ቴዲ በድጋሚ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ነበር (ክንፉ አሰፋ ፍራንክፈርት) ባለፈው ሳምንት ወደ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ-ኬንያ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ከጀመረ በኋላ እንዲመለስ መደረጉን የአየር መንገዱ ምንጮች አስታወቁ። በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ የሁለት መቶ ሺህ ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ምንጮቹ ጠቁመዋል። በተሳፋሪዎች ላይም ከፍተኛ መጉላላት ደርስዋል። teddy afro አውሮፕላኑ ካኮበኮበ በኋላ እንዲመለስ የተደረገበት ምክንያት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከባለቤቱ ከአለምሰት ሙጬ ጋር በአውሮፕላኑ በመሳፈሩ ምክንያት መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ አስደንጋጭ ክስተት የተፈጸመው አለምሰት ሙጬ በደረሰባት ድንገተኛ ህመም ለህክምና ወደ ኬንያ እየተጓዘች ባለችበት አውሮፕላን ነው። አውሮፕላኑ ዞሮ ከተመለሰ በኋላም ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በደህንነቶች ተይዞ ከአውሮፕላኑ እንዲወጣ ተደርጓል። የህወሃት የደህንነት አባላት የቴዲ አፍሮን ፓስፖርት ቀምተው አሰናብተውት ነበር። ቴዲ አፍሮ በሰሜን አሜሪካ በየዓመቱ የሚደረገው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ላይ ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ጋር መጋበዙ የሚታወስ ሲሆን ይህንን በመቃወም ሚሚ ስብሃቱ እና ባለቤትዋ ዘሪሁን ተሾመ ዘመቻ ከፍተው እንደነበር የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን 33ኛ ዓመት በዓል ላይ እነዚህ ድምጻውያን አልተገኙም። ድምጻውያኑ በበዓሉ ያልተገኙበት ምክንያት የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ በደረሰው የኮምፒውተር ሽብር ጥቃት- የቪዛ ችግር ያጋጠማቸው መሆኑ ቢገለጽም፤ ቪዛ ቢያገኙ ኖሮ እንኳ በደህንነቶች አፈና ከሃገር ሊወጡ እንደማይችሉ ግልጽ ነበር። የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌዴሬሽን አሸባሪ ተብሎ በነሚሚ ስብሃቱ መፈረጁን የህወህት መንግስት ተቀብሎ በውስጥ አጽድቆታል። ቴዲ አፍሮ ባለቤቱን ለማሳከም ወደ ኬንያ በመጓዝ ላይ እንዳለ በኬንያ በኩል ወደ አሜሪካ ሊጓዝ ነው ተብሎ በነ ሚሚ ስብሃቱ በደረሰው ጥቆማ ነው አውሮፕላኑ እንዲመለስ የታዘዘው። በዚህ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት በተሳፋሪው ላይም ከፍተኛ መጉላላት የደረሰ ሲሆን አየር መንገዱም ለከፋ ኪሳራ ተዳርጓል ሲሉ የአየር መንገዱ ምንጮች ተናግረዋል። ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከባለቤት ጋር ወደ ኬንያ ይጓዝ የነበረው የሰሜን አሜሪካው የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ከተጠናቀቀ በኋላ ነበር። የህወሃት ደህንነት አባላት ይህንን እንኳን ማገናዘብ የማይችሉ ደካሞች እንደሆኑ ምንጮቹ ተቁመዋል። ከብዙ መጉላላት በኋላ ቴዲ አፍሮ ፓስፖርቱን አስመልሶ ወደ ጀርመን – ፍራንክፈርት የበረረ ሲሆን በቅዳሜ ምሽት የአውሮፓ ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ ዝግጅቱን ያቀርባል። ከዚያም የጄኔቭ ስዊዘርላንድ ማዘጋጃ ባሰናዳው ዝግጅት ላይ ልዩ ተጋባዥ በመሆን በመጭው ሳምንት ስራውን ለህዝብ በነጻ ያሳያል። የቴዲ አፍሮ ባለቤት አለምሸት ሙጬ በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ-ቨርጂንያ ህክምናዋን እየተከታተለች ትገኛለች። ድምጻዊ ቴዲ አፍሮን በአካል አግኝቼ ባነጋገርኩበት ግዜ የዚህን ዘገባ ትክክለኝነት አረጋግጫለሁ። ይህንን እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ወደፊት በስፋት እመለስበታለሁ።
ቴዲ በድጋሚ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ነበር።
Read Time:1 Minute, 38 Second
- Published: 10 years ago on July 18, 2015
- By: maleda times
- Last Modified: July 18, 2015 @ 6:00 am
- Filed Under: Ethiopia
Average Rating