www.maledatimes.com የቀድሞ የ‹‹አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ›› ፓርቲ የአዲስ አበባ ወጣቶች አደረጃጀት የፋይናንስ ኮሚቴ አባል ፍቃዱ በቀለ ታሰረ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የቀድሞ የ‹‹አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ›› ፓርቲ የአዲስ አበባ ወጣቶች አደረጃጀት የፋይናንስ ኮሚቴ አባል ፍቃዱ በቀለ ታሰረ

By   /   July 18, 2015  /   Comments Off on የቀድሞ የ‹‹አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ›› ፓርቲ የአዲስ አበባ ወጣቶች አደረጃጀት የፋይናንስ ኮሚቴ አባል ፍቃዱ በቀለ ታሰረ

    Print       Email
0 0
Read Time:51 Second

ዛሬ ጥዋት ሌላ የእስር ዜና ሰማን፡፡ የታሰረው፣ የቀድሞ የ‹‹አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ›› ፓርቲ የአዲስ አበባ ወጣቶች አደረጃጀት ውስጥ የፋይናንስ ኮሚቴ አባል እና የወረዳ 15 ሰብሳቢ የነበረው ፍቃዱ በቀለ ነበር፡፡ አጋጣሚ ከወዳጄ አናንያ ሶሪ ጋር ስለነበርን ‹‹በምን ይሆን ደግሞ?›› ብለን ራሳችንን መጠየቃችን አልቀረም፡፡ ወላጅ እናቱና እህቱን በአካል ጠይቀን እንደተረዳነው፣ አንድ ጓደኛው ‹‹አሸባሪ ነው›› ብሎ ጠቁሞበት መሆኑን ነው፡፡ እኛም ካዛንቺስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ልንጠይቀው ሄደን ‹‹እሱን ማግኘት አይቻልም›› ብሎ አንድ ፖሊስ ቢነግረንም በአጋጣሚ ከርቀት አይተነው ሰላም ልንለው ችለናል፡፡
እንግዲህ፣ በየዕለቱ የዜጎችን እስር መስማት የተለመደ ሁነት ሆኗል፡፡ የባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለትየ‹‹ቀዳሚ ገጽ›› ሥራ አስኪያጅ እና የቀድሞ የ‹‹ሚሊየኖች ድምጽ›› ሪፖርተር የነበረው ሃብታሙ ምናለም ‹‹የአልሸባብ ሴል ነህ፤ ኦባማ በሚገኝበት ስብሰባ ላይ የቨብር ተግባር ልትፈጽም አሲረሃል›› ተብሎ ተጠርጥሮ መያዙንና ፍርድ ቤት ቀርቦም ለድጋሚ ቀጠሮ ለሐምሌ 20 ቀን 2007 ዓ.ም መቀጠሩ ይታወሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከቀናቶች በፊት ሌላ የቀድሞ አንድነት ሴት አባል ከታሰረች በኋላ መፈታቷም የሚታወቅ ሲሆን አበበ ቁምላቸው የሚባል የቀድሞ አንድነት በአሁን ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ አባልም ‹‹ወደኤርትራ ሰው ትመለምል ነበር፣ አንተም ወደዚያ ልትሄድ አስበሃል›› ተብሎ አሁንም ድረስ በካሳንቺስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛል፡፡

Elias Gebru Godana's photo.በኤልያስ ገብሩ
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on July 18, 2015
  • By:
  • Last Modified: July 18, 2015 @ 8:01 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar