bush sirag fergesa and samora
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በከፍተኛ ስብሰባ ላይ መጠመዳቸውን ከቦታው ያገኘነው መረጃ አስታወቀ።በአዲስ አበባ ከተማ ከሃምሌ 25 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ በከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ሳሞራ የኑስና ሲራጅ ፈርጌሳ ስብሰባ መካሄዱና በስብሰባው እንደመወያያ ርእስ ሁኖ የቀረበውም አዲስ ሰራዊት ቢጨመርም አብዛኛው የሚፈርስና የሚበታተን በመሆኑ አሁንም የሰራዊቱ ይዘት አነስተኛ ነው። እናንተ ምን እያደረጋችሁ ነው? ለምንድነው የማትቆጣጠሩት የሚል እንደነበር መረጃው አስረድቷል። የክፍለ-ጦሮች አመራሮች የቀረበላቸውን ጥያቄ መመለስ እንዳልቻሉ የገለጸው መረጃው ስብሰባው ወደ ታች በመስመራዊ መኮነን ደረጃ ወርዶ በተለይ ከሻንበል በላይ በተደረገው ስብሰባ ላይ የሰራዊቱ መፍረስ ምክንያት በከፍተኛ የሰራዊቱ አዛዦች ውስጥ ብልሹ አሰራር፤ ወገናዊነትና አድልዎ በመኖሩ ነው ብለው መናገራቸው ተገልጿል። መረጃው በማከልም- የበላይ የሰራዊቱ አዛዦች ከተራ ወታደሮችና የበታች የሰራዊቱ አዛዦች የነጠቁትን ገንዘብ የግል ኑሮአቸውን እያመቻቹበት ነው ተብሎ በስብሰባው በተነገረበት ግዜና የተሰጠውን ሃሳብ ተከትሎ የድጋፍ ድምፅ በተሰማበት ወቅት የመድረኩ መሪዎቹ ድንጋጤና ፍርሃት እንደተሰማቸውና በከባድ ስጋት ላይ በመውደቃቸው ምክንያት አመራሮቹ ስብሰባውን ለማካሄድ መቸገራቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating