www.maledatimes.com ፍትህ ፍትህ ፍትህ ለአሚራ!!! ሼር በማድረግ ለፍትህ እንጩህ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ፍትህ ፍትህ ፍትህ ለአሚራ!!! ሼር በማድረግ ለፍትህ እንጩህ።

By   /   August 10, 2015  /   Comments Off on ፍትህ ፍትህ ፍትህ ለአሚራ!!! ሼር በማድረግ ለፍትህ እንጩህ።

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 19 Second

Amira

Amira


ሰለሞን ታደሰ
ይህች እህል እና ውሃ ያልለየች የ4አመት ከ6 ወር ታዳጊ መኖሪያዋ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ነው ።
በአንድ የቀን ጎዶሎ ወላጆቹዋ በተከራዩበት ግቢ ውስጥ ነዋሪ በሆነ የ25 አመት ወጣት እንደተደፈረች ለፖሊስ በደረሰ ክስ መነሻነት እና በተደረገላት የህክምና ምርመራ ድንግልናዋ ያልተገሰሰ ቢሆንም የማህፀን ግድግዳ የመሰንጠቅ ፣ የመላላጥ እንዲሁም የመቅላት ምልክት እንደሚያሳይ ይጠቁማል።
ተከሳሹ በጊዜው በ30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ዋስትና ከእስር የተፈታ ሲሆን የተመሰረተበት ክስ ደግሞ በመራቢያ አካሉ ሳይሆን በእጁ ነው ድርጊቱን የፈፀመው በሚል በአስገድዶ መድፈር ሳይሆን “6264 ሀ ን በመተላለፍ” ማለትም “መሰል ድርጊት ” በተባለ ሆነ።
ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎት ተከሳሹን ጥፋተኛ ነህ በማለት ሀሙስ እለት የወሰነው ውሳኔ ግን በርካቶችን ያስደነገጠ እና የወላጆችዋን አንገት ያስደፋ ነበር… የ4 ወር እስር!!!!።
እለተ አርብ መረጃው እንደደረሰኝ ከአሚራ እናት እና አባት ጋር ወደ ፍርድቤቱ በመሄድ ዳኛውን ለማግኘት እና ለማነጋገር ብሞክርም ባለመኖራቸው ሊሳካልኝ አልቻለም ። በመቀጠል ወደ አቃቂ ቃሊቲ ፍትህ ፅ/ቤት በማምራት ከቢሮው ዋና ሀላፊ ጋር በመሆን የውሳኔ ፋይሉን መመልከት ብንችልም ውሳኔው እንደተገለፀው ነበር ።አቃቤ ህጓ የክስ ደረጃውን ለምን ዝቅ አደረገችው? መድፈር ማለት ምን ማለት ነው? ጥፋተኛው ተጠያቂ እንዲሆን የግድ ድንግልናዋ መገሰስ ነበረበት? የሳንባ በሽተኛ እና በቀጣዩ አመት ተመራቂ ነኝ ብሎ የጥፋት ማቅለያ ማቀረብስ ከእርከን በታች ፍትህ ያሰጣል? ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎቼ የሀላፊው መልስ ” ስለጉዳዩ የሰማሁትም ከአንተ ነው አቃቤ ህጓን አነጋግሬ ሰኞ መልስ እሰጥሀለሁ”የሚል ነበር።
እነዛ በችርቻሮ ንግድ የሚተዳደሩት ምስኪን ወላጆች ግን በተሰበረ ልብ እንባቸውን እየዘሩ ” ወላድ ይፍረደን!! መንግስት ይፍረደን!!” ይላሉ በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጠኛ መሆኔን ጠላሁ ህመማቸው አመመኝ! እንባቸው አስነባኝ።
እኔ አቅመ ደካማው ፍትህን እንዳሰጣቸው ሲለምኑኝ ከማፅናናት ውጪ የምለው ባጣ ሀገር ይስማው… ለፍትህ እንጩህ አልኩ።
ፍትህ ለአሚራ!!!!!!
( ፎቶው የአሚራ የጀርባ ምስል ነው)

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on August 10, 2015
  • By:
  • Last Modified: August 10, 2015 @ 7:46 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar