www.maledatimes.com “የአመቱ ታላቅ በጎ ስራ” - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“የአመቱ ታላቅ በጎ ስራ”

By   /   September 7, 2015  /   Comments Off on “የአመቱ ታላቅ በጎ ስራ”

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 28 Second

//እስኪ አመስጉንልኝ ቴዲ ተሾመ ከOBS TV ጋር በመተባበር ለአንድ ግለሰብ ማሳከሚያ 400000 ብር በመስጠት ሌላ ታሪክ ሰራ//
ትላንት እሁድ ከጠዋቱ 5:00 ሰአት በቦሌ ዮድ አቢሲኒያ እንድገኝ አንድ እጅግ የማከብረው እና የማደንቀው ሰው በስልኬ ደውሎ ጠራኝ።
መቼም ብዙዎቻችን የሸገርን የታክሲ ግፊ ጠንቅቀን እናውቀዋለን።
እኔም ከብዙ የታክሲ ግፊ እና የታክሲ መጨናነቅ በኋላ ቦሌ ወደ ሚገኘው ዮድ አቢሲኒያ ገባሁ።
ወደ ውስጥ ስገባ ግን አይኔ የተመለከተውን ነገር ማመን አቃተው።
የምር ነው የምላችሁ ከውስጥ እንደደረስኩ እጅግ ተደነኩኝ፣ተገረምኩኝ ዮድ አቢሲኒያ የባህል አዳራሹ በሜሪ ጆይ የልማት ማህበር ተረጂዎች አረጋውያን እና ህፃናት ጢም ብሎ ተሞልቷል በርካታ የጥበብ ሰዎችም ከአረጋውያን እና ከህፃናት አብረው ታድመዋል።
እነዚያ ምስኪን የእኔ ቢጤ አረጋውያን እና ህፃናት እዚህ ቤት ውስጥ መገኘታቸው ትልቅ ደስታ እንደሰጣቸው ከበርካቶች ፊት ማንበብ ችያለሁ።
የእለቱ ፕሮግራምም የሜሪ ጆይ የልማት ማህበር አረጋውያንን እና ህፃናትን እጅ በማስታጠብ እና ምሳ በማብላት ተጀመረ።
እኔ እነ ቴዲ ተሾመን እና ሌሎች ስመ ጥር አርቲስቶችን በእጅጉ ያደነኩበት እለትም ይህ እለት ነበረ ከምስኪኖች በታች ዝቅ ማለት ምን ያህል መታደል እንደሆነም ተመልክቼበታለሁ።
ከምሳ በኋላ የእለቱ ፕሮግራም በኮሜዲያን እና መድረክ መሪ በጥላሁን እልፍነህ ተጀመረ።
ጥላሁን አረጋውያኑን እና ህፃናቱን በዮድ አቢሲኒያ ባንድ ታጅቦ ዘና ሲያደርግ ከቆየ በኋላ እጅግ ልዩ እና ጣዕመ ዜማ ያላቸው ሙዚቃዎች ቀርበው አረጋውያኑ እና ህፃናቱ የናፈቁትን ደስታ መድረክ ለይ ወጥተው መግለፅ ለመቻል በቅተዋል።
ኧረ እንደውም በድህነታቸው ምክንያት ተደብቆ እና ተረስቶ የነበረ የሙዚቃ ችሎታቸውን ያወጡ እና ታዳሚውን ያስደመሙ ሰዎችም አልታጡም።
የምር ትላንት እነ ጌትሽ ማሞም ለአረጋዊያን የነበራቸውን ፍቅር በተግባር ማሳየት ችለዋል።
በመቀጠል ንግግር እንዲያደርግ መድረክ ለይ የተጋበዘው አርቲስ ሰለሞን ቦጋለ ሲሆን።
ለአረጋውያኑ እና ለህፃናቱ ታስቦ እንደዚህ አይነት የምሳ ፕሮግራም መዘጋጀቱ እጅግ እንዳስደሰተው ከተናገረ በኋላ
ስለ ትግስት እና ስለ አላዛር ጉዳይም ተጠይቆ ነበር።
ትግስት በአሁን ሰአት ደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ሲሆን ማክሰኞ ኦብሪሽን ስለምትደረግ እና ቀጣይ ማክሰኞ ወደ ሀገሯ ኢትዮጵያ ስለምትመለስ ይህ ከጎናችን የነበረው ህዝብ ፀሎት እንዲያደርግላት ጠይቋል።
በተጨማሪም የአላዛር የመኪናው ጫራታ ጉዳይ አዳራሽ በማጣት ምክንያት ቢራዘምም እና አሜሪካ ያሉ ሆስፒታሎች ቪዛ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆን ባይችሉም አሁንም ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ተናግሯል።
ሌላው ለሜሪ ጆይ የአረጋውያን እና ህፃናትም በኪሱ የነበረችዋን 1000 ብር ሰጥቷል።
በመቀጠልም አረጋውያኑ ምሳ በልተው እና ተደስተው ብቻ መሄድ የለባቸውም ለበአል መዋያም ያስፈልጋቸዋል ብለው ያሰቡ አካላት ለሁሉም አረጋውያን አንድ አንድ ሺ ብር የባል መዋያ አበርክተዋል።
ይሄን ዝግጅት በዋነኝነት ያዘጋጁት OBS TV መስከረም 1የእንቁጣጣሽ እለት ቀጥታ ስርጭቱን የሚጀምረው የቴሌቭዥን ሾው እና ቴዲ ስቱዲዮ ናቸው፣ዮድ አቢሲኒያ ደግሞ ቤቱን እና የምሳውን ወጪ ሙሏ ለሙሉ ሸፍኗል።
በነገራችን ለይ መስከረም 1 የሚጀምረው OBS TV ልዩ ትኩረቱ በአረጋውያን እና በምስኪን ወገኖቻችን ለይ ያደረገ የቴሌቭዥን ፕሮግራም መሆኑ የበለጠ አስደስቶኛል።
የመክፈቻ ፕሮግራሙንም ለየት ያደረገው በአረጋውያን መመረቅ መቻሉ ሲሆን ትላንት የነበረውን ማራኪ ዝግጅት በአዲስ አመት በቤትዎ ሆነው በአዲስ ቻናል OBS TV ይመልከቱት።
የዝግጅቱ ተባባሪ አካላት የነበሩትም
አጎና ሰራዊት ሲኒማ
ሴባስቶፖል ሲኒማ
ሬፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ
አብርሀም ግዛው ኢንተርቴይመንት
ሰይፉ ፋንታሁን
እና ሌሎችም ለሜሪ ጆይ እና ለአረጋውያኑ የገንዘብ ስጦታ አበርክተዋል።
ልብ አርጉልኝ ሰጥተዋል ነው እንጂ ቃል ገብተዋል አላልኩም።
ብቻ በእዚህ አጋጣሚ ይሄን ዝግጅት ያዘጋጁትን በሙሉ ሳላደንቅ እና ሳላመሰግን አላልፍም!ለነገሩ ይሄን ሀሳብ እንዲያስቡ የረዳቸው ፈጣሪ ይመስገን እና በአረጋውያኑ መመረቅ መቻላቸው እራሱ ትልቅ ፀጋ ነው።
የሜሪ ጆይ አስተባባሪ የሆነችዋ ወጣት አዲስ ህይወት አበበ ሁሉንም አካላት በእጅጉ አመስግናቸዋለች።
በተጨማሪም ሜሪ ጆይ የልማት ማህበር በ21 አመት ቆይታው ለ56 ሺ ህፃናት ለ42 ሺ አረጋውያን ተደራሽ መሆን ችሏል።አሁንም በሀዋሳ ከተማ እየገነባው ላለው የአረጋዊያን መጠለያ ምርቃት ሁሉም ሰው እንዲሳተፍ ከቻለም እንደ መፅሀፍ፣ወንበር፣አንሶላ፣ብርድ ልብስ፣አልጋ የመሳሰሉት የማይፈለጉ ቁሳቁሶች ያለው ሁሉ በመስጠት ቢተባበረን ስትል ጥሪዋን አስተላልፋለች።
ከቆይታ በኋላ ግን አዳራሹ በሀዘን እና በለቅሶ ድባብ ተሞላ ሰለሞን ቦጋለ ሶስት አረጋውያን አንድ አንድ ጥያቄ እንዲጠይቅ እድል የሰጠው ቴዲ ተሾመ ሲሆን ሰለሞን ከአረጋውያኑ መሀል በመሆን ጥያቄ መጠየቅ ጀመረ ለሶስት ሰዎች በመጨረሻ ግን ተጠያቂ የነበረችዋ በቅርቡ በሜሪ ጆይ የተቀላቀለችዋ አካል ጉዳተኛ አንድ እህታችን ነበረች ይች እህታችን የአንድ ሴት ልጅ እናት ስትሆን የእግሯ ህመም ሰላሟን ከነሳት ሰኘባብቷል።
ህመሟ ግን እዚህ መዳን እንደማይችል ተነግሯት ፈጣሪዋን በማማረር እና ሌት ተቀን በማልቀስ ለይ ነበረች።
የ7 አመት ልጁአን ሜሪ ጆይ ቢያስተምርላትም ህመሟኔ ግን ለማዳን ሀቅም በማጣቱ ምክንያት ዘግየት ብሎ ቢቆይም
ትላንት ሰለሞን ቦጋለ ቃለ መጠየቅ እያደረገላት አዳራሹ በሙሉ በሀዘን ተመላ ሁሉም ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት አመሸ።ሰለሞን እንደምታውቁት ሆዱ ቡቡ ነው ጭራሽ ማውራትም አልቻለም እንባ ቀደመው ያች ምስካን ሴት እና ሰለሞን አልቅሰው ሁሉንም አላቀሱት።
ቴዎድሮስ ተሾመም ሌላ ታሪክ ሰራ ከOBS TV ጋር በመተባበር ተጠይቃ የነበረውን የህክምናዋን ወጪ 400000 ብር ሸፍኖ ለማሳከም ወሰነ።
ይህን ሲናገር ቴዲ እንባ እየተናነቀው ነበረ።
ብቻ የትላንቱን የዮድ አቢሲኒያውን ዝጎጅት የአመቱ መጠናቀቂያ ታላቅ በጎ የተደረገበት ልዩ እለት ብዬዋለሁ።
ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን!
እናንተ የሀገሬ ሰዎች ለታናሾቻችሁ ትልቅ ክብር ሰጥታችኋል እና ክበሩልን!

ዋልተንጉስ ዘሸገር

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on September 7, 2015
  • By:
  • Last Modified: September 7, 2015 @ 9:35 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar