www.maledatimes.com በሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌደሬሽን ያዘጋጀው ልዩ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ በሄኖክ አለማየሁ እና ዘላለም ገብሬ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌደሬሽን ያዘጋጀው ልዩ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ በሄኖክ አለማየሁ እና ዘላለም ገብሬ

By   /   June 29, 2015  /   Comments Off on በሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌደሬሽን ያዘጋጀው ልዩ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ ተከፈተ በሄኖክ አለማየሁ እና ዘላለም ገብሬ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 2 Second

በሜሪ ላንድ ቨርጂኒያ እና ዲሲ ይከናወናል ተብሎ ለረጅም ጊዜ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሰሜን አሜሪካ እግርኳስ ጨዋታ የመክፈቻ ዝግጅት በዛሬው እለት በደማቅ ሁኔታ ተከፍቶአል ። ይሄው በሰሜን አሜሪካ በየዓመቱ የሚደረገው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ በሜሪላንድ በርድ ስታዲየም በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በድምቀት ተከበረ:: ከአሜሪካ እና ከካናዳ የመጡ ከ30 በላይ ቡድኖች በስታዲየሙ በመገኘት በዚሁ በመክፈቻ ዝግጅት ላይ ራሳቸውን አስተዋውቀዋል:: በዚህ ዝግጅት ላይ ለእንግሊዙ አርሰናል ክለብ እየተጫወተ የሚገኘው ጌድዮን ዘላለም የተገኘ ሲሆን ከሕዝቡም ደመቅ ያለ አድናቆት ተችሮታል:: በዚሁ የመክፈቻ ዝግጅት የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ተስፋዬ ባሰሙት ንግግር የዘንድሮው ዝግጅት በርካታ ሕዝብ በመገኘት በመከፈቱ መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይ ቀናት ደማቅ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል:: ethiopia soccer 1እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ ረቡዕ ምሽት የብሄራዊ ትያትር 60ኛ ዓመት በዓል በታሪካዊ ሁኔታ ይከበራል; የፊታችን ሐሙስ አርብና ቅዳሜም ከእግር ኳሱ በተጨማሪ ታላላቅ አርቲስቶች እንደ እነ ጠለላ ከበደ አያሌው መስፍን ሌሎችም በስልሳዎቹ አካባቢ የነበሩት በሙሉ በስራዎቻቸው የሚዘከሩ እን በክብር የሚገኙ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን በህይወት የሌሉትንም ሆነ ታላላቅ ስራዎቻቸውን ጥልውልን ያለፉትም በክብር እንደሚዘከሩ ጠቁመዋል ከዚያም ባሽገር በወቅቱ አሉ የሚባሉት ታላላቅ አርቲስቶ  ትልልቅ የሙዚቃ ኮንሰርቶች እንደሚያዘጋጁና እንደሚያቀርቡ የጠቆሙ ሲሆን  ሕዝቡም በነዚህ ስፍራዎች እየተገኘ እንዲዝናና ጥሪያቸውን አቅርበዋል:: የዘንድሮው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን 32ኛ ዓመት በዓል መታሰቢያነቱ በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ ላለቁት ኢትዮጵያን መታሰቢያ እንደሆነ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዘዋል:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተወካይ ባሰሙት ንግግር የሊቢያውን ሰቆቃ አስታውሰው “እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አይረሳትም” ብለዋል:: ፕረዚዳንት አቶ ጌታቸው ለማለዳ ታይምስ እንደገለጹት ከሆነ በዘንድሮው አመት የቨርጂኒያ ቡድን ለ3ኛ ጊዜ ካሸነፈ ይህ ዝግጅት በ32 አመቱ ለየት የሚያደርገው ደማቅ ፕሮግራም ይሆናል ብለዋል ። በሌላም በኩል በዚሁ የስፖርት ፌደሬሽን ባለው የስልጣን ተዋረድ ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ በዘንድሮው አመት ምርጫ ተከናውኖ 61 ቦርድ አባላት ያሉት ሲሆን በ32 ቡድኖች መካከል 9 የአመራር አባላት የጸሃፊውን እና የፕረዚዳንቱንም ቦታጨምሮ የአሉ እና እያገለገሉ የሚገኝ ሲሆን በየሁለት አመቱ ምርጫ የሚያከናውኑ ሲሆን በዚህ አመትም ለሁለተኛ ጊዜ ሙሉው አመራር በቦታው ላይ እንዲቆይ የተደረገ ሲሆን በሚቀጥለው ጊዜም ከዚህ የተሻለ የአመራር ስራ ይዞ ሊቀርብ እንደሚችል እና ለተከታዮቹ የስልጣን ቦታ ላይ ተተኪዎች የተሻለ መረብ ዘርግቶ ሊያልፍ እንደሚችል ጠቁመዋል ።

