www.maledatimes.com በስደት ለዜጎች መታረድ መገደል እንዲሁም ለሚደርስባቸው ስቃይ ተጠያቂው የወያኔ ነው !! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በስደት ለዜጎች መታረድ መገደል እንዲሁም ለሚደርስባቸው ስቃይ ተጠያቂው የወያኔ ነው !!

By   /   May 9, 2015  /   Comments Off on በስደት ለዜጎች መታረድ መገደል እንዲሁም ለሚደርስባቸው ስቃይ ተጠያቂው የወያኔ ነው !!

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 32 Second

ዳዊት ደምመላሽ ( ኖርዌይ )

ያለፈው ወር ኢትዬጵያውያኖች በሀዘን እርር ድብን ያልንበትና መቼም ቢሆን ከዕሊናችን የማይጠፋ በሰው ልጅ ክቡር ፍጡር ላይ ከሰው ልጅ የማይጠበቀወን ያውም ከአፍሪካ በደቡብ አፍሪካ ደርባን ላይ እጅግ አሰቃቂ ታሪክ ይቅር የማይለው ማንኛውንም የሰው ልጅ የሚያሳፍር የትኛውንም ጥቁር ሰው ደግሞ ወዴት ልደበቅ የሚያሰኝ ሰብዓዊ ዘር ጠል ዘመቻ በኢትዬጵያኖች ላይ ተፈፅሞባቸዋል አስፓልት ላይ ለውሃ ልክ ስራ በሚፈለጉ ድንጋዬች እራስ እራሳቸውን ተፈጭተዋል ኢትዬጵያውያን ወንድሞቻችን በቆመጥ እንደ እባብ እራስ እራሳቸውን ተቀጥቅጠዋል ደማቸው አስፋልት ላይ ፈስሳል ይህ አልበቃ ብሏቸው የኌልዬሽ ወደ ኌላ ከጐማ ጋር ተጠፍሮ ታስሮ በላያቸው ላይ ቤንዚን ተርከፍክፎ ተቃጥለዋል የሞቱት አስር ላልሞሉ ይችላሉ አብረናቸው በጐማ ቀለበት ውስጥ የተቃጠልነው ቢሊዎኖች ነን፣፣

በየእነሱ መቃጠል በእነሱ በድንጋይ መወገር አንጀታችን እርር ድብን ብሎ ቁስላችን ሳይድን ክቡር በሆነው የሰው ልጅ ላይ ተደርጐም ተሰምቶም የማይታወቅ ኢትዬጵያውያኖችን ብቻ ሳይሆን መላውን የዓለም ህዝብን ያስደነገጠ በዕለተ ዳግማትንሳኤው ሰቅጣጭ ዜና ከወደ ሊቢያ ሰማን ኢትዬጵያን ወንድሞቻችን እንደ በግ ሲታረዱና በጥይት አናታቸውን ደብድበው ሲገድሏቸውና የሜድትራንያን ባህር በደም እምባ ስትጥለቀለቅ ተመለከትን፣፣ለኢትዬጵያውያኖች ዳግማትንሳኤው የደስታ ሳይሆን የሀዘንና የለቅሶ ሆኖ ዋለ የዓለም የዜና አውታሮች እነ ቢቢሲ፣ሲኤኔን፣አልጀዚራ ቀኑን ሙሉ 30 ኢትዬጵያውያኖች አይሲ ኤስ መታረዳቸውንና በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን እየደጋጋገሙ ሲዘግቡት ዋሉ ማምሻው ላይ የቀድሞው ኢትቪ አሁን ኢቢኤስ ብሎ ስሙን ቀይሮ የመጣው ከሰዓት በስተቀር እውነትን ተናግሮ የማያውቀው የወያኔው የውሸት የሚዲያ ጣቢያ በሀሰት ዜና አንባቢዎቹና ተላላኪዎቹ በሊቢያ የሞቱት ወንድሞቻችንን ኢትዬጵያውያን ስለ መሆናቸው አላረጋገጥንም በማለት በሀዘን ላይ ሀዘን በመጨር ሳምንቱም ለኢትዬጵያውያኖች ሙሉ የሀዘን ሳምንት ሆነ ሰነበተ እውነት ወያኔ እነዚህ የምንመለከታቸው ኢትዬጵያውያኖች መሆናቸው ጠፍቶት ሳይሆን የዜጎች መታረድ መገደል ለእሱ ምንም ባለመሆኑ ነው ፣፣Xenophobia burns ethiopian citizen

ጅብ ከሄደ ውሻ ምን እንደሚባለው የማቾች ቤተሰቦች የልጆቻቸውን ሞት ሰምተው ሀዘናቸውን ከወዳጅ፣ከዘመድ፣ከጐረቤት ጋር ተቀምጠው እርማቸውን ካወጡ በኌላ ገቪው የህወሀት መንግስት ኢትዬጵያውያን መሆናቸውን አረጋግጫለው አለ አሁን ኢትዬጵያውያን መሆናቸውን አረጋግጫለው ያለው ቦታው ድረሰ በመሄድ ሳይሆን የማቾች ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ሲገደሉ በዓይናቸው አይተው ሀዘን ላይ ስለተቀመጡ ብቻ ነው ፣፣በዚህም ብቻ ያልበቃቸው የወያኔ የፈደራል ፖሊሶች ሀዘኑን ለመግለፅ ወደ አደባባይ የወጣን ህዝብ ሲደበዱቡ ሲፈነክቱ አካለ ጎዶሎ ሲያደርጉ ተመልክተናል እውነት ሀዘንን ለመግለፅ የወጣን ህዝብ መደብደብ ወይንስ ወገንን ያረደንና የገደለን ሄዶ ደምን መበቀል ወይንስ በስደት ላይ እየሞቱ እና የመንግስ ያለ እያሉ ያሉ ዜጎችን መታደግ በአሁኑ ሰዓት በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዬጵያውያን በየመን ሰንዓ ሰሚ መንግስት በማጣቸወ የሚሞቱበትን ቀናቶች እየጠበቁ፣፣ISIS

ህውሀት ወያኔ እስኪ ይህን መልስልኝ የነፃነት ታጋዩን አንዳርጋቸው ፅጌን አፍናችው ለመውሰድ የተጠቀማችሁበትን ባዶ አውሮፕላን ለምን በሞት አፋፍ ያሉ ኢትዬጵያውያኖችን ህይወት ለመታደግ አትጠቀማችሁበትም ነበር ?አንድ የነፃነት ታጋይን ለብቻው በአንድ አውሮፕላን አፍኖ ወስዶ በማሰቃያ ክፍል ውስጥ በማስገባት የጣር ድምፅ መስማት ወይስ የሞት ጣር እያሰሙ ያሉ ወገኖችን ህይወት መታደግ ?አንዲን አፍናችው ብትወስዱም ብዙዎችን አንዳርጋቸው ተክቷል በአላማውም ፀንተን እንኖራለን ፣፣

ኢትዬጵያዊ በአገሩ ሰርቶና ተከብሮ መኖርን ጠልቶ አይደለም ከጐረቤት ኬንያ እስከ ደቡብ አፍሪካ እስር ቤቶችን አጨናንቆ የሚገኘው ሴት እህቶቻችን አማራጭን በማጣት በአረብ ሀገራት ኑሮን ለማሸነፍ ብለው ደፉ ቀና ቢሉም በአሰሪዎቿቸውና በልጆቻቸው ይደፈራሉ፣ይገደላሉ፥ከኢምባሲ በር ላይ እንኩዋን የሚያስጥላቸው በማጣታቸው እየተወሰዱ ሲገደሉ ተመልክተናል ለዚህ ሁሉ ሞት የሚዳረጉት ኢትዬጵያ ውስጥ ባለው በአንድ ዘር የበላይነት የነገሰበት በመሆኑ፣የዜጎች መብት የማይከበርበት ሀገር በመሆኑ፥ጋዜጠኞችና ጦማርያነን በእየ እስር ቤቱ የሚሰቃዩባት ሀገር በመሆኑ፣የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው የሚታሰሩበት፣ሀገር በመሆኑ ነው ፣፣

ግራም ነፈሰ ቀኝም ነፈሰ ለዜጎች መሰደድና በስደት ላይ ለሚደርስባቸው ሞት ተጠያቂው እራሱ ወያኔ ነው !! ስለዚህ በዘር በሀይማኖት በጎሳ በፖለቲካ ያለንን አመለካከት ሳናሰፋ ልዩነትታችን በማጥበብና በማቀራረብ ይህን የበሰበሰ ስርዓት በማስወገድ በህዝቦች ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተች አዲሲቷን ኢትዬጵያ እንመስርት ፣፣

ኢትዬጵያ ለዘላለም

ትኑር !!

 

 

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on May 9, 2015
  • By:
  • Last Modified: May 9, 2015 @ 9:56 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar