0
0
Read Time:30 Second
በግሩም ተ/ሀይማኖት
የመንኑ አማጺ ሚኒሻ…5 ኢትዮጵያዊያንን ለሳዑዲ አረቢያ ሲሰልሉ ያዝኩኝ ይላል። ከዚህ በፊትም ከአልቃይዳ ጋር አብረው የተሰለፉ ኢትዮጵያዊያን አሉ በማለት ገልጸው ነበር። በእርግጥም ጥቂቶችን የየመንዋ ሁለተኛ ዋና ከተማ አደንን ለመቆጣጠር በዘመቱበት ወቅት ልጆቹን አግባብተው ወደ እነሱ እንዳስገቧቸው ተነግሯል።
የሁቲ ባለስልጣኖች ለአልመናር የሉብናን ቴሌቪዥን በስጡት መረጃ መሰረት ከሳዑዲ የተሰጣቸውን የሽብር ተልዕኮ ለመፈጸም ጥቃት ሊያደርሱ ወንዶቹ እንደሴት ለብሰው ሲንሳቀሱ በቁጥጥር ስር አዋልናቸው ብለዋል።
በግል ባለኝ መረጃ መ�ሰረት ከየመን ወደ ሳዑዲ ድንበር ጥሰው የሚገቡት በዚህ አይነት የሴት ልብስ ለብሰው ነው። በቅርቡ በሳዑዲ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻም እንዲሁ ለብሰው ተይዘዋል። የሉብናኑ አል-መናር ቲቪ ቦታውን በትክክል ባይናገርም ሳፊያ ከተባለው ቦታ መያዛቸውን ተናግሯል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating