www.maledatimes.com የማለዳ ወግ … የማፍር የምኮራባቸው ፣ ጥበበኞች … - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማለዳ ወግ … የማፍር የምኮራባቸው ፣ ጥበበኞች …

By   /   May 9, 2015  /   Comments Off on የማለዳ ወግ … የማፍር የምኮራባቸው ፣ ጥበበኞች …

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 59 Second

* “አልመች አለው ጎኔ !” ጃኪ
============ ===================

ጥበብ የማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ስሜት የሚገለጽባቸው ቀዳሚው እያዝናና የሚያስተምር ዘርፍ ቢሆንም አሁን አሁን ግን ያ እየሆነ አይታይም ። የማፍር የምኮራባቸው ፣ ጥበበኞች ጉዳይ  አሁን አሁን ያሳስበኝ ይዟል …እናም የጎልማሳው አቀንቃኝ  የጃኪ   “አልመች አለው ጎኔ !” ጣዕመ ዜማ ውስጥ ስሜቴን ቢነካካው ፣ የማፍር የምኮራባቸው ፣ ጥበበኞች …ብየ ጀመርኩት  !

የጥበብ ሰዎች በግል እንደ ተራ ዜጋ የፈቀዱትን ፖለቲካ አቋም  የመያዝ መብታቸውን የማከብር ቢሆንም ታዋቂነታቸውን ተጠቅመው ከእውነተኛ የህዝብ መብት ጥያቄና ስሜት ሳይሆን ለሆዳቸው ሲያድሩ ማስተዋል ስሜትን ይጎዳል ። በተለይም ደግሞ የጥበብ ሰዎች ለሆዳቸው አድረው ከገዥ አንባገነኖች ጋረ ወግነው የህዝብ ድምጽ ሳይሆን የፖለቲካ ፖርቲዎች ቱልቱላ ሲሆኒ ማየት ያማል።

ያለመታደል ሆኖ በእኛ ኢትዮጵያ ከጥቂት የጥበብ ሰዎች በስተቀር አብዛኛው የጥበብ ሰዎች ከህዝብ እውነት የራቁ  አዎዛጋቢ ሰብዕና ያላቸው እየሆኑ ነው ። የሀገሬውን መከራ ፣ ስቅየትና የኑሮ ውጣ ውረድ ገባ ብለው መግለጹ ቀርቶ ሲገፋና ሲበደል እንኳ አጋርህ ነህ የማይሉት አሳፋሪዎችም እየሆኑ ለመምጣታቸው ብዙ ያየነው በሊቢያ በሰሞነኛውን የISIS ጥቃትን ተከትሎ የታዘብነው አቋም ነው ። ሀገር ሲያዝን ፣ የሀገሬውን መከራ ፣ ስቅየትና የኑሮ ውጣ ውረድ ከፍቶ መጠን ሲለቅ ፣ ህዝብ ከአድማስ አድማስ ሲጨነቅ በሀዘን በመከራው ወቅት ትክክለኛውን የህዝብ ስሜት የተጋሩና የገለጹት ምንኛ የታደሉ ናቸው ? በአንጻሩ ጥበብ አጓጉል ክብርን ፣ ገንዘብ ለማግበስበሻነ ትና ለፖለቲካ ወገንተኝነት አድርገውትና አግድመው ለፖለቲካው አድልተው የህዘብን ጉዳት ያልተሰማቸው ፣  ድምጻቸውን ያላሰሙት ምንኛ ያልታደሉ ናቸው  ?

ብቻ ጥበብ የህዝብ ስሜት መገለጫ ጭምር ናትና የህዝብ ጥበበኛ መሆን መቻል መታደልም ጭምር ይመስለኛል። ይህ እውን ሲሆን ማየትም ደስ ይለኛል ፣ ደስ ይለናል …
“አልመች አለው ጎኔ !” ይለናል ጃኪ … የውስጥ ህመማችን በሚማርክ  የድምጽ ቅላጼው አልመች ፣ አልደላን ማለቱን  ሲገልጸው … ለማለዳ ወጌ መነሻ መድረሻ የሆነኝም ይህው ነጠላ ዜማ ነው ፣  እኔ ወድጀለታለሁ … !

አልመች አለው ጎኔ
============
እዳክራለሁ እኔ
እዳስሳለሁ እኔ ፣
ወጥቸም አልተሳካ ፣
በቤቴም ሆዳ አይሞላ ፣
ይሄ ሲሄድ ያ ይመጣል
ጊዜ ሽሮ ቃል ያነባል ፣
አልመች አለው ጎኔን  !

አንዱ ጊዜ አልፎ ጸና
ነገ እንደ ዛሬ ገና
ምድር ከሰማይ ርቃ
አንዱ ሲሄድ አንዱ ይመጣል
ጊዜ ሽሮ ቃል ያነባል ፣

እዚህም ሲያልቅ ወገኔ
ማየት ተሳነው አይኔ
በቁሙ ነፍሱን ሲያጣ
እንዴት ደራሽ እንጣ ?
አረ ጉድ ነው አቤት ቁጣ !
ሀሰት  እውነት  ሁኖ  እየኖረ
ስንቱ ኑሯል  እያማረረ

ተስፋው ፣ ሲጨልምበት
ነፍሱን ሰጠ ፣ ለስደት

አይነጋም ወይ? ያ ጨለማ
አለው በይን  አንች  እማማ !
አልመች አለው ጎኔን  !

ደርሶ የሞላ እለቱ
በዘመድ በጥረቱ
ተረሳ የትናንቱ
ከፍ ስላለ ቤቱ

ጉርሻ አምጣ
አለው ጣጣ
በዚህ ቁጣ
ለውጥ የት ይምጣ ?

ጣፋሽ  ስኳር ስትልስ
ኑረሃል አንተ ምላስ
ይበቃሃል ሀቁ ይውጣ
የላዩም አይቆጣ
ፍርድ የላይ ነው ምድር ከንቱ
ይበጀናል እንደ ጥንቱ

ሳቅ ሳቅ ሲለኝ
ዝም አንች አያፍርም
ስቅ ሲለኝ
ውሃ ዘግ የለም

በብዙ ሚሊዮን ቆጥሮናል
መስማማት አቅቶናል

ማን በቤቱ አርፎ ይተኛ
ሰው በሰው ቤት ሆኖ አድመኛ

አልመች አለው ጎኔን
ርቆ እንደሰማይ ከኔ
አልመች አለው ጎኔን …

****  ****** ******

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር  !

ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 22 ቀን 2007 ዓም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on May 9, 2015
  • By:
  • Last Modified: May 9, 2015 @ 10:14 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar