www.maledatimes.com የ”ኢትዮጵያ” ደራሲዎች ማህበርና የሕወሓት እሰጥ አገባ/የፖስታ ቤት ምፀት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የ”ኢትዮጵያ” ደራሲዎች ማህበርና የሕወሓት እሰጥ አገባ/የፖስታ ቤት ምፀት

By   /   September 28, 2012  /   Comments Off on የ”ኢትዮጵያ” ደራሲዎች ማህበርና የሕወሓት እሰጥ አገባ/የፖስታ ቤት ምፀት

    Print       Email
0 0
Read Time:12 Minute, 47 Second

የ‹‹ኢትዮጵያ›› ደራሲዎች ማህበር ከኢትዮጵያ ፖሰታ አገልግሎት ጋር በመተባበር የማስታወሻ ቴምብር ከተዘጋጀላቸው የአማርኛ ደራሲዎች ዝርዝር ዉስጥ የአፈ ቀይሳር አፈወርቅ ገ/የስ ስም ሳይ እንዴት ሊሆን ይችላል? ኢትዮጵያውያን ግራዚያኒ በአገሩ ሊሰራለት የታሰበውን ሃወልት እንድንቃወም በትጋት እያስታወሱን ባለበት ወቅት የራሳችን ገራዚያኒ አዚሁ ሃወልት እያሰራንለት ነው? እና ለምን የአማርኛ ቋንቋ ደራሲዎች ብቻ ተመረጡ? የሚል ጥያቄዎች ይዤ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ <<ኢትዮጵያ>> ደራሲዎች ማህበር ጎራ አልኩ፤
1. ጥያቄ አንድ – አፈወርቅ ገ/የስ ኢትዮጵያ በጣሊያን እንድትገዛ(ቅኝ ገዛት ስር እንድትሆን) ሽንጣቸውን ገትረው የሞገቱ ሰው ሆነው እያለ (በጣሊያን መወረራችንን ይደግፉታል) እንዴት የማስታወሻ ቴምብር ይሰራላቸዋል? ልብ አድርጉ፤ የሮማ ካቶሊክ የጣልያንን ጦር ባርካ በመሸኘቷ ነው ይቅርታ እንድትጠይቅ ኢትዮጵያውያን እየተሟገቱ ያሉት፡በሁሉቱ መካከል ልዩነት ይኖር ይሆን? ማህበሩስ ባዘጋጀው ብሮሸር የአፈ ቀይሳርነት ማእረግ ከጣሊያን መንግስት እንዴት ማግኘት እንደቻሉ ለምን አልገለፀውም?
ከማህበሩ ያገኘሁት ምላሽ፡- እኛ ለአማርኛ ስነፅሁፍ ያደረጉት አስተዋፅኦ እንጂ የሰዎቹ ግለ ታሪክ አናይም፡፡
የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጭው ማለት መሆኑ ነው እንግዲህ፡፡ ግን ለተማሪዎች ስናስተምር የአፈወርቅን ባንዳነት ወይስ ለአማርኛ ስነፅሁፍ ያደረጉት አስተዋፅኦ ወደ አእምሮአቸው ቀድሞ እንዲመጣ የምንፈልገው?
2. አፈወርቅ ከባንዳነታቸው በተጨማሪ የሚታወቁት በዘር ጥላቻ ፅሁፋቸው ነው፡፡
ዳግማዊ አጤ ምንሊክ በሚል ለአፄ ምንሊክ እጅ መንሻነት በፃፉት መፅሃፋቸው (አስቡት እነደገና በታተመው የመፅሃፉ ሽፋን ላይ የመቶ አመት ባለፀጋ ታላቅ መፅሃፍ ይላል)
“ምንሊክ በነገሰልነና ይህ አምበጣ ትግሬ በጠፋልነ እያለ የማመኝ ሰው በኢትዮጵ አልነበረም” ( ገፅ 48)
“ጎጃምን የመሰለ ደግ አገርም ሶስት ወር ሙሉ በትግሬ አንበጣ ተመደመደ” (ገፅ 52)
“የትግሬ ወታደር በዚያ ጉረሮ በሚፍቅ ቋንቋው ኩሪ ኩሪ እያለ እርጉዝ አስወረዳት፤ እመጫት ጡቷ ደረቀባት” (ገፅ54)
ብለው ፅፈው ነበርና ለሽልማት ካበቃቸው አንዱ መስፈርት ይኼ ይሆን ብሎ መጠርጠር ይቻል ይሆን?
3. ጥያቄ ሁሉት፡- ደብተራ ፍስሃን እንዴት አላካተታችሁትም?
በማህበሩ ፅ/ቤት ያገኘኋቸው ሰው ምላሽ፡ ደብተራ ፍስሃን አንድ አፄ ምንሊክ ላይ ችግር ያለበት ፍትህ ጋዜጣ ላይ የሚፅፍ ዮናስ የሚባል ልጅ ሲጠቅሰው ስሙን አስታውሳለሁ፡፡
የኔ ማብራሪያ –
‹‹ደብተራ ፍስሃ ማለት የነ አፈወርቅ ዘመን ሰው(Contemporary) ነው፡፡ ጦብላህታ የሚል ርእስ ያለው የትግርኛልብ ወለድ ፅፏል፡፡ ደብተራ ፍስሃ የመጀመሪያ የትግርኛ ልብ ወለድ የደረሱት እ.አ.አ. በ1895 ሲሆኑ አፈወርቅ ግንየመጀመሪያ የአማርኛ ልብ ወለድ የደረሱት(የታተመው) በኛ አቆጣጠር በ1900 ነው፡፡የመጀመሪያ የአማርኛ ልብወለድ ደራሲ መሆን ያሸልማል፡፤ የመጀመርያ የትግርኛ(የኢትዮጵያ?) ልብ ወለድ ደራሲ መሆን ግን እንኳንስሊያሸልም ስምህ እንኳን አይታወቅም፡፡ እና የኢትዮጵያ ደራሲዎች ማህበር ሳይሆን የአማርኛ ቋንቋ ደራሲዎች ማህበርመባል ነው ያለባችሁ ››
የሚል ድምዳሜየን ከተናገርኩ በኋላ ተጨማሪ ጥያቄ ሰነዘርኩ-፤ ‹‹ ምን ያህል በእንግሊዘኛ ቋንቋ የፃፉ ኢትዮጵያውያን ደራሲዎች አሏቹህ? ››
የማሕበሩ ሀላፊዎች አንድ ሶስት የሚሆኑ ደራሲዎችን ከጠቀሱልኝ በኋላ ‹‹The shadow of my company›› የሚል ርእስ ያለው ልብወለድ ደራሲስ ታውቁታላቹህ የሚል ጥያቄ ስወረውር መልሱ አናውቀውም ሆነ፡፡
አንደኛውን በማህበሩ ላይ ያለኝ አስተያየት ተዛብቷልና ‹‹ ደራሲውን ያላወቁት ደራሲው ትግራዋይ (የትግራይ ሰው) ያውም የህወሓት ታጋይ የነበረ ስለሆነ ይሆን? ›› የሚል ጥያቄ ወደ አእምሮየ መጣ፡፡
4. በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት ኢንስቲትዩት በቢፒአር ጥናት ታጥፎ ‹‹ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ›› ሲሆን፤ የዲፓርትመንቱ (የትምህርት ክፍል) ሃላፊው በምክንያት አስደግፈው ያቀረቡት ተቃውሞ ከቢፒአር ኮሚቴ በስተቀር የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ቀልብ ስቦ እንደነበር አምናለሁ፡፡
አሁን ግን ለአማርኛ ቋንቋ ደራሲዎች የማስታወሻ ቴምብር እንዲሰራላቸውና በአንጻሩ የእነ ደብተራ ፍስሃን ስማችውን እንኳን ለማወቅ ያልቻሉት(ያልፈለጉት?) እነዛ መምህራን መሆናቸውን ሳውቅ ግን የቢፒአር ኮሚቴ አባላት ‹‹የመምህራኑን አመለካከት/አስተሳሰብ በጥናታቸው ደርሰውበት ይሆን?›› የሚል ሃሳብ አጫረብኝ፡፡
ኮሚቴዎቹ ‹‹ የኢትዮጵያ ›› ቢባልም የሚያተኩሩት የአማርኛ ቋንቋ ላይ ስለሆነ ‹‹ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ›› ተብሎ ቢጠራ ይሻላል ነበር ያሉት፡፡ የኢትዮጵያ ደራሲዎች ማህበርና የአአዩ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በተግባር የቢፒአር ኮሚቴውን ድምዳሜ አጠናከሩት እንጂ የተለየ ሆኖ አልተገኘም፡፡
5. ኢትዮጵያ ምፀት የሞላባት አገር አይደለች? ‹‹አክሱም ለወላይታ ምኑ ነው? ›› ተብሎ ሲያበቃ የአክሱም ሀውልት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ የወላይታ ሰው እንደሆኑት ሁሉ፤ የአፈወርቅን የማስታወሻ ቴምብር ያዘጋጀላቸው መ/ቤት ሃላፊ የትግራይ ሰው ናቸው፡፡ አቶ ጊደይ ስለ አፈወርቅ የሚያውቁት ነገር ይኖር ይሆን? እስቲ የምታውቋቸው ካላችሁ ጉዳዩን አንሱላቸው፤፤
6. በደራሲዎች ማህበር ያገኘኋቸው ሰው የማህበሩ ሰዎች ወደ ትግራይ ጉዞ ለማድረግ እቅድ እንዳላቸው ነገሩኝ (ጉዞው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ተራዘመ እንጂ መስከረም መጀመሪያ ላይ ነበር ለማድረግ የታሰበው)፡፡ የአማርኛ ስነፅሁፍ ላይ ማብራርያ ለመስጠት ይሆን የጉዞው አላማ?
ለማንኛውም አኔ ደግሞ ወደ መቐለ እየሄድኩ ስለሆነ ማህበራቹህ የትግርኛ ደራሲዎችን ሊወክል እንደማይችል ከትግርኛ ቋንቋ ሙህራን ጋር እነጋገርበታለሁ፤ የትግርኛ ቋንቋ ስነፅሁፍ ከአማርኛ ይቀድማል እየተባለ የሚወራው ትክክለኛ ከሆነም በጥናት አስደግፈው በአደባባይ እንዲሞግቱ ለእነ ዳንኤል ተኽሉ ሃሳብ አቀርባለሁ ብየ ከማህበሩ ፅህፈት ቤት ወጣሁ፡፡
*****************
The author Tesfakiros Arefe can be reached at: tesfa_kiros@yahoo.com.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 28, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 28, 2012 @ 12:51 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar