በዋሽንግተን ዲሲ:
በዋሽንግተን ዲሲ: ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ የነበረን ቆይታ ለሳምንታት የዘለቀ የነበረ ሲሆን የዘሃበሻው ሄኖክ አለማየሁ ፣ ቴዎድሮስ መይሳው እና ማለዳ ታይምስ ውሎና አዳራቸው የተለያዩ የገበያ ማእከላትን አሰሳ በማድረግ ስራቸውን እና የእንግዳ አቀባበላቸውን መገምገም ትልቁ ሰራቸው ሆኖ ከርሞአል ታዲያም የሶስቱንም ስቴቶች ምግቤቶች አንዳንድ ለመምረጥ ሞከርን እና ከሶሰቱም የመረጥናቸውን ጥቂቶቹን ስራቸውን ለማንሳት ወደድን ፣ከነዚህም መካከል ድንቅነሽ ከሜሪላንድ ፣ አዲስ አበባ ከሜሪላንድ ፣ ቤቴ ከሜሪላንድ ፣ባላገሩ ከቨርጂኒያ እና ዱከም ከዲሲ ፣ዕንዲሁም ካልዲስ ኮፊ ሾፕ እና ሂት ዘ ስፓት የተሰኙትንም የቡና መሸጫወችንም ለመዳሰስ እንሞክራለን እነዚህም ከበቂ በላይ መስለው ስለታዩን በእነዚህ ድርጅቶች ላይ ያለነን ልምድ ለእናንተ አንባበያኖች ልናካፍላችሁ ወደናል!
ከየትኛው ምግቤት መጀመር ፈታኝ ቢሆንም ዛሬ ግን መልካም መስተንግዶን መጀመሩ ጥሩ ከመሆኑም በላይ የምንሰጣቸውን የምግብ ቤቶች አስተያየት ወይንም (review ) ወደፊት ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ ለሚጉዋዙ ተጉዋዞች ሊጠቅም ይችላል ብለን እንገምታለን ።
የመጀመሪያው ቤቴ የተሰኘው ሪስቶራንት ሲሆን የሚገኘው 811 Roeder Rd, Silver Spring, MD 20910
(301) 588-2225 ሲሆን በአንድ ሙሉ ቤተሰብ አባላት የመስተንግዶ ስራ እቀረበ ቀልጣፋ እና ብቁ ምግቤት መሆኑን ለመረዳት ችለናል ። በተለይም ቁርስ እና ምሳ ሰአት ብቅ ብለው ለሚመገቡ ክቡር ደንበኞቻቸው ከባለቤቶቹ ጀምሮ እስከ አስተናጋጅ ሰርተኞቹ ጭምር ቀልጣፋ እና አስደሳች የሆነ አቀባበል በማድረግ ከምግባቸው ጥራት እና ብቃት ጋር ተደማምሮ ቀልጣፋው ስራቸው ከተተመነው ጥሩ ዋጋቸው ጋር በማስደሰት ዕግር ኳስ ወደ ሜሪላንድ የተጓዘውን እንግዳ ሲያስተናግዱ ታይተዋል።
ይህ አስደናቂው መስተንግዶአቸው ደጋግመን እንድንሄድ እና የእንሱን ምግብ ብቻም አይደለም አጠቃላይ አቅርቦቶቻቸውን እና ግልጋሎቶቻቸውን በእርካታ ልንታደም በቅተናል :እኛም ቤቴ ምግቤትን በርቱ ከማለት ያለፈ ነገር ለመግለጽ ጊዜውም አልነበረንም ።
አስከትለን ወደ ዲሲ ዱከም ሪቶራንት ጎራ እንበል እና ምን አይነት መስተንግዶ እንደጠበቀን እንገራችሁ ፣ አድራሻው 1114-1118 U St NW Washington, DC (202) 667-8735 ዱከም በተጉዋዝንበት ሰአት አስተናጋጆች ለማስተናገድ አይደለም ሰላም ለማለት ጊዜ የማይሰጡ ሆነው ነበር ያገኘናቸው ቀጥሎም የምግብ ትእዛዙ ከቀረበ በሁዋላ የሚወስደው ጊዜ እና የምግቡ ጣእም የትየለሌ ነበር ፣ታዲያ እንደዚያም ሆኖ ግን ለምን ዋሽንግተን ዲሲ ድረስ መጣን ብሎ ሊያስቆጭዎት ይችል ይሆናል ፣በተለይም ዱከም ሪስቶራንት ከአስር አመታት በፊት ጀምሮ በኢትዮጵያን ቴሌቪዥን ጭምር በማስታወቂያ ጆሮአችንን ሲያደነቁረን ስለነበር በልባችን ውስጥ አንድ የቀረ ነገር ያለ ይመስለናል ይሄውም የኢትዮጵያውነት ዜማን የያዘውን ምርጥ ምግብ ፣ምንም ያልተበረዘበት እውነተኛውን ቅምሻ ጣእም (ቴስት) ታዲያ እዚህ ምግብ ቤት ግን የሚቀርብልዎ እንጀራ ሁለት አይነት ነው አንደኛው ከኢትዮጵያ የሚመጣው እንጀራ ሲሆን ገና ከእጅዎ ጣቶች ላይ ሲያርፍ እየተሸራረፈ የሚረግፍ ሢሆን ምን ያህል በበረዶ ማስቀመጫ ውስጥ እነደተቀመጠ ለማወቅም ያዳግታል ፣
ሁለተኛው ደግሞ እዚያው የሚጋገረው ሲሆን ይህም እንጀራ ለጨጉዋራ ውህደት አስቸጋሪ ሆኖ ለእረጅም ሰአታት ሳይፈጭ እና የጨጓራዎን አካል ይዞ ተቋጥሮ ይቀራል ታዲያ ይህ አይነቱ እንጀራ በየትኛውም ትስቴት የሚገኝ መሆኑ አዲስ ባይሆን ከዚያ ለየት የሚያደርገው ግን 14 አይነት በየ አይነቱ እና 16 አይነት በየ አይነቱ ተብሎ የሚቀርብልዎት ሁለት አይነት የጾም ምግብ ሲኖር ከአይነቶቹ መካከል እንደ ቁጥር የሚገባው ሽሮ በዘይት ታሽቶ የሚቀርበው የሽሮ ዱቄት ነው ሌላው ደግሞ ነጭ አተር ሲሆን ከጣእምነት ማጣቱ የተነሳ የተቀቀለ ንፍሮ አይነት ጣእም ይዞልዎት ይቀርባል ፣ከአስራ አራቱም የምግብ አይነቶች ውስጥ አንድ ልሙጥ ሽሮ ብትቀርብ እና ምስር ወጥ ቢቀርብ የተሻለ ጣእም ያላቸው ሲሆኑ ሌሎቹ ግን ለስያሜ እና ገንዘብን በቀላሉ ለማግኘት የሚቻልባቸው ዘዴዎች የተፈጠሩ ይመስላሉ እናም ያዘዝነውን ምግብ በደንብ እንኳን ሳናቀላጥፍ ጉዞአችንን ወደ አረፍንበት ሆቴል ለማምራት ተገደናል ሆኖም እንደ እኛ አስተያየት ከእንደነዚህ አይነት ምግቦች ውስጥ ምንት ትርጉም የማይሰጡ እና ከምግብ የማይቆጠሩ ነገሮችን ከቁጥር አስገብቶ የምግብ አይነት እና ምግቤት ለማለት ቢከብድም ስም እና ዝናን ይዘው ከበስተጀርባቸው በስራቸው ጣር ውስጥ ያሉ ብዙ ምግብ ቤቶች ሞልተዋል እና ጠንቀቅ ማለት ይበጃል ።
በተመሳሳይ ሁኔታ ድንቅነሽ ምግብ ቤት ከሜሪላንድ 8301 Georgia Ave, Silver Spring, MD 20910
(301) 589-6700 ባለቤት አልባ ምግብ ቤት ፣ይህንን ልንልበት የቻልንበት ምክንያት ፣ባለቤት ደንበኞቹን እንደ ራሱ ክብር ምክበር የማይችል ከሆነ እና ማንነታቸውን ሳያውቅ የሚዘረጥጥ ሲሆን ባለቤት አልባነቱን ያሳያል ፣ታዲያ የዚህ ቤት ባለቤት ወይንም አስተዳዳሪ የሆነችው ግለሰብ በማናቸውም ሰአት የመጡትን ደንበኞቹዋን በስድብ ስትወርፍ ማየቱ አሳሳቢ ከመሆኑም በላይ ለሌሎች የሚጋብዝ ሆኖ አልታየንም ፣በሃገራችን እንደሚባለው ደንበኛ ንጉስ ነው ይባላል ፣በውጭው አለም እንደዚያው ደንበኛ ከማንኛውም በላይ ክቡር ነው ሆኖም እንደ አለመታደል ሆኖ የዚህ ቤት አስተናጋጅ የሆነችው ወጣት (በስሟ እሙዬ የምትባለው) ደንበኞችን በጋጠወጥ ቃላት ስትናገር ማየቱ የመስትንግዶአቸውን መጉዋደል በሰፊው ይታያል ፣ይህም ብቻም አይደለም ፣ለሚያቀርቡትም ምግብ ወይንም እንጀራ እንደ ቼኮላት የጠቆረ ሲሆን ከየትኛው ልለም የፈለቀ የጤፍ ምርት እንደአመጡ ባይታወቅም ምንም አይነት ስሜንት የማይሰጥ ምግብ ማቅረባቸው ይበልጡኑ ከማበሳጨትም አልፎ ዳግም ዞሮ ማየት እንደማያስፈልግ ያሳያል።
አዲስ አበባ ሪስቶራንት ፣ይህንን ምግቤት ብዙ መዘርዘር የምያስፈልገን ያለ አይመስለኝም በጥቂቱ ከ5 የማይበልጡ የምግብ ዝርዝሮች ይዘውልዎት የሚቀርቡ በአንድ ነጭ ወረቀት የሚቀርብልዎት የምግብ ዝርዝር በቀልጣፋ አቅርቦት የሚቀርብልዎት ይመስልዎት ይሆናል ሆኖም ግን ይህ ስራቸው የተዋረድ ሆኖ በሜኑው ላይ የቀረቡትንም አምስት አይነቶች ምግብ ከምሽቱ 9፡00 ታዞ የቀረበልን ከለሊቱ 12፡00 ሰአት ነበር ፣ይህንን ሰአት በማጋነን ያቀረብነው ሳይሆን ከአስር አመታት በላይ የተለያየን ጉዋደኛሞች የስራ ባልደረቦች (ጋዜጠኞች) ተገናኝተን በደስታ ፍካት ስለ ቀድሞው የህይዎት እና የኑሮ ቆይታችን ስናወራ ያዘዝነውን ምግብ እረስተነው በስተመጨረሻ ትእዛዙን በማስታወስ ስንጠይቅ ከሌላ ምግብ ቤት ታዞ እንደሚመጣ አይነት ስሜት ሼፎቻችን ቢዚ ናቸው የሚል ምላሽ ካስተናግጁዋ ቢሰጠንም ከመሃከላችን አንዷ የግሩፕችን አባል ሆነችው (ጽዮን ግርማ) እንዴት እንደዚህ ይደረጋል በማለት ቆጣ ባለ ስሜት ብትናገርም ሰሚ ያጣ ጆሮ ሆኖብን ፣እንዲቀርብልን በጽሁፍ ያዘዝነው ምግብ ከሶስት ሰአታት ቆይታ በሁዋላ በመቅረቡ ፣የመስተንግዶ አልባ ቤት ብለን ሰይመነዋል እና በጭራሹ ሊሄዱበት የማይገባ ምግቤት እንደሆነ ሳንገልጽ አናልፍም አድርሻውም 8233 Fenton St, Silver Spring, MD 20910
(301) 589-1400
በመጨረሻም ካልዲስ ኮፊ ሾፕ እና ሂት ዘ ስፓት እንዲሁም አቦል ቡናን እንጨምር እና ሌሎቹንም ምግብ ቤቶችን አመስግነን እንለያችሁ
እነዚህ የቡና መሸጫ ቤቶች በጣም ደስ የሚል እና የእንኩዋን ደህና መጣችሁ መልእክታቸው የሃገርቤት የበአል ትዝታን ይጭራል ፣በየ አውዳመቱ ሰው በየቤቱ ተጠራርቶ እንኩዋን ደህና መጣችሁ የሚባባልበት ስሜት ድባቡን በእነዚህ ቤቶች ያገኙታል ፣በእርግጥ በዲሲም ሆነ ሜሪ ላንድ አለበለዚያም ቨርጂኒያ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶች በጣም አናሳ ሆነው ብናገኛቸውም ስራቸውም ላቅ ያሉ ሆነው ያገኘናቸው አሉ ፣ከእነዚህም መካከል ከላይ የጠቀስናቸው የቡና መሸጫ ቤቶችም ሆኑ እንደ እነ ቄራ ስጋ ቤት ፣ባቲ፣አባይ፣ሌሎችም ምርጥ ምግብ ቤቶች ከባለቤቶቹ መልካም ስነምግባር እና የአስተናጋጆች ትህትናና እና ድካም ይብልጥ እደጉ ተመንደጉ የሚያሰኛችሁ ብዙ ነገር አለ እና በርቱ ስንል ፣በተለይም ለ ሂት ዘ ስፖት ባለቤት አቶ ቢኒያም ፣ለመልካም ሁኔታህ፣ ከደስተኛው ፈገግታህ እና አክብሮታዊ ጨዋታህ ጋር ላደረካቸው መልካም ነገሮች እና ቀና መስተንዶ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን 2313 Georgia Ave Washington DC …. ላንጋኖ ምግብ ቤት የሚገኙትንም አስተናጋጆች ከእነ ምግብ ቤቱ ባለቤቶች ምስጋናችን እና የመልካም ስነ ምግባር ባለቤቶች ስለመሆናቸው ከልብ ለማመስገን ወደድን በስተመጨረሻም አንድ ነገር ለማለት ወደድን ፣ ለወዳጃችን >>>>>» ስምህን መጥቀስ ስለማንፈልግ ብቻ ፒስ ላውን እንበለው እና
በሌላም መልኩ ደግሞ ፒስ ላውንጅ ደግሞ በሰኞ ምድር ረቡእ ብሎ የተጨማሪ ስፔሻል ዋጋ ተብሎ በእያንዳንዱ መቀመጫ ወንበር $18 እና ባልተጠቀሙት መጠጥ ወይንም ሌሎች አቅርቦቶች ላይ የዋጋ ተመን እና የአቅርቦት ጭማሪ በሪሲቶች ላይ ጨምሮ ማቅረብ እተደጋጋሚ በማየታችን በጣም አሳፋሪ አሰራር ሆኖ አይተነዋል ፣በሌላም መልኩ ደግሞ የባለቤቱ ፍቅረኛ ነች የተባለችውን ወጣት በመጠጥ ባልኮኒው ውስጥ ተቀምጣ ግማሽ ጠርሙስ ግሬጉስ ስትታዘዝ እኩል በእኩል ውሃ ቀላቅሎ ማቅረብ ከስተመርን እንደመናቅ እና በቀላሉ ዘዴ ገንዘብን እንደመዝረፍ ይቆጠባል እና ይህንን ነገር ልብ ሊባልለት ይገባል ብለን ለባለቤቱ ጭምር ነግርነን መውጣታችን የእኛ የብእር ቱርፋታችን ነው ።
መልካም ሰንበት ።
Average Rating