0
0
Read Time:43 Second
የአሜሪካው ኤቤሲ ቴሊቭዥን እህት ኩባንያ ለሆነው የቨርጂኒያው WDBJ7 ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ የሆነችው የ 24 አመቷ አሊሰን ፓርከር ወደሌላ ድርጅት ለመዛወር እድል በማግኝቷ ከ WDBJ7 ጋር የመጨረሻዋ ሰራዋ የሚሆነውን የዛሬው የቀጠታ(live) ቃለምልልስ ነበር ።ይሁን እንጂ አሊሰን ከባልደርባዋ (ምስል ቀራጩ) አዳም ዋርድ ጋር በስራ ተጠምደው ሳሉ በአንድ ወቅትለአጭር ጊዜ የሰራ ባልደረባዋ በነበረው በሁዋላም ከሰራው በተባረረው የ41 አመቱ ቬስታር ፈላንግስተን በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው አልፏል። ቃለምልልስ ሲደረግላቸው የነበሩት እንግዳም ቆሰለዋል ።ገዳዩ ቬስታር እርምጅውን የወሰደው በጥላቻ ሰሜት ተነሳስቶ መሆኑን በቲዊተር እና በፊስ ቡኩ ላይ ጠቅሶ የራሱን ህይወትም ማጥፋቱ ተገልጻል ።እዚህ ላይ ይሄ አሳዛኝ ድርጊት ሲፈጠር የአሊሰን እጮኛ እና ዜና አቅራቢ የሆነው ክሪስ እና የተቀሩት የእለቱ ተረኛ ባልደረቦች በሙሉ ደርጊቱን ከስቱዲዮ በቀጥታ የመለከቱ ነበር። ሃዘኑንም አስደንጋጭ እና ድርብ ድርብርብ አድርጎታል።የተሊቪዠኑ ጣቢያው ሃላፊ የሆኑት ማርክም “ጋዜጠኞች ወደ ጦር ሜዳ ሲላኩ አደጋ እንዳይገጥማቸው ትሰጋለህ ፣እንደዚህ አይነቱ ክስተትን ግን እንዲት እናምናለን?”በማለት ሃዘናቸውን እና ድንጋጤያቸውን ገልጸዋል።ነፍስ ይማር!!!
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating