www.maledatimes.com በጀርመን አላማው የወያኔን ስርአት ከኢትዮጵያ መንቀል የሆነ ታላቅ ህዝባዊ ውይይት:: - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጀርመን አላማው የወያኔን ስርአት ከኢትዮጵያ መንቀል የሆነ ታላቅ ህዝባዊ ውይይት::

By   /   May 7, 2015  /   Comments Off on በጀርመን አላማው የወያኔን ስርአት ከኢትዮጵያ መንቀል የሆነ ታላቅ ህዝባዊ ውይይት::

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 31 Second

በጀርመን አላማው ወያኔን ስርአት ከኢትዮጵያ የመንቀል የሆነ ታላቅ ህዝብአዊ ውይይት::

ባሳላፍነው ቅድሜ ሚያዚያ 24 2007 ዓም በጀርመን ፍራንክፈርት የኢትዮጵያን የውውይትና የትብብር መድረክ ስብሰባ ተካሄደ:: ስብሰባውን በጀርመን የኢትዮጵያዊያን የውውትና የትብብር መድረክ ኮሚቴ የተዘጋጀ ሲሆን በስብሰባው አቶ ኦባንግ ሜቶ ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ እና አቶ የሱፍ ያሲን የምስራቅ አፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካና ተንታኝና የቀድሞ የጦቢያ መጽህሄት አምደኛ ከታዳሚው ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊና ፖለቲካዊና ሰብአዊ ችግሮችና መፍትሄዎች ሰፋ ያለ ገለጻና ንግግር አድርገዏል::

አቶ የወንደሰን አናጋው የትብብሩ ዋና ጸሃፊ አጭር የእንኳን መጣችሁ ንግግር በማድረግ ዝርዝር የስብሰባውን መርሃግብር ለታዳሚው ገለጻ አድርገዏል:: በመቀጠልም የትብብሩ ሊቀመንበር አቶ ጌታሁን አሰፋ በሊቢያ በግፍ የተገደሉት 30 ንጹዋን ኢትዮጵያዊያንን ታዳሚው በአጭር የህሊና ጸሎት እንዲያስባቸው በማድረግ ውይይቱን በንግግር ከፍተዋል::

የምስራቅ አፍሪቃና የመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ ተንታኝና የቀድሞ የጦቢያ መጽሄት አምደኛ የሆኑት አቶ የሱፍ ያሲን ኢትዮጵያዊነትንና ስለ ኢትዮጵያዊነት ስለሚያወሳው መጽሃፋቸው አጭር ማብራሪያ በመስጠት ከታዳሚው የተለያዩ ጥያቄዎችን በመቀበል መልስ ሰጥተውበታል:: ሰፊና ጥልቅ የታሪክና የፖለቲካ እውቀታቸው ተሰብሳቢውን በይበልጥም ወጣቱን ያስደነቀ እንዲሁም ጠቃሚ ትምህርትን ያስጨበጠ ነበር:: በርግጥም እንደዚህ አይነቱ የውይይት መድረክ ለወጣቱ የታሪክና የፖለቲካ እውቀት መጎልበት ወሳኝ ሚና ይጫወታል::

በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ውጭ በሚገኙ ስደተኞች ላይ እየደረሰ ስለሚገኘው የሰብአዊ መብት ጥሰት በስሜታዊነትና ልባዊ ሃዘን በተሞላበት ሁኔታ የሰብአዊ መብት ተከራካሪው አቶ ኦባንግ ሜቶ ንግግር አድርገዋል:: በዚህም ንግግራቸው ታዳሚውን በእንባ በማራጨት ኢትዮጵያዊነት በዘርና በቋንቋ ብቻ ጠቦ የሚታይ እንዳልሆነ ይልቁንም በፍቅርና በመተሳሰብ እንዲሁም በአንድነት የሚገለጽ መሆኑን አስረድተዋል:: በወያኔ ጠባብ ዘርን ያተኮረ አፓርታይዳዊ የጭቆና አገዛዝ ምክንያት ዜጎች ለስደት መዳረጋችውን በመግለጽ ለዚህም በሊቢያ በየመን በደቡብ አፍሪቃ እንዲሁም በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ኢሰብአዊ ግፎችን ጠቅሰዋል:: በተጨማሪም በሊቢያ በአሸባሪው አይሲስ ለተሰዉት 30 ንጹህ ኢትዮጵያዊያን ሃዘኑን ለመግለጽ በወጣው የአዲስ አበባ ነዋሪ ላይ የወያኔ መንግስት የወሰደውን ጭካኔ የተሞላበት ድብደባና እስራት አሳፋሪ መሆኑን በመጠቆም ለኢትዮጵያ ነጻነት እንዲሁም ሰብአዊ መብት መከበር እርስ በራሳችን መወያየትና መመካከር የእርሳቸውና የድርጅታቸው እምነትን አላማ መሆኑን ገልጸዋል:: ከተሰብስቢው የተጠየቁትን የተለያዩ ጥያቄዎችንም በተገቢና አስተማሪ በሆነ ሁኔታ አብራርተው መልስ ሰጥተውባቸዋል::

ይህ የኢትዮጵያዊን የውይይትና የትብብር መድረክ ህዝብዊ ስብሰባ የአቋም መግለጫ በማውጣት በተሳካ ሁኔታ ተፈጽሟል

ለተጠናከረው ሪፖርትና ዘገባ

ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on May 7, 2015
  • By:
  • Last Modified: May 7, 2015 @ 10:54 am
  • Filed Under: Ethiopia

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar