በአንቦ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረው ግርግር እና መንግስት የወሰደው ጥቃት አንደኛ አመትን አስመልክቶ የአንቦ ከተማ እና እና የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች እንዲሁም የከተማው ነዋሪዎች በከፍተኛ ውጥረት ላይ ሲሆኑ ፣መንግስት በከተማዋ ያሰማራቸው የፌደራል ፖሊሶች እና የዩንቨርሲቲው ተማሪዎች ከፍተኛ ፍጥጫ ላይ ቢሆኑም ከዛሬ ነገ ብጥብጥ እና ችግር ይፈጠራል ተብሎ ተፈርⶆል ። ሆኖም ግን በዚሁ ጉዳይ በተነሳ የአንቦ ከተማ የውሃና መብራት እና የስልክ አገልግሎት ካገኘች ከ፩፪ ቀናት በላይ እንዳስቆጠረች በስፍራው ተዘዋውራ የነበረችው የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ወይዘሪት ኢትዮጵያ ገልጻለች።
ወይዘሪት ኢትዮጵያ ያናገረቻቸው አንዳንድ ሰዎች ሲገልጹም ለስራ ከአዲስ አበባ የመጡ የግብረ ሰናይ ድርጅቶችም አገልግሎታቸውን ሳይፈጽሙ ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ በፍርሃት ምክንያት መመለሳቸው በጣም አሳሳቢ መሆኑን ጠቁመዋታል ። ሆኖም መንግስት ነጻነት ያልሰጠው ይሄው ህብረተሰብ በፍርሃት ድባብ ይዞት አፍኖት ያስቀመጠው ት0እግስቱ የፈነዳ እለት ችግሩ የተባባሰ ሊሆን ይችላል በማለት አስተያየቷን የማለዳ ታይምስ ዘጋቢዋ ጠቁማለች ።
ባለፈው አመት ቁጥራቸው በዛ ያለ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያውያኖች በመሞታቸው የመረረ ሃዘን የጠለቀባቸው እነዚሁ ተማሪዎች በዘር ጉዳይ እንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ መዳረጋቸው እና ከትግራ ልጆች ጋር ጥርስ ለጥርስ መናከሳቸው የነገውን ታሪክ ሊያበላሽ እና ሊያቆሽሸው ይችላል ሆኖም ግን ይቅር መባባልን ለምደን ሰላም ማውረዱ ተገቢ ይሆናል በማለት አንድ አዛውንት የገለጹ ሲሆን ለዚህ ሁሉ በደል ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግስት እና በዩኒቨርሲቲው ስር ያሰማራቸው ደህንነት ተብለው የተሰየሙት ተማሪዎች እና መምህራን ናቸው ሲሉ ጠቅልለዋል ። ማለዳ ታይምስ ።
Average Rating