www.maledatimes.com የሕወሃት የንግድ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ አሊ ሲራጅ በድንገት አረፉ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሕወሃት የንግድ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ አሊ ሲራጅ በድንገት አረፉ!

By   /   July 11, 2015  /   Comments Off on የሕወሃት የንግድ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ አሊ ሲራጅ በድንገት አረፉ!

    Print       Email
0 0
Read Time:50 Second

 

ቅዱስ ሃብት  በላቸው

የኦህዴድ መሪዎች ከስብሰባ መልስ በሚከሰት ድንገተኛ ሕመም እስከወዲያኛው የማሸለባቸው ሚስጢር ምን ይሆን?
የንግድ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ አሊ ሲራጅ ዛሬ ጠዋት በናዝሬት/አዳማ በኦህዴድ ስብሰባ ላይ አንዳሉ በድንገት በመታመማቸው ለሕክምና ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ሳለ መንገድ ላይ ህይወታቸው ማለፉን ለገዥው መንግስት ቅርበት ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።
የኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ አሊ ሲራጅ የ46 አመት ጎልማሳ ሲሆኑ በቅርቡ በተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ ኦህዴድ/ኢህአዴግን ወክለው በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወዳድረው ማሸነፋቸው ተገልፆ ነበር።
ከአንድ አመት በፊትም የኦሕዴድ ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ሙሉ ቀን በድርጅታቸው ግምገማ ላይ ውለው ምሽት ላይ ቢሯቸው ውስጥ እንዳሉ እራሳቸውን ስተው በመገኘታቸው፤ ለሕክምና ውጭ አገር ድረስ ቢሄዱም ሕይወታቸውን ማትረፍ ባለመቻሉ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል። አቶ አለማየሁ ከሙስና የፀዱ ብቻ ሳይሆኑ፤ ሙሰኞችንና ሙስናን ለመዋጋት ቁርጠኛ አቋም የነበራቸው ሰው መሆናቸውንና በቅርበት የሚያውቋቸው ሰዎች የሚናገሩ ሲሆን፤ የሕልፈተ-ሕይወታቸውም መንስዔም ሆን ተብሎ የተሰጣቸው መርዝ ሳይሆን እንደማይቀር ብዙዎች ጥርጣሬያቸውን ሲሰነዝሩ እንደነበር ይታወሳል። አቶ አለማየሁም ይቺን ዓለም ላይመለሱባት የተሰናበቷት ገና የ45 ዓመት ጎልማሳ ሳሉ ነበር።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on July 11, 2015
  • By:
  • Last Modified: July 11, 2015 @ 8:31 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar