Tamiru geda
ታዳጊዋ ህጻን ጽንሱን በጊዜ ማቋረጥ ወይስ መውለድ ነበረባት ?
በማከላዊ አሜሪካ( ፓራጓይ) ውስጥ ነዋሪ የሆነችው ሰሟ ለጊዜው ያልተጠቀሰው የ 10 አመቷ ጨቅላ ባለፈው ሚያዚያ ወር ከፍተኛ የሆድ ቁርጠት ሰሜት ሲሰማት ችግሯን ለወላጅ እናቷ ትናገራለች። ወላጅ እናቷም በአቅራቢያቸው ከሚገኝ አንድ ሆስፒታል ይወስዷታል። ዶክተሮቹም ለራሳቸውም ሆነ ለእናቷ እና ለጨቅላ ለጃቸው አንድ የለጠበቁት መርዶ ያረዷቸዋል። እርሱም ያቺ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰች እምቦቃቅላ ልጃቸው በማህጸኗ ወስጥ ጽንስ መቋጠሯን ነበር። እሺ ጽንሱስ ተጸነሰ ይባል የጽንሱ አባትስ ማን ነው? የሚለው ጥያቄ ሌላኛው ጥያቄ ነበር ። ልጅቷ የጸነሰችው ከ42 አመቱ የእንጀራ አባቷ መሆኑ በህክምና ምርመራ ሲረጋገጥ ሌላኛው ዱብ እዳ ነበር። የእንጀራ አባትየውም በህግ ጥላ ስር ወድቆ ፍርዱን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል.።
“ልጄ ከባለቤቴ እና ከ እንጀራ አባቷ መጸነስ የለባትም” ያሉት ወላጅ እናት ጨቅላ ልጃቸው ጽንሱን እንደታቋርጥ ለህክምና ባለሙያዎች ጥያቄ ቢያቀርቡም በ ፓራጓይ ህግ ጽንስ የሚቋረጠው የጸንሱ መኖር ለእናትየው ጤነነት አስጊ መሆን ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነ እና ጽንሱም በወቅቱ የ 22 ሳምንት እድሜ ማስቆጠሩ ነገሮችን ውስብሰብ እንደሚያደረጋቸው እና ጽንሱን ማቋረጥ እንደማይሞከር የነገራቸዋል ።የ33 አመቷ ወላጅ እናቷም ቢሆኑጉዳዪን ለፖሊስ ይፋ አድርጌ ነበር ቢሉም አንዳንድ ዘገባዋች ግን ወሬውን ለፖሊስ ሹክ ያሉት ወላጅ እናቷ ሳይሆኑ ጎረቤቶች ናቸው ያላሉ ። ያም ሆነ ይህ ግን እናትዪው ከተጠያቂነት አላመለጡም ። “በግድ የለሽነት ባህሪያቸው” ከ አቃቢ ህግ ክስ ቀርቦባቸው በዋስትና ተለቀዋል ። ለጅቷም ያለፈላጎቷ የጸነሰችው ጽንሱን ባለፈው ሃሙስ በህክምና ባለሞያዎች እገዛ በሰላም ተገላግላለች ተብሏል ።
ታዲያ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የመደፈር ጥቃት የደረሰባት ጨቅላዋ ህጻን ጸንሱን በህክምና እገዛ ማቋረጥ ሲገባት፣ በህግ ሽፋን ያለፍላጎቷ እንድትወልደው መደረጉ በእርሷ አካላዊ ፣ሰነልቦናዊ እና የሰበአዊ መብት ላይ የተፈጸመ ታላቅ ግፍ ነው በማለት የአገሪቱ መንግስት ህግ እና እርምጃውን በጽኑ ኮንነዋል። አንዳንድ የአሜሪካ እጩ ሪፐብሊካን ፓርቲ ፕሬዚዳንታዊ ተመራጮችም “ጽንስ ማቋረጥ ተገቢ አይደለም” ሲሉ የ11 አመቷን ጨቅላ ገጠመኝን ሰሞኑን አንስተዋል። እንደ የተባበሩት መንግስታት ዘገባ በላቲን አሜሪካ ውስጥ እድሜያቸው ከ 16 አመት በታች የሆኑ ልጃገረዶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ የመሞታቸው እጣ በ አራት እጥፍ ከፍ ብሎ ይገኛል።በ 2013 አኤአ የወጣ ጥናት እንዳተተው ከሆነ በአለማችን ላይ እድሜያቸው ከ 14 አመት በታች የሆኑ2 ሚሊዮን ልጃገርዶች በድ ምክንያት ፋየጤንነት አደጋ ይጋለጣሉ። ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ 70,000 የታዳጊ አገር ሴቶች እንዲሁ በአመት ወስጥ ከወልድ ጋር በተነካካ ችግር ህይወታቸውን ያጣሉ።
Average Rating