tamgeda@gmail.com
ባለፈው አርብ (ሃምሌ 4 /2015 እ ኤ አ ) ከመላው የአሜሪካ ግዛቶች የተሰባስቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ዲሞክራሲ ፣ ፍትህ ፣ እኩልነት እና ሰላም ናፋቂ ኢትዮጵያዊያን በአሜሪካው መናገሻ ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የዋይት ሃውስ ቤተ መንግስት ደጃፍ ላይ በመስባስብ የፕ/ት ባራክ ኦባማ አስተዳደር በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሂደ ያለውን ዘግናኝ እና አሳሳቢ የሆነው የስበዊ መብት ረገጣን ወደ ጎን በመተው በምትኩ ፕ/ት ኦባማ ለወቅቱ የኢህአዲግ መንግስት ባለሰልጣናት ኣውቅና እና “ቡራኪ ለመስጠት “በተያያዝነው የሃምሌ ወር መባቻ ላይ ወደ አ/አ ለመጓዝ ማቀዳቸውን በመቃዎም ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በአይነቱ እና በይዘቱ ታላቅ የተባለ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
ይህ አይነቱ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ይበል እና ወደፊትም ተቀናጅቶ ይቀጥል የሚያሰኝ ሲሆን፣ መቼም ሁሌም ትላልቅ ፕሮግራሞች ሲዘጋጁ እና ሲካሄዱ መጠነኛ የሆኑ ግድፈቶች መከስታቸው የማይካድ ሲሆን በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ ላይም ሰልፉን በግንባር ተገኝቶ ለመዘገብ የተላከው የአሜሪካ ራዲዮ የአማሪኛው ክፍል(ቬኦኤ) ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ሄኖክ ሰማ እግዜር ከግዙፉ ስልፈኛ መካከል አፈንግጠው የውጡ ጥቂት ስልፈኞች አላሰፈላጊ ከሆኑ ቃላት አንስቶ እንደ እርሱ ዜና ዘገባ “የጋዜጠኛ መታወቂያውን መንጭቆ መውሰድ እና መጣል፡ ኣርሱንም ማዋክብ እና ከጀርባው ለድብደባ ያደረስ” የሰነልቦና እና የአካል ጥቃት ፈጽመውበታል።ቪኦኤም አሳዛኙ ገጠመኙን በድህረገጹ ላይ በከፊል በተነቀሳቃሽ ምስል አስደግፎ ለጥፎት ይገኛል።
ጋዜጠኛ ሄኖክ ስለ አሳዛኙ ገጠመኙ ለፖሊስ ሲያስረዳ
እዚህ ላይ ጋዜጠኛ ሄኖክ ምን አይነት ባለሙያ ነው? ደካማ እና ጠንካራ ጎኖቹ ምንድን ናቸው ? ከሙያው አኳያ እነማንን አስከፋ እነማንንስ አስደስተ? ወዘተ… የሚሉት እና መስል ተጠየቆች እንደተጠበቁ እና ለ ቀጠረው (ለቬኦኤ ራዲዮ) ፣ለራሱ ለጋዜጠኛው ህሊና እና በዋንኛነት ደግሞ ለመላው የ ቬኦኤ አድማጮች ፍርድ የምተዋቸው ጉዳዮች ሲሆኑ ጋዜጠኛ ሄኖክ “ ባድማጮቹ ዘንድ የቱን ያህል የተጠላ እና የዝሆን ያህል የገዘፉ ጉድለቶች ቢኖሩበትም” ጋዜጠኛው አቅርቧል ለተባለው የተሳሳተ ዘገባዎች የህግ አግባብነት ባለው መልኩ መቃወም፡ መክሰስ እና ለአንተ በጭራሽ መረጃ አነስጥም (ለቃለ ምልልስ ፈቃደኛ አይደለንም) ማለት እየተቻለ “ ከራሷ ዜጎች አልፋ እኛም ብንሆን በአገራችን ያላገኝነውን እና ሁሌም ኣንዲተገበር የምንናፈቀው ሃሳባችንን በነጻ የመግለጽ፣ የመደራጀት ፣ በሰላማዊ መንገድ የፈለግነውን የመደገፍ እና የመቃውም ፍጹም መበት ባጎናጸፈችን በምድረ አሜሪካ እምብርት ላይ በአገሩ ልጆች በተለይ ደግሞ ለ ፍትህ ፣ ለዲሞክራሲ ፣ ሃሳብን በነጻ ለመግለጽ እና ለእኩልነት መብት መከበር ለመታገል እንዲሁም የአምባገነኖችን እኩይ ተግባራትን በጽኑ ለመቃወም እና ለአለም ህዝብ ለማጋለጥ ቁሩ እና ሃሩሩ ሳይበግራቸው ለተቃውሞ ሰልፍ ወደ አደባባይ ከወጡ ሺዎች መካከል በጣት የሚቆጠሩት ሰልፈኞች ያደረሱበት የማዋከብ ፣ የማሸማቀቅ ኣንደርሱ(ሄኖክ) ዘገባ “የጉሸማ ጥቃት “ የትም ይሁን የትም ፣በምንም መልኩ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘሁትም ። ጥቃቱን የፈጸሙት ወገኖችም ቢሆኑ በማወቅ ይሁን፣ በምንቸገርኝነት አሊያም በስሜታዊነት ከጋዜጠኛው ጋር የፈጠሩት እሰጣ እገባም ቢሆን ከጋዜጠኛው ጀርባ ኣለም አቀፍ ተደራሽነት ያለው ቪኦኤ የተባለ ግዙፍ ተቋም መኖሩን ፣ከዚህ ተቋም ጀርባም ነጻፕሬስን እንደ አይናቸው ብሌን የሚመለከቱት በብሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖች መኖራቸውን እና የእነርሱን አይኖችን ለመጠንቆል መሞከር እንደሆነ ጠንቅቀው የተገነዘቡት አይመስለኝም ።ይህ ጥቃት በሌላ ጎኑ በ አገር ቤት ጋዜጠኞችን ፣ጦማርያኖችን ፣ የፖለቲካ እና የሃይማኖት መሪዎችን እና ተወካዮችን በማዋከብ ፣ በማሳደድ፣ በማሰር ፣ ቶረቸር በማደረግ ፣ ያለ ጥፋታቸው በከባድ እስራት በመቅጣት እና በመበቀል ፣ እድል የገጠማችውንም እገር ጥለው እንዲስደዱ ላደረጋቸው እና በማደረግ ላይ ለሚገኘው ለወቅቱ የኢህአዲግ መንግስት የልብ ልብ የሚስጥ እና “አበጀህ!” የሚል መልእክት የሚያሰተላልፍ ነው ።
በተቃራኒው ደግሞ ህገመንግስታዊ መብት የሆነው ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብታቸውን ሲተገብሩ በተለያዩ የህግ ሽፋኖች አማካኝነት በቃሊቲ ፣በቂሊንጦ እና በሌሎችም እስር ቤቶች ውስጥ እየማቀቁ የሚገኙ የነጻ ፕሬስ አባላትን እና የዲሞክራሲ ታጋዮችን የማሳዛን ፣አንገትን የማስደፋት እና የማስለቀስ ድርጊት ሆኖ ተስምቶኛል ። ለምን ቢባል? ሃሳብን የመግለጽ መብት ለጥቂቶች ብቻ የማይስጥ ወይም “እኛ የወደድነው ብቻ ይደመጥ” የማይባልለት ተፈጥሮአዊ እና የስብ አዊ መብት በመሆኑ ነው ።
ለዚህ አባባሌ ማጥቀሻ የሆነኝ ዘንድ ከተቋቋመ አራት አስር አመታት ያስቆጠረው ታላላቅ የእምነት ተቋማት የሆኑት የእስልምና፣የክርስትና እና የአይሁድ አባቶች ፣ የአገር እና የፖለቲካ መሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችን በካርቱን አማካኝነት በፈርንፋይኛ ፣በእንግሊዘኛ እና በአስፓኒሽ ቋንቋዎች በማብጠልጠል እና በመሳለቅ የሚታወቀው ቻርሌይ ኢብዶ(Charlie Hebdo) ጋዜጣ በእስልምና ሃይማኖት በተለይ ደግሞ በነብዮ መሃመድ ዙሪያ ያወጣቸው ተከታታይ ካርቱናዊ ሰላቆቹን ተከተሎ በህትመቱ የተቆጡ ታጣቂዎች ባለፈው ጥር 7 /2015 እኤ አ ፓሪስ (ፈረንሳይ) በሚገኘው ቢሮው ላይ ባደረሱት ጥቃት ዋና አዘጋጁን ጨምሮ 12 አባላቱ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ እነደገደሏቸው መዘገቡ አየዝነጋም።ታዲያ ምንም እንኳን የጋዜጠኞቹ ምጻታዊ ስላቆች እና ፊዞች ሁሉንም ወገን ያስደስታል ባይባልም በጋዜጠኞቹ ላይ የተቃጣው የጥቃት እርምጃ ግን ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ላይ ከተሰነዘረ ጥቃት ጋር በማያያዝ በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ካፈው ግማሽ ምእተ አመት ጀምሮ የሚፈጁት የ ፍልስጤሙ እና የ እስራኤሉ (ፕ/ት መሃመድ ሃባስ እና ጠ/ሚ/ር ቢንጃሚን ናተኒያሁ)፣ ከድህረ የቀዝቃዛው የአለም ጦርነት በኋላ ግዙፍ የተባለ ውጥረት ውስጥ የገቡት የሩሲያው እና የዩክሪኑ ፕ/ት (የውጪ ጉ/ሚር ሰርጌ ላቫሮቭ እና ፕ/ት ፔትሮ ፖሮሽአንኮ) ጨምሮ ከ40 በላይ የአገር እና የሃይማኖት መሪዎች( እንደ አጋጣሚ ከአውራ መሪዎች መካከል ፕ/ት ኦባማ ብቻ አለተገኙም) በፓሪስ ጎዳና ላይ ከ አንድ ሚሊዮን በላይ በሚገመቱ አፍቃሪ ነጻ ፕሬሶች በመታጀብ እና እጅ ለእጅ በመያያዝ “እኔም ቻርሊይ ኢብዶ ነኝ”(Je suis Charlie Hebdo)፣”ፍቅር ከ ጥላቻ ይጠነክራል”( Love is stronger than hate) …ወዘተ የሚሉ መፈክሮችን በማስማት የነጻ ፕሬስ ነጻነት በየትም ስፍራ ገደብ ሊበጅለት እንደማይገባ እና ነጻ ፕሬስ በየትኛውም ስፍራ እና ጊዜ በጭራሽ ለድርድር እንደማይቀርብ በማስረገጥ አቋማቸውን ገልጸዋል።የሰብ ኣዊ መብት ተሟጋቾቹ እነ ሁማን ራይት ዎች እና አሚኒሲቲይ ኢንተርናሽናል ፣ የጋዜጠኞች እንባ ጠባቂዎቹ እነ ሲፒጂ(ከ ኒዮርክ) እና ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ማህበር(ከፖሪስ)ጥቃቱን በከፍተኛ ቃላት እና ቁጣ አውግዘውታል።
ሰለ ፓሪሱ የቻርሊይ ኢብዶ ጋዜጣ አሳዛኝ ገጠመኝ ለትውስታ ያህል ይህንን ያህል ካልኩ ወደ ሰሞነኛው የዋይት ሃውሱ ደጃፍ በጋዜጠኛ ሄኖክ እና “ሰራው አይጥመንም” ባሉት ወገኖች መካከል የተፈጠረውን ግጭት በተመለከተ ከተቃውሞ ስልፉ አዘጋጆች መካከል አንዱ ለቬኦኤ ቀርበው “ ሄኖክ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዘንድ የወቅቱን ስርአት ይደግፋል ተብሎ ሰለሚታመን ፣በቅርቡም በኢትዮጵያ የተካሄደው እና ኢህአዲግ 100% አሸነፍኩ ያለው ምርጫን ፍትሃዊ ነው ብሎ በመዘገቡ በርካታ ኢትዮጵያዊያኖች በጥሩ አይን ሰለማያዩት ፣ሄኖክ ለዘገባ ከሚመጣ ቪኦኤ በእርሱ ፈንታ ሌላ ሰው ቢልክ የተሻለ መሆኑን መክሬው ነበር ። በሄኖክ እና በግለስቦቹ መካከል በተፈጠረው ግጭት ላይ የታክስ ፎርሱ(የሰልፉ አዘጋጆች) እጆች በፍጹም የለበትም።” በማለት የታክስ ፎርሱ ትላንትም ሆነ ወደፊትም ለሰላማዊ ትግሉ በጽናት እንደሚቆም ሲናገሩ ተደምጠዋል። እዚህ ላይ ግብረሃይሉ ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ መጎልበት የሚያደርጋቸው ጥረቶች በማንኛውም ወገን የሚበረታታ እና የሚደገፍ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ የግብረሃይሉን መንፈስ እና አላምን የሚያጎድፉ እንደ ስሞነኛው አይነት አላስፈላጊ እና አሳዛኝ እንከኖች ሲፈጠሩ ግን ግብረሃይሉ በግንባር ቀደምነት ወጥቶ “ በእኛ ስም መደረግ የለበትም” በማለት የማጋለጥ እና የማውገዝ ዲሞክራሲያዊ ሃላፊነት የተጣለበት ይመስለኛል። ይህንንም ማድረግ ለወደፊቱ ትግሉ መንገድ ይጠርጋል ። የአሜሪካ ህግም ይደግፋል ።
የተጠያቂነት ነገር ካነሳሁ ዘንዳ ቪኦኤም ቢሆን በጋዜጠኞቹ ስራዎች ዙሪያ ስሞታዎች እና ወቀሳዎች ከየቱም አቅጣጫ ሲመጡ ጉዳዩን በግልጽነት በመመርመር የደረስበትን ጭብጥ ለአድማጮቹ ውሎ ሳያድር የማሳውቅ እና የጥርጣሬ ዳመናዎችን የመግፈፍ የሚዲያ ተቋማዊ ሃላፊነት እንዳለበት እና በየትኛውም ስፋራ የሚሰማሩ ጋዜጠኞቹ ደህንነትን በተመለከተም “የትም ፍጭው ዱቂቱን ብቻ አምጭው ወይም ለዘብተኛ“ ከሚያስመስል አካሂድ ወጥቶ ሪፖርተሮቹ “ የፕረስ ፍቃዳቸው ሲታገድ፣ ሲነጠቅ፣ሲዋከቡ ወይም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አገር ጥለው እንዲሰደዱ ሲደረጉ “ እነ CPJ,RSF, HRW,AI …ወዘተ የሚያወጧቸውን ፕረስ ነክ ዘገባዎችን እና መግለጫዎችን እየጠቀሰ ከሚያሰደምጠን አዲስ መጢዎቹ እነ አልጀዚራ ቲሊቭዥን ስለባልደረቦቻቸው በግብጽ መታስር እና መዋከብ በተመለከተ ከ አንድ አመት በፊት ካደረጉት የነጠረ ተከታታይ ሙያዊያዊ የተቃውሞ ፣የማውገዝ እና የአቁዋም ጽናት ሊማር ይገባዋል እላለሁ።
በስተመጨረሻም ጋዜጠኛ ሄኖክ ስማ እግዚሄር ከዘገባዎቹ ጋር በተያያዘ ስሞኑን ያጋጠመውን አካላዊ እና ሰነልቦናዊ ወከባን ተከትሎ ሰሞኑን የተነሱት አንዳንድ የደጋፍ እና የተቃውሞ አሰተያየቶችን ስመለከት በፈረንሳዩ የቻርሊይ ኢብዶ ጋዜጠኞች ላይ የደረሰውን ጥቃት ለመቃወም በመዲናይቱ ፓሪስ ቻርልስ ደጎል አደባባይ ዙሪያ ተሰባስበው ከነበሩት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ሰልፈኞች ውስጥ ወደላይ ከፍ አድረገው ካውለበለቧቸው የነጻ ፕሬስ አፍቃሪዎች መፈክሮች እና ፖስተሮች መካከል” አንተ በምትለው አልስማማም ፣ነገር ግን ማለት የምትፈልገውን ሁሉ እንድትናገር እስከ ህይወት መሰዋእትነት ድረስ እዋደቅልሃለሁ።”(“ I don’t agree with what you say, but I will fight to the death to defend your right to say it.” ) የሚለው መፈክር በቻርልይ ኢብዶ ጋዜጣ የተለያዮ ፣ እወዛጋቢ እና አከራካሪ ስላቃዊ ካርቱኖች እና መጣጥፎች ነጋ ጠባ ከሚፈለቀለቁት ባለተናነስ በጋዜጣው አድራጎቶች እርር እና ድብን በማለት ፈጣሪ ኣንዳች የሆነ የማስታገሻ መአቱን እንዲያወርደበት የተመኙ ቢሊዮኖች (ጽረ- ቻርሊይ ኢብዶዎች )ሳይቀሩ ልባቸውን ነካክቶታል ፣ ቀልባቸውንም ስቧል ። እኔም መፈክሩ ከፓሪስ ውጭ የምንገኘነውን በዙዎቻችንን ያስማማል ብዮ አምናለሁ።
በዚህ አጋጣሚ የለጥፋታቸው እና ያለማሰረጃ ከአመታት በላይ ከውህኒ ቤት ተውርውረው ሲማቅቁ ከሚገኙት ከሃያ በላይ ጋዜጠኞች፣አምደኞች እና ጦማሪያኖች መካከል አምስት ያህሉ ለእነ እነርሱ ጭምር ባስገርማቸው ሁኔታ የፕ/ት ኦባማን የአ/አ ጉብኝት ዋዜማን ተከትሎ የኢሀአዴግ መንግስት የ ኦባማን አፍ ለማዘጋት ሲል “ክሴን አንስቻለሁ” በማለት ምንም እንኳን ቀድሞውኑም መከሰስ እና መታስር ሳይገባቸው ከእስራት ተለቀው ቢያንስ ከሚወዳቸው ህዝብ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል በመብቃታቸው በውስጤ ልዮ የደስታ ስሜት ጭሮብኛል ። የተቀሩትም በ አስር ሺዎች የሚቆጠሩት የህሊና ኣሰረኞች እና ወገኖቻችን ከሰቆቃው ነጻ የሚሆኑበት እና ማጎሪያ ቤቶቹም ቢሆን ወደ ሆስፒታልነት ፣ወደ ት/ቤት ነት ወደ ሙዚዮምነት እና ወደ መዝናኛ ስፍራነት የሚቀየሩበት ጊዜ እሩቅ እንደማይሆን ጽኑ እምነት አልኝ።
Average Rating