የሰሜን አሜሪካው የእግር ኳስ ጨዋታ ሊጀመር የቀረው ጥቂት ቀናቶች ቢሆንም በዚህ ወቅት ላይ ሙዚቃቸውን ያቀርባሉ ተብለው የሚጠበቁት ሙዚቀኞች በአሜሪካ አለመግባታቸው አሳሳቢ ሆኖአል ። ከእነዚህም ውስጥ ጎሳዬ ተስፋዬ እና ቴዲ አፍሮ ይገኙበታል ። ለእግርኳስ ጨዋታው ወቅት ይደረጋል ትብሎ የሚታሰበው የሙዚቃ ኮንሰርት በእነቴዲ አፍሮ በኩል ላይከናውን ይችላል ይህ በእንዲህ እንዳለም የጃኪ ጎሲ ጉዳይም ቢሆን ተያያዥነት ያለው ሲሆን ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄድ የደርሶ መልስ ትኬት ቆርጦ ካልሄደ አስቸጋሪ የሆነ ኪሳራ ውስጥ ፌደሬሽኑ ሊወድቅ ይችላል ተብሎ ይገመታል። ምክንያቱም በአሁን ሰአት ላይ የአሜሪካ ኤምባሲ የዳታ ሲስተም ከተበላሸ ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘ ሲሆን በየቀኑ ከ50.000 በላይ የአለም ህዝቦች ያገኙት የነበረው የቪስ ቅበላ አሰራር በጊዜው በመቋረጡ ምክንያት ነው።ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ እስከ ጁላይ 7 2015 አመተ ምህረት የዳታ ሲስተሙ ሊስተካከል እንደማይችል የስቴት ዲፓርትመንት ያሳወቀ ሲሆን ቪሳ ላልተሰጣቸው እና እስካሁን ድረስ ቪዛ ላመለከቱ ሁሉ በትህትና እንዲጠብቁ አሳስቦአል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቀድሞ ይመጡልኛል ብሎ በማስታወቂያ ደረጃ ሲያስተዋውቃቸው የነበሩት ሙዚቀኞች ለጊዜው እንደማይደርሱለት ያላሳወቀው የስፖርት ፌደሬሽኑ ችግሩን በቸልተኝነት በማየት እና የማን አለብኝነት መንገድ በመመልከቱ ይመስላል ሲሉ ማለዳ ታይምስ ካነጋገራቸው ሁለት የችካጎ እግርኳስ ተጨዋቾች የሆኑ ሁለት ግለሰቦች ገልጸዋል።
ከዚህ በፊት እንደተለመደው ከሆነ ቴዲ አፍሮ በመጨረሻ ደረጃ ላይ ቪዛ ለማስመታት እንደሚሯሯጥ የታወቀ ቢሆንም በአሁን ሰአት ላይ ግን በአውሮፓ ቱ ላይ የሚገኝ ሆኖ ሳለ ግን የአሜሪካውን ቪዛ እጁ ላይ አለማስገባቱ አሳሳቢ ሆኖአል በሌላም በኩል የጎሳዬ ተስፋዬ ለእረጅም ጊዜ በሃገርቤት መቀመጡ ለእንደዚህ አይነት ችግር ተጋላጭ ቢሆንም እና መረጃውን በበቂ ሁኔታ መከታተል ባይችልም የፌደሬሽኑ ሃላፊዎች ጉዳዩን አስጨርሰው የመላክ ከፍተኛ ሃላፊነት ነበረባቸው ሲሉም አክለው ጠቁመዋል ።
Average Rating