በኢትዮጵያ ውስጥ ታዲያስ አዲስ በሚለው ልዩ ፕሮግራሙ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን እና ቬሮኒካ በዛሬው እለት ጋብቻቸውን በሸራተን ሆቴል ማከናወናቸው ተገለጸ ፣ለረጂም አመታት ሲታቀድ የነበረው እና በድብቅ ማንነቷ ሳይታወቅ ሰይፉ ፋንታሁን ሊያገባ ነው ሲባልላት የነበረችው ወጣት ቬሮኒካ በዛሬው ዕለት በግላጭ ለህዝብ እንድትታይ በቅታለች ።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ አስተናጋጅነት ትሰራለች የተባለችው ቬሮኒካ የወደፊት የህይወት አጋሬን መርጫለሁ በማለት ከመድረክ ተዋናይ ጋዜጠኛ የቶክ ሾው እና የራዮ ፕሮግራም አዘጋጅ እና አስተባባሪውን እንዲሁም በተለያዩ የቴሌቪዢን ፕሮግራም በማስተዋወቅ የሚታወቀውን እና በቀልድ ጨዋታዎቹ እጅግ የሰው ቀልብ ውስጥ የገባውን ሰይፉ ፋንታሁንን ማግባቱዋን አረጋግጣለች ።
ሰይፉ ፋንታሁን ከዚህ በፊት የጋብቻ ጥያቄ ለኮኒያቸው ለተባለች ወጣት በአትላንታ ከተማ ያቀረበ የነበረ ሲሆን እና በወቅቱ ህዝብን አስደስቶ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት የእጮኝነት ጉዳያቸው ፈርሶ መለያየታቸውን የማለዳ ታይምስ ከዚህ ቀደም መዘገባቸው አይረሳም ሆኖም ግን በዛሬው እለት ከመሞሸሩም ባሻገር የተወለደበት እለት በመሆኑ በአሉን ድርብ ያደርገዋል ሲል ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ይገልጻሉ ።

seifu fantahun ena veronica
መልካም ጋብቻ ለሰይፉ ፋንታሁን እና ቬሮኒካ ሲሉም አክለው መልካም ምኞታቸውን ያስተላልፋሉ
ቪዲዮውን ለማየት ይህንን ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
Average Rating