ከቀድሞው ስራ አስኪያጁ ከአቶ አዲስ ገሰሰ በሁዋላ የተተካው አቶ ዘካሪያስ ጌታቸው ከስራ አስኪያጅነቱ መፈናቀሉን እና በምትኩ የቴዎድሮስ ካሳሁን ባለቤት የሆነችው ወ/ሮ አምለሰት ሙጬ በስራ አስኪያጅነት ቦታ ተክታ እንደምትሰራ ምንጮጫችን ከአዲስ አበባ ገለጠዋል ። አቶ ቴወድሮስ ካሳሁን እና አቶ ዘካሪያስ ጌታቸው በተገናኙበት የሰራ ዘርፍ ጠንካራ የሆነ ግኑኝነት የነበራቸው ሲሆነ በአሁን ሰአት ግን በቴዲ አፍሮ የውስጥ የጥርጣሬ መንፈስ ስራ አሰኪያጁን ከስራ ያባረረ መሆኑን የተገለፀ ቢሆኑም በቋሚነት ስራ አስኪያጅ ሊሆን የታቀደ ሰው አለመኖሩን ቢጠቆምም የሙዚቃ ክህሎትም ሆነ የህዝብ ግኑኙነት ዘርፍ እውቀት የሌላትን ባለቤቱን አምለሰት ሙጬን መተካቱ የቴዲ አፍሮ የኪሳራ እና የውድቀት ጉዞ ነው ሲሉ ተችተውታል።
አቶ ዘካሪያስ ጌታቸው ስራ አሰኪያጅ ከሆነ ጊዜ ጀምሮ የቴዲ አፍሮ አሰራር ሂደትም ሆነ የኔትወርክ ስራ በጥሩ ሁኔታ ከመፋጠኑም በላይ በተለያዩ የሶሻል ኔትወርኮች እንዲታወቅ እና ስራዎቹ በፍጥነት ለአለም እንዲደርሱ ከፍተኛውን አስተዋፅዖ ያደረገ ስራአስኪያጅ ሲሆን በሌላም በኩል ለረጅም አመታት ሳይጐበኝ ተቀምጦ የነበረውን የቴዲ አፍሮ ዌብሳይት በሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኝዎች እንዲኖሩት ከመጣርም በላይ በአይቱን እና በሌላም የሙዚቃ መሸጫ ሱቆች ወደ $14000 ሙዚቃዎቹ እንዲሸጡ ያደረገለት ስራ አስኪያጁን ማባረሩንም ሆነ በሌላ መንገድ መጠርጠር የቴዲ አፍሮ ደካማነት ነው ሲሉ ጠቁመው ቴዲ አፍሮ አበረው ከሚሰሩት ጋር በሚያደርገው የገንዘብ ከፍያ የሰራቸውን በአግባቡ እነደማያገኙ ሁሉ ከቀድሞው ሰራ አሰኪያጅ ጀምሮ እሰካሁኑ እነዲሁም የቀደሞው ጊታር ተጨዋቹ አበራ አለሙ ከስራ መልቀቅ ምክንያት ይሄው መሆኑን እና ከአቶ ዘካሪያስም ጋር የተፈጠረው ጉዳይ የሄው ሳይሆን አይቀርም የሚል መደምደሚያ ላይ ተደርሶአል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቴዲ አፍሮ እና ዘካሪያስ ጌታቸው በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ከበአል በሁዋላ በአዲስ አበባ ተገናኝተው እንደሚነጋገሩ የተጠቆመ ሲሆን በዚሁ አለመግባባቱ ከሰፋ እና አቶ ዘካሪያስ ጌታቸው ጉዳዩን ወደክስ ከመራው የቴዲ አፍሮ ውድቀት ይሆናል ሲሉ ምንጮቻችን የገለጡ ሲሆን ቴዲ አፍሮ ሊያስብበት የሚገባ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ማወቅ ይገባዋል ሲሉ አሳውቀዋል።
የበአል ዝግጅት በቴዲ አፍሮ ቤት ያደርጋል ተብሎ የሚጠበቀው ድርጅት የኢቢአስ የቴሌቪዥን ጣቢያ ይህንን መረጃ አጠጠናክሮ ይጠይቀዋል ብለን እናስባለን ።የዚህ ዜና ጥንቅር በማለዳ ታይምሰ መረጃ ማእከል የተሰራ ነው።
Average Rating