0
0
Read Time:35 Second
———
የቀድሞ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች ም/ሰብሳቢ የነበረው እና የዛሬ 20 ቀን በሽብር ወንጀል ተርጥሮ፣ ‹‹ሰዎችን ለግንቦት ሰባት በመመልመል ወደኤርትራ ትልክ ነበር›› የተባለው ፍቃዱ በቀለ ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ገደማ በዋስ ከታሰረበት ካሳንችስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተፈታ፡፡ በተጨማሪም በተመሳሳይ ክስ ተጠርጥሮ ከ25 ቀናት በላይ በዚሁ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው የቀድሞ አንድነት እና በአሁን ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አበበ ቁምልቸውም በዋስ እንዲወጣ መታዘዙን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ ዜናም፣ ‹‹የአልሸባብ ህዋስ ነህ፤ ባራክ ኦማባ በሚገኙበት ስብሰባ ወቅት የሽብር ወንጀል ልትፈጽም አሲረሃል›› ተብሎ ለ28 ቀናት፣ መገናኛ አሚቼ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው የ‹‹ቀዳሚ ገጽ›› ጋዜጣ ሥራ አስኪያጅና የቀድሞ የ‹‹ሚሊየኖች ድምጽ›› ጋዜጣ ሪፖርተር ሀብታሙ ምናለ ከትናንት በስትያ ምሽት 2፡30 ገደማ ከእስር መውጣቱ ይታወሳል፡፡

Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating