በአዲስ አበባ ከተማ እና እንዲሁም በሌሎችም ክልል ከተሞች የወያኔ መንግስት ለሚቀጥለው ተመራጮችን በተለያዩ ክልሎች እና በአዲስ አበባ መስተዳድር ስሙ በውል በማይታወቅ የፖለቲካ ድርጅት ስም ተመራጮችን ሊያወዳድር እንደሆነ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል ፡; እንደምንጫችን ዘገባ ከሆነ የቤት ለቤት ምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ የወያኔን አውራውን ንብ እና ሌላም ተጨማሪ ፍላየር በማዘዋወር በመስጠት ላይ እና እኛን ካልመረጣችሁ በማለት ግፊት በማሳደር ላይ እንዳሉ ገልጸዋል። በተለይም ወጣት ፓርቲ የሆነው የሰማያዊ ፓርቲ ለወያኔ አስተዳድር ከፍተኛ ስጋት የጣለበት ከመሆኑም በላይ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትን እና ተደናቂነትን ማግኘታቸው ይበልጡኑ ለማጭበርበር እንዲመቻቸው የሚያስችላቸውን ዘዴ እንዲፈልጉ አስችⶀቸዋል ይላል ። በሌላም በኩል ደግሞ መንግስት ያባረራቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ስም ሌሎችን ሰዎችንም በራሱ ድርጅት ስም በማስገባት እነዚህን ምረጡ በማለት በወያኔ የምርጫ ኮታ ላይ አስገብⶆቸዋል ሲል ገልጾአል ።
ከአመት አመት የመሻሻልም ሆነ የስልጣኔ በር የማይከፈትላቸው ወያኔዎች ከማጭበርበር ውጭ እና ህዝብን በግፍ ከማሰቃየት እና ከመግደል የሃገር ሃብት ከመዝረፍ የማይቆጠቡ መሆናቸውን አውቀን የምንመርጣቸውን ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች በምናገኛቸው መንገዶች በመሄድ የፓርቲዎችን አርማ መጠየቅ አለብን በፓርቲዎቹ ቢሮውስጥም ቢሆን ከተመራጮቹ ጋር መነጋገር አለበን ፣ የምንመርጥበትን ዋነኛ አላማ እና አርማቸውን በጥንቃቄ በማወቅ መምረጥ ይገባናል ሲል አትⶆል ።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating