Read Time:1 Minute, 39 Second
Dawit Solomon
—
የተባበሩት መንግስታት በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት 4.5 ሚልዩን የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን በአገሪቱ በተከሰተ ድርቅ ምክንያት የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው መግለጹ አይዘነጋም፡፡
እንደ ሪፖርቱ በድርቁ በከፍተኛ ደረጃ የተጠቁት የአገሪቱ ክፍሎች የአፋር ምስራቅና የደቡብ ሱማሌ ክልሎች ናቸው፡፡ ባልተለመደ ሁኔታም በመካከለኛ የምስራቅ ኦሮሚያ፣በሰሜን ትግራይና አማራ ወረዳዎች የውሃ እጥረት መከሰቱም ተስተውሏል፡፡
ሁኔታው በዚህ መንገድ የሚቀጥል ከሆነም የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር በዚህ አመት 55 ከመቶ ሊጨምር ይችላል እየተባለ ቢሆንም የእርሻ ሚኒስትር ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ አለማየሁ ብርሃኑ ለአልጀዚራ በሰጡት ቃል ‹‹ለአደጋ ጊዜ የተዘጋጀ በቂ የምግብ ክምችት አለን በአሁኑ ወቅት በማከፋፈል ላይ እንገኛለን››ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
አለማየሁ አክለውም ‹‹ስለችግሩ መረጃ እንደደረሰን የፌደራልና የክልል መንግስታት በችግሩ ለተጠቁት ሰዎች ምግብ ማከፋፈል ጀምረዋል››ብለዋል፡፡
በነሐሴ ወር የኢትዮጵያ መንግስት በኤል ኒኖ ምክንያት በተከሰተ የአየር ጸባይ ቀውስ የሚፈጠረውን ድርቅ ለመታደግ 35 ሚልዮን ዶላር መመደቡን ተናግሮ የነበረ ቢሆንም የተባበሩት መንግስታት 230 ሚልዮን ዶላር ቀውሱን ለመታደግ በአመቱ መጨረሻ እንደሚያስፈልግ ይፋ አድርጓል፡፡
በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዴቪድ ዴል ኮንቴ ‹‹የዝናብ መጥፋት ማለት ተክሎች አይኖሩም፣ሳር አያድግም ስለዚህ ሰዎች እንስሳቶቻቸውን መመገብ አይችሉም ››ይላሉ፡፡
በዝዋይ አቅራቢያ የሚኖር አንድ ገበሬ ለአልጀዚራ በህይወት ለመቆየት ሲል የግል ንብረቶቹን መሸጡን ተናግሯል፡፡‹‹ምንም ማድረግ የምንችለው ነገር የለም ፡፡››የሚለው ገበሬው ‹‹ቤተሰቦቻችንን ለመመገብ የሚያስችለን ነገር የለም፡፡ምግብ ለመግዛት እንስሳቶቻችንን መሸጥ ይኖርብናል፡፡ነገር ግን በቂ ምግብ ባለማግኘታቸው የተነሳ ከብቶቻችን ታመዋል››የሚለው የዘጠኝ ቤተሰብ አስተዳዳሪ የሆነው ባልቻ ነው፡፡
በኤል ኒኖ መንስኤ በተዛባው የአየር ጸባይ ከሰኔ እስከ መስከረም ወር የነበረው የዝናብ መጠን እጅግ በጣም አነስተኛ ነበር፡፡እንደ ዩኒሴፍ ገለጣ ከሆነም የዘንድሮው ኤል ኒኖ በ20 ዓመታት ውስጥ ከተከሰቱት እጅግ በጣም ኃይለኛው ነው፡፡
ከግብርና በሚገኝ ገቢ የአገሪቱን አመታዊ ገቢ በግማሽ ለምትሸፍን አገር ኢኮኖሚ ድርቁ ከፍተኛ ችግር እንደሚደቅን ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡የአየር ጸባይ ለውጥ በኢትዮጵያ እንደ አዲስ ክስተት አይታይም፡፡እንዲህ አይነት ችግሮች በተከሰቱ ቁጥርም የሚደርሱት ጉዳቶች ከፍተኛ ሆነው ሲመዘገቡ ቆይተዋል፡፡
በአጠቃላይ በአገሪቱ ከሚገኙ እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች ከሆኑ ህጻናቶች 44 ከመቶ ያህሉ የተመጣጣኝ ምግብ እጥረት የሚያጋጥማቸው ሲሆን 28 ከመቶ ያህሉ የክብደት መጠናቸው አነስተኛ ስለመሆኑ ሲአይኤ ባወጣው ፋክት ቡክ አስፍሯል፡፡
ዩኒሴፍ በበኩሉ በ2015 የተመጣጣኝ ምግብ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህጻናት ቁጥር 264.515 ቢሆንም ከጥር አስከ ግንቦት ባሉት ወራቶች ድጋፉን ማድረግ የተቻለው ለ111.076 ያህሉ ብቻ መሆኑን አትቷል፡፡

Average Rating