www.maledatimes.com ጦማሪያኑ ለአራተኛ ጊዜ ለብይን መቀጠራቸውን ተቃወሙ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጦማሪያኑ ለአራተኛ ጊዜ ለብይን መቀጠራቸውን ተቃወሙ

By   /   September 9, 2015  /   Comments Off