የመረጃ ግብአት …
“የወሳኙ ማዕበል ” ዘመቻ የመሰንበቻው አበይት ክንውኖች !
========================
የዘመቻው ቃል አቀባይ መግለጫ …
=======================
* የወሳኙ ማዕበል ሳውዲ መራሽ ዘመቻ በሁቲ አማጽያንን ላይ ከተጀመረ ወዲህ የአማጽያኑን የመከላከልና የማጥቃት አቅም ለማዳከም 1200 የአየር ጥቃቶች መደረጋቸውን የዘመቻው ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በሶስተኛ ሳምንት በደፈነው ዘመቻ ገለጻቸው አስታውቀዋል
* አማጽያኑ በተከፈተባቸው የህብረቱ አየር ድብደባ በከፍተኛ ሁኔታ የአየር ሀይልና የምድር ጦር መሽመድመ ዳቸውን ቃል አቀባዩ ሲያስታውቁ በየመን ግዛቶች በሸብዋን ፣ አብያን ፣ ላህጅና ያፍዕ በምድርም አማጽያኑን የሚቃወሙ ሀገር ወዳድ የጎሳ መሪ የመናውያን ጠመንጃ አንስተው እየተፋለሟቸው መሆኑን ጠቁመዋለል። የህብረቱ ቃል አቀባይ በማከልም በምድር የተጀመረውን የየመናውያን እንቅስቃሴ ህብረቱ ድጋፍ እንደሚሰጠውም ተናግረዋል
* የኢራንና የሂዝቦላህ ሁቲዎችን በመደገፍና በማሰልጠን በየመን ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸው አዲስ አለመሆኑን የጠቆሙት ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል አህመድ አሲሪ በመግለጫቸው ተያዙ ስለተባሉት ሁለት ኢራናውያን ተጠይቀው መያዛቸውን አረጋግጠዋል
* በየትኛውም የባህር ፣ የምድርም ሆነ በአየር መገናኛዎች የሁቲ አማጽያን ድጋፍ ሊያገኙ የሚችሉባቸው መንገዶች ሁሉ መዘጋጋታቸውም የሳውዲ መራሹ ዘመቻ ቃል አቀባይ ተጠቁሟል
* ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ 35 ሽህ ቶን ሰብአዊ እርዳታ የያዘች የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል አውሮፕላን ዘመቻው ለተጀመረ ለሁለተኛ ጊዜ የመን ሰንአ ገብታለች
* የፖኪስታን ፖርላማ የሀገሪቱ ጦር ለሳውዲ ህልውና ያለውን ጽኑ ድጋፍ ቢያረጋግጥም በሳውዲ የሚመራውን የአረብ ሀገራት በየመን ሁቲ ላይ የከፈቱትን የወሳኙ ማዕበል ዘመቻ ጦሩ እንደማይቀላቀል ውሳኔ ማሳለፉ የገልፍ ሀገራትን አላስደሰተም
* የኢራን ፕሬዚደንት ሀሰን ሮሄኒ የየመን ጦርነት በውይይት መፈታት አለበት ሲሉ የመንግስት የበላይ የሆኑት የሀይማኖት አባት አያቶላህ አሊ ሆሜኒ በበኩላቸው ሳውዲ አረቢያ በየመን የዘይዲ ጎሳ የሁቲ ተዋጊዎች ላይ የወሰደችውን የአየር ድብደባ ” የሰው ዘር ማጥፋት ነው !” ሲሉ ባሳለፍነው ሳምንት አጥብቀው ኮንነውታል
* በእስካሁኑ የየመን ግጭት 643 ነፍስ ሲቀጠፍ 2,200 ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የአለም አቀፍ ጥበቃ ድርጅት World Health Organisation መረጃ ጠቁሟል
የሳውዲ የመን ድንበር ውጥረት …
======================
* በነጅራንና በጀዛን በሚዋሰኑት የሳውዲ የመን የጠረፍ ከተሞች ከዚህ ቀደም ከሞቱት 3 የሳውዲ ድንበር ጠባቂ ወታደሮች በተጨማሪ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ 3 የሳውዲ ድንበር ወታደሮች በነጅራን ድንበር መሞታቸው ሲጠቆም 500 ያህል የሁቲ አማጽያን የወሳኙ ማዕበል ዘመቻ ከተጀመረ መገደላቸውን የህብረቱ ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል አህመድ አሲሪ አስታውቀዋል
* የሳውዲ የመን የጠረፍ የገጠር መንደሮች የሚገኙ ከ900 በላይ ሳውዲ አባዎራዎች ለደህንነታቸው ሲባል ከአካባቢው ተነስተው ወደ ውስጥ ከተማ እንዲሰፍሩ ተደርጓል
* ከየመን በጦርነቱ እየተፈናቀሉ እየሸሹ ወደ ሳውዲ የሚገቡት የመናውያን ቁጠር ከፍ እያለ መምጣቱ ተዘግቧል
* በሳውዲ የጠረፍ ከተሞች የሚገኙ ት ት/ቤቶች ለደህንነት ሲባል ተዘግተዋል
ኢትዮጵያውያን በየመን …
=================
* ዛሬም ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የየመን ከተሞች በጭንቅ ላይ ናቸው ፣ በሰንአ ጦርነቱን ተከትሎ ህገ ወጥነት ሲንሰራፋ ፣ ኑሮው ተወዶ እሳት ሆኗል ፣ ከተባበሩት መንግስታት መጠለያና ከመጠለያ ውጭ ያሉ ዜጎች በአደጋ በጦርነት መካከል የድረሱልን ዋይታቸውን እያሰሙ ነው
* በሰማይ የህብረቱ ጦር የአየር ድብደባ ፣ በምድር የሁቲና በተቃዋሚዎቻቸው ፍልሚያ ሰላሟን የነሳት ሁለተኛዋ የየመን ጥንታዊ የወደበረ ከተማ በኤደን ያሉ ኢትዮጵያውያን ከከባቸው አደጋ አንጻር የሚይዙት የሚጨብጡት አጥተዋል ፣ ደራሽ ባያገኙም “ድረሱልን!” እያሉ ነው!
* መሪ በሌላትና በጦርነት ሁከት እየፈራረሰች ባለችው ሀገረ የመን የተለያዩ ከተሞች ” በህገ ወጥ መንገድ ወደ የመን ገባችሁ! ” ተብለውና በሌላም ሌላ ጥቃቅን ጉዳዮች ለተለያዩ እስር የተዳረጉ ዜጎቻችን የረሃብ ጥማቱ ችጋር በርትቶባቸው በአደጋ ላይ መሆናቸውን እየሰማን ነው
* 700 ያህል ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሀይማኖት ሲያስረዳ ፣ ጠኔ ረሀቡ በርቶባቸው ከሰንአ አቅራቢያ ያለ አንድ እስር ቤትን ሰብረው ሊወጡ ሲሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን የመገደላቸውን ፣ 11 ያህል የመቁሰላቸውንና የተረፉት በጠባቂዎች ዱላ መነረታቸውን ከወደ ሰንአ ግሩም ተክለ ሀይማኖት የተገደሉት ኢትዮጵያን በፈሰሰበት መሬት ላይ ቆሞ እንደነበረ በገለጸልን ልብ ሰባሪ መረጃውን ጠቁሞናል
* ከአውሮፓ ሀገራት እስከ እስያና ሩቅ ምስራቅ ሀገራት በየመን ያሉ ዜጎቻቸውን ለማውጣት ተረባርበው ተሳክቶላቸዋል ።
* የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎችን ለማውጣት መዝገባ በጀመረ ማግስት 30 ዜጎቹ በኤደን በኩል በጅቡቲ አድርገው ወደ ሀገር ቤት መግታቸውን አስታውቋል ። ማን ረድቶ አሸጋገራቸው የሚለው አሁንም አወዛጋቢ ቢሆንም መግባታቸው ግን እውነት ነው
* መንግስት በቀጣይ ዜጎችን ከየመን ለመመለስ ” ጥረት እየተደረገ ነው !” ተብሎ እስካሁን 3000 ገደማ መታወቂያና ፖስፖርት ያላቸው ተመርጠው መመዝገባቸው ይጠቀሳል
* ከተመዘገቡት መካከል ወደ ሀገር ትመለሳላችሁ ተብለው ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ መሳፈሪያው ያመሩ ሳይሳካላቸው ተመልሰዋል
* ምዝገባው መታወቂያና ፖስፖርት ያላቸውን ብቻ ስለሚያካትት በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መጠለያ የነበሩት ኢትዮጵያውያን እና በባህር የገቡ ፖስፖርትና መታወቂያ የሌላቸው ተንገዋለው መቅረታቸውን በምሬት እየተናገሩ ነው ። ያም ሁሉ ሆኖ መስፈርቱን አሟልተው እየተለዩ ከተመዘገቡት ውስጥ ወደ ሀገር የተመለሰ እስካሁን አልታየም ፣ አልተሰማም !
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 5 ቀን 2007 ዓም
Average Rating