በሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ሸዋሮቢት ከተማ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባሎች እና ወጣት የለውጥ አራማጅ የፓርቲው አቀንቃኞች በመንግስት ሃይል ታፍነው ወደ እስር ቤት ከተወረወሩ ከወር በላይ መሆናቸውን ከክልል ሶስት ሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋሮቢት ከተማ አስተደር ነዋሪዎች የሆኑ እና የፓርቲው አባሎች እና አመራሮች ለማለዳ ታይምስ የአባሎቻቸውን መታሰር ጠቁመዋል ።
እነዚህ የሰማያዊ ፓርቲ አባሎች በየትኛው ቦታ እና እንዴት እንደታሰሩ ለመጠየቅ ቢሄዱም የመንግስት ሃይሎች ምንም አይነት መረጃም ሊሰጧቸው እና ያሉበትንም ሁኔታዎች ሊያሳውቋቸው ባለመቻላቸው በከፍተኛ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የሰማያዊ ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት ለማግኘት እና ስለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው መግለጫ እንዲያወጡ ለመጠየቅ በደጋግሚ ቢጥሩም ምንም ምላሽ ሊሰጧቸው አለመቻሉ እራሱ አሳሳቢ ከመሆኑም በልይ በክልሉ ለሚገኙት አባሎች እራስ ምታት መሆኑን ገልጸዋል ።
የፓርቲው አመራር ምላሽ መስጠት ሲገባቸው እንደ ወያኔ መንግስት ለአባሎቻቸው ዝምታን መፍጠሩ ለለውጥ የተዘጋጁ ሳይሆኑ ለጥቅሞቻቸው የተነሱ ሃይሎች መስለው ነው የታዩን ብለው የተናገሩት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት እና የቀወት ወረዳ የሰማያዊ ፓርቲ የወጣት መልማዮች ዋና ሃላፊ በዛሬው እለት ይህንን መግለጭ ወደ ግል መገናኛ ብዙሃን ልናመጣው የቻልነው ሰሚ አካል ብናገኝ ጥሩ ነው በሚል ምክንያት ነው ሲሉም አክለው ገልጸዋል ። ከአንድ ወር በፊት የታሰረውን ወጣት ቴዎድሮስ ሃብቴ እስካሁን ያለበትንም ሁኔ ካለማወቃችን የተነሳም ለፍርድ እንኳን አቅርበው ጥፋተኝነቱንም ህነ የተከሰሰበትን ሁኔታ ለመረዳት አልቻልንም የሌሎችንም ወጣት የዘርፍ ክፍሎቹንም ለመከታተል አልቻልንም ሲሎ ገልጸዋል ።ማለዳ ታይምስ
Average Rating