የትምህርት መቅሰም ነገር ሲነሳ ብዙዎቻችን ከ አይምሯችን ድቅን የሚልብን ያው ት/ቤት መግባቱ ላይ ነው። እውቀት ከመደበኛው ት/ቤት ባልተናነሰ ከቤት ፣ ከጎረቤት ፣ከአካባቢም ይቀሰማል።አበውም “መልኩን ሰጠኝ እንጂ እውቀቱንስ ከጎረቤቴ እማራለሁ” የሚሉት ለዚሁ ነው ።ታዲያ በዚህ ሃሳብ በከፊልም ቢሆን ከተሰማማን ፣ ምንም እንኳን ድርጊቱ አሳዝኝ ቢሆንም በሶማሌያ ከዘመተው የኡጋንዳ ጦር ሰራዊት ውስጥ 12 የሚገመቱት ባለፈው ማክሰኞ ጠዋት በ አልሽባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን ተከትሎ የኡጋንዳ መከላከያ ባለሰልጣናት ከኢንቴቤው አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ አቅራቢያ ከሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ የሟቾቹ ወታደሮች አስክሬናቸውን በወታደራዊ አጀባ እና በልዩ ክብር በመቀብል ፣ የተሰማቸውንም ሃዘንን በመግለጽ እና የሞቱቱንም ዘማቾች ሰም ዝርዝርን ለህዝባቸው በአስቸኳይ ይፋ እንደሚያደርጉ ቃል በመግባት ፣የሟቾች ቤተሰብንም እንደሚያጽናኑ እና አገሪቱም በቀጣይነት በሶማሊያ ጉዳይ ምን እንደምታደርግ አቋሟን ገልጸዋል። የመገናኛ ብዙሃናቷም ቢሆኑ ያለ አንዳች ክልከላ ይህነኑ መጥፎ ገጠምኝን ከጅማሪው ኣስከ መጨረሻው በምስል አስደግፈው ለአለም ሕዝብ አቅርበውታል ።
ታዲያ እንደ ኡጋንዳ ሁሉ በሺህ የሚቆጠር ሰራዊቱን ወደ ሶማሊያ ያሰማራው የኢሕአዲግ መንግስት ሰለሰራዊቱ የጦር ሜዳ ውሎዎች እና አዳር ከዚህ ቀደም ከተለያዩ ጋዜጠኞች ሆነ ከፓርላማ አባላቱ ሳይቀር ጥያቄዋች ሲቀርቡልት ”ዝም በሉ፣ አያገባችሁም “ የሚሉት ጆሮ ዳባ ልበስ ምላሾቹ ግልጽነት እና ለሕዝብ ተጠያቂነት የቱ ጋር ነው? ጦርነቱ፣ ወድቀቱ ሆነ ገድሉ የማነው? ለሚሉ ጥያቄዎች ሰፊ በር ይከፈታል ። አንዳንዴ ከ ደካማ ጎረቤትም ቢሆን መማሩ አይከፋም ።በዚህ አጋጣሚ ኡጋንዳዎች መነሻው ሆነ መድረሸው ምንም ይሁን ምን በግልጽነታችሁ ልትኮሩ ይገባል ። ነፈስ ይማር።
Average Rating