር በማድረግ በሚከወነው ድብደባ አማጽያኑን አቅመ ቢስ አድርጎ እንዳዳከማቸው ቃል አቀባዩ ተናግረዋል

*  ቃል አቀባዩ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ሰርጎ የሚገባባትን በሚዮን ደሴት Meon Island የሚገኙ የባህርና ሃይሉና የእግረኛው  ጦር መሳሪያዊች በሳውዲ መራሹ የአየር ድብደባ ኢላማ ገብተው ተደምስሰዋልም ብለዋል

* በአየር ድብደባው ተስፋ የቆረጡና የተዳከሙት የሁቲ አማጽያን በመገናኛ ብዙሃንን ከእውነት የራቁ መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን በማሳሳት ላይ ናቸውም ብለዋል ብ.ጀኔራል አህመድ አሲሪ

* በሌላ በኩል እየተካሔደ ስላለው ዘመቻ ማብራሪያ የሰጡት በአሜሪካ የሳውዲ አንባሳደር አድል አልጃብሪ  ዘመቻው በጥሩና በመጥፎ መካከል እንጅ በሱኒና በሸአ የእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል ሚካሔድ ጦርነት አለመሆኑን ተናግርዋል።  አምባሳደሩ በማከልም የሳውዲ መራሹ አረብ ሃገራት ዋና አላማ በኢራን በሂዝቦላህ የሚመራውን የሁቲ አማጽያን ከስልጣን አስወግዶ ፣  ህጋዊው የፕሬዚ አብድልረቡ መንግስት ወደ ቦታው መመለስ ነው ብለዋል ። አንባሳደሩ የቀድሞው የየመን ፕሬዚ አሊ አብደላህ ሳላህን በሚመለከት ሲናገሩ አሊ አብደላ ሳላህ ከሁቲዎች ጎን መሰለፋቸው  የተሳሳተ አካሄድ ነው ሲሉ ነቅፈውታል

በሳውዲ የመን ደንበር ድንበር መገዳደል …
============================

* በሳውዲ የመን ድንበር ባሳለፍነው ረቡዕ አንድ ድንበር ጠባቂ በሳውዲ የመን ድንበር ሁለት የድንበር ጠባቂ መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን ትናንት አርብ ተጨማሪ ሁለት ወታደሮች መሞታቸውን ተጠቅሷል ። መረጃውን የድንበር ጦሩ ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል  አዎል ቢን ኢድ አል በላዊ አረጋግጠውታል

* የሳውዲው ንጉስ  ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ የሟች የድንበር ወታደር ቤተሰቦችን ልዩ የሀዘን መልዕክተኞች በመላክ  አጽናንተዋል

ከዘመቻው ድጋፍ እስከ የመንን መልሶ መገንባት  ….
================================

* በሳውዲ ታላላቅ ምሁራንና ታላላቅ የሐይማኖት አባቶች በሳውዲ መራሹን የየመን አየር ድብደባ ድጋፋቸውን እየሰጡ ነው

* የመን ከሁቴ አማጽያን ጠርታ የፕሬዚደንት አብድል ረቡ መንሱር ሃዲ መንግስት በሁቲ አማጽያን የተቀማውን ስልጣን ተቀብሎ የመን ስትረጋጋ የባህረ ሰላጤው ባለ ሃብቶች 150 በላይ ፕሮጀክቶችን በመክፈት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የማፍሰስ እቅድ መያዛቸው ተጠቅሷል
( መቸ ይመጣ ይሆን?  ብቻ ለዚያ ቀን ያድርሰን …)

በየመን የኢትዮ ይዞታና  የ” እውነት ፣ ውሸቱ”  እሰጣ ገባ
===================================

* በየመን የኢትዮጵያ ኢንባሲ ጥቃት እንደደረሰበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖምና መስሪያ ቤታቸው ከቀናት በፊት ፣ ቀጥሎም የኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ቢያስታውቁም የተላለፈው መረጃ አነጋጋሪ ሆኗል።  በተባራሪ ጥይት በኢንባሲው የሚገኝን አንድ መኪና ጎማ መታ ተብሎ ጥቀሰት ብሎ ማቅረቡ የተጋነነ መሆኑን ከየመን ሰንአ የደረሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ

* በየመን ሰንአ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ዲፕሎማቶች ሳይሆኑ የኮሚኒቲ  ሰራተኞች ለመመለስ ፍላጎት ያላቸውን ተመላሽ ዜጋዎች በመመዝገብ ላይ መሆናቸው ተጠቅሷል ። የኢንባሲውን መደብደብ ዜና የሰሙት በቦታው ያሉትን የኮሚኒቲ ተወካዮች ሳይቀር በሚኒስትሩ ኢንባሲው ተጠቃ በሚል በቀረበው መረጃ ግራ የተጋቡ እንደነበር የአይን እማኞች ጠቁመዋል

*  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም ” በየመን ሰነአ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ጥቃት ደረሰበት!”  ያሉትን ሰሞኛ ዝርዝር መረጃ ያልቀረበበት አነጋጋሪ መረጃቸውን  ተከትሎ ” ከአውስትራልያ የመጣች ታዳጊ 20 ሚሊዮን… ለገሰች !” እንደተባለችው ታዳጊ ወጣት ስጦታ ገንዘብ ምንጭ ዙሪያ የተደረገውን ያህል ሙግት እሰጣ ገባ የየመኑ ጥቀሰት ባይገንም  ” እውነት ፣ ውሸቱ ”  ግን ቀጥሏል
( አሜሪካ ቢሆን ይህ ይደምቅ ነበር ያሉኝ አሉ: )  )

* ከቀናት በፊት በኤደን የመን አድርገው ጅቡቲ የገቡት 30  ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት መግባታቸው ተጠቁሟል ፣ ”  ወደ ሃገር ቤት መግባቱ ለደህንነታችን ያሰጋናል !”  ያሉት ግን ወደ ሶስተኛ ሃገር የሚሻገሩበትን መንገድ በመላ አለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ድምጻቸውን እናሰማላቸው ዘንድ በመማጸን ላይ ናቸው   !

እስኪ ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on April 5, 2015
  • By:
  • Last Modified: April 5, 2015 @ 7:39 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar