ለእረጅም ጊዜ በጉጉት በሰሜን አሚሪካ ይገባሉ ተብሎ ሲጠበቁ የነበሩት እና በአሁን ሰአት በሚኖሶታ የመጀመሪያውን ስብሰባቸውን ያደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ አመራር (ሊቀመንበር) የሆኑት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በነገው እለት በችካጎ ከተማ ደማቅ ስብሰባ እንደሚያካሂዱ ተጠቆመ ። በነገው እለት በሊዊስ ሚሞርያል ሆስፒታል አዳራሽ የሚከናወነው ስብሰባ በ፪፡00 ሰአት የሚጀመር ሲሆን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እና የኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ለዚህ ስብሰባ ተሳታፊ እንዲሆን አስተባባሪዎቹ ጥሪ አቅርበዋል ። የሰማያዊ ፓርቲ የመጀመሪያው የሆነው አለም አቀፍ የስብሰባ ጥሪ በሰሜን አሜሪካ በሚኒያፖሊስ ከመጀመሩም በላይ በስኬት መጠናቀቁን የዘሃበሻ አዘጋጆች ለማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል በላኩት መረጃ ገልጸዋል ። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ይልቃል ይህንንን የሰሜን አሚሪካ ጉⶋቸው የተደረገበት ዋነኛ ምክንያት ለመጭው ግንቦት ለሚካሄደው ስብሰባ የሚደረግ የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት ለማድረግ እና የፓርቲያቸውን ጥንካሬ በማሳየት እና በገው ፓርቲ የሚደርስባቸውን እንግልት እና እስር እንዲሆም ሞራላዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ተቋቁመው የደረሱበትን ደረጃ ሊገልጹ የሚችሉበት መድረክ ማዘጋጀታቸውን የዚህ ስብሰባ አዘጋጆች ጠቁመዋል ። ኢ/ር ይልቃል በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል፣ ምርጫው ውስጥ መቆየት ያለው ፋይዳ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አጠቃላይ ገፅታና እንቅስቃሴ ምን ይመስላል፣ በሚሉት ጥያቄዎች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ኮሚቴው ገልጿል፡፡
የፓርቲውን የሰላማዊ ትግል ስትራቴጂዎች በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ማስረዳትና በነዚህ ጉዳዮች እንዲሁም ባጠቃላይ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ዉይይት ማኪያሄድም የዝግጅቱ አንድ አካል መሆኑም በመግለጫው ተጠቅሷል።
Average Rating