በትላንትናው እለት የዞን ዘጠኝ ጦማርያንን እና ጋዤጠኞችን መለቀቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል በዛሬው እለት ማለዳ ደግሞ ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ እና ጦማሪት ማሂ ፋንትሽ (ማህሌት ፋንታሁን) ከቤተሰቦቻቸው መቀላቀላቸውን ተነገረ። ባራክ ኦባማ ወደ እትዮጵያ የመገባታቸውን ሁኔታ ተከትሎ ፣ቅድሚያ ጉዞአቸውን ከማከናወናቸው በፊት እነዚህን ንጹህንን ዜጎች እንዲፈቱ ያደረጉት ጫና ነው የሚል መላምት ሳይደርሱ አይቀርም የሚለው ሃስብ በሰፊት እየተነገረ ነው ።
የተለያዩ ድህረ ገጽ የፕረዚዳንቱን ጉዞ አስመልክቶ አብዛኞቹ ሲቃወሙት እንደነበር እና በተለይም በዋሽንግተን ዲሲ የዲሲ ግብረ ሃል የተሰኙት የፖለቲካ ቃዋሚዎች ሰላማዊ ሰልፍ ከመውጣት አልፈው ጋዜጠኛ ሄኖክ ሰማእግዜርን እስከማዋከብ እና መደብደብ ድረስ ደርሰው ነበር።
በማንኛውም አለም የአንድን ሰው ሃሳብ የመግለጽ እና የማንጸባረቅ መብቱ የእራሱ የግለሰቡ መብት መሆኑን ያልገባቸው የገዢው ፓርቲ አመራር አካላት እና የተቃዋሚ አባላቶች በሙሉ በቅድሚያ ሊያንጸባርቁት የሚገባው ነገር ቢኖር ግለሰብ የራሱን ፍላጎት ማንጸባረቅ እንደሚችል እና የእኔን ሃሳብ ለምን አልተቀተልክም ተብሎ ተቃውሞ የሚቀርብበት እና ጥላቻ የሚዘንብበትን መንገድ መከተል አላስፈላጊ መሆኑን ሊያውቁት ይገባል ፣በሌላም በኩል በመንግስት እጅ ስር የሚተዳደረው የኢትዮጵያቴሌቪዥን እና በድርጅቱ ስር የሚተድደሩት መገናኛ ብዙ ሃኖችም ሆኑ በግንቦት ሰባት ስር የሚተዳደርው መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም በታላቁ ጥላሁን ገሰሰ ስም በአንድ ግለሰብ የተቋቋመው ቲጂቲቪ ፤ የሰዎችን ስብእና የሚገፈው በጣም በከፍተኛ ደረጃ ከመሆኑም ባሻገር፤ የሚሰሩት ስራ ናሬሽን የበዛበት እን የጋዜጠኝነትን ስነ ምግባር ሳይከተሉ የራሳቸውን ስሜት ብቻ የሚያንጸባርቁ ሲሆን በእነዚህ መገናኛ ብዙሃኖች ሌሎች ንጹሃን ሚዲያዎችም አብረው እንደሚጨፈለቁ ግልጽ እና ተጠያቂነትን ያሳድራል።
ለዚህም ምክንያት በባለፈው ሳምንት ከጋዜጠኞች ጋር በተደረገው ስብሰባ ላይ የቀረበው ትችት እና ወቀሳ እንደምሳሌ ልንጠቅሰው የምንችል መሆኑን ሳንጠቁም አናልፍም ። ሆኖም በተገቢው መልኩ የጋዜጠኝነት ስነምግባርን እና ደንብን የህዝብን ህልና እና ነጻ አመለካከት ይዞ የሚቀርብበት ቢሆን ሃገራዊ እድገታችንም ሆነ የአመለካከታችን ነጸብራቅ እንዲሁም የፖለቲካዊ ልዩነታችንን ማጥበብ እና ማስፋት የምንችልበት ሊሆን የሚገባው ሊሆን ይችል ነበር ፣ እንደነዚህ አየት ሚዲያዎችም አሉን ብለእን እርስ በእራሳችን መነጋገር ሳንችል ቀርተን ችግሮቻችችንን መፍታት ካልቻልን እና መቀራረባችንን ካላሰፋን የበለጠ የፖለቲከኞች ምርኩዝ ሆነን ልክ እንደ ምርጫ 97 በትካሻችን ላይ ተንጠልጥለው ሲያልፉ እና ጋዜጠኞችን ወደ መቀመቅ ሲያስወርዱ ሊታዩ እንደሚገባ ማስተዋል ተገቢ ነው ።
ለዚህም ይመስላል የወያኔ መንግስት በተለያዩ ጋዜጠኞች ላይ ማለትም ከፍተኛ ጽሁፍ በመጻፍ የህዝብን ትኩረት በሚስቡ ወጣቶች እና ብልህ ብእርተኞች ላይ የእጁን አለጋ ሊያሳርፍባቸው የበቃው እየበቃም ያለው። እንደ እነ እስክንድር ነጋ አይነትቹን ታላቅ ብእርተኞችን በእስር ላይ ማዋሉ አሳዛኝ ከመሆኑም በላይ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አመለካከትም ሆነ እውቀት ከምናቸውም የወያኔ ባለስልጣን ተብዬዎች በላይ የጠለቀ እና በትክክለኛ መልኩ ባለው እውቀት የመስራት እድሉ ቢሰጠው ብዙ ነገሮችን መለወጥ የሚችል ድንቅ ሰው መሆኑን ያልገባቸው ወይኔዎች ለ 4 ዓመታት በእስር ላይ አግተውት ይገኛሉ ። በዛሬው እለት የተለቀቀችውንም ርዮት ኧሙም በተመሳሳይ መልኩ ከአስተማሪነት ባሻገር ህጻናትን በመርዳት እና እንዲሁም በጽሁፎቻ በበቂ ሁኔታ የምትትታወቅ ሲሆን አቻ የማይገኝላት ትእግስተኛ ጋዜጠኛ የሚለውን ስያሜ አግኝታለች።
Average Rating