ከጋዜጠኞች በተለያዩ ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል ለምን በድጋሚ ወደ ሜሪላን ሊመጣ ቻለ ለምን እንደ እነ አትላንታ ባሉት አገሮች ላይ ሊዘጋጅ አልቻለም የሚል ጥያቄም የሰፈረላቸው የነበረ ሲሆን እንደ አመራሩ መልስ ከሆነ የአትላንታም ሆነ የሌሎች ክልል ከተሞች በቂ የሆነ ተፎካካሪ አልነበራቸውም ስለዚህ ተሽሎ የተገኝው ሜሪላንድ ነበር ከዚያም ባሻገር የመጫወቻ ሜዳቸውም በሰፊው የሰጠ እና እንግዶቻችንን ለማስተናገድ በቂ ቦታ እንዳለን የምናቅበት ሲሆን ከዛሬ ሶስት አመት በፊት የሜሪላንድ ህዝብ ተቀይሞንም ስለነበር እነርሱም ለማስደሰት እንደገና በቦርዱ ምርጫ በከፍተኛ ተቀባይነት በማግኘቱ ወደ መሪላንድ ልንመለስ ችለናል ብለዋል።

ከባለፈው ስህተታችን ተምረን በስታዲየሙ ዙሪያ የሚገኙትን መግቢያ በሮች እንዲከፈቱ አድርገና ፣በዋችንግተን ዲሲ መገኘቱ እራሱ ልዩ የሚያደርገው ይሄው ዝግጅት እንደዛሬው የህዝብ ብዛት ሰሞኑን የአየር ንብረቱ ጥሩ ከሆነ ከዚህ በላይ እጥፍ የሆነ ህዝብ እንጠብቃልን አሁን እንኩዋን ደህና መጣችሁ የሚለውን መልእክታችንን በእናንተ ዘንድ በድጋሚ ልናደርስ እነዳለን ሲሉ አክለዋል ።

በዚህ አመት በተደረጉት ቅድመ ዝግጅቶች ላይ እንዴት ነው ማወቅ የሚቻለው የሚል ጥያቄም ቀርቦላቸው በተለያዩ ድህረ ገጾች ላይ በመግባት እንዲሁም በፈደሬሽኑ መገናኛ መድረክ ድህረ ገጽ በመግባት መመለከት የሚችሉ መሆኑንም ተናግረዋል ፣የዘንድሮው አመጥ ጠንካራ ሃይል የጠየቀን ስራ ቢኢሆንም በስኬት እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል፡

የመድሃኔዓለም ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ተወካይ ቄስ በሪሁን መኮንን በሊቢያው ሰቆቃ ሊያስተምረን ስለሚገባ ነገር ተናግረዋል:: የሁሉም የሃይማኖት መሪዎች ልዩነት ሳይበግራቸው በአንድነት በመቆም ሊሰሩ እንደሚገባ ይህ ሃዘን አስተምሮናል ብለዋል:: በሰሜን አሜሪካ የሙስሊም ኮሙዩኒቲ ተወካይ ሼክ ሱለይማን ነስረዲን በበኩላቸው በሊቢያ የተገደሉት ወገኖች የተገደሉት ክርስቲያን በመሆናቸው ሳይሆን ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ነው ሲሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሃይማኖቶች መከባበር ለመጠቆም ሞክረዋል:: በዛሬው የመክፈቻ ጨዋታ የላስቬጋሱ አበበ ቢቂላ የሲያትሉን ዳሸን 2ለ0 – ዴንቨር የሚኒሶታውን ኒያላ 4ለ0 – ቺካጎ  ፊላደልፊያን 2ለ1 – ኦሃዮ ቦስተንን 4ለ1 ሲያሸንፉ የሎሳንጀለሱ ዳሎል የዲሲው ዩናይትድ 1ለ1 እንዲሁም የሎሳንጀለሱ ስታርስ ከሜሪላንዱ ከቅዱስ ሚካኤል ጋር 1ለ1 ተለያይተዋል:: በሌላ በኩል የፌዴሬሽኑ ዋና ጸሃፊ አቶ ያሬድ ነጋሽ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት በዛሬው የመክፈቻ ዝግጅት መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይ ቀናት በርካታ ሰው እንደሚገኝ ያላቸውን ግምት ገልጸዋል:: በሃይማኖት አባቶቹ መል ዕክት መደሰታቸውንም ገልጸዋል:: በድምቀት የተከፈተው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫልን በስፍራው የሚገኙት የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች ከማለዳ ታይምስ ጋር በመተባበር በየቀኑ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ይዘግቡላችኋል:: –

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on June 29, 2015
  • By:
  • Last Modified: June 29, 2015 @ 6:40 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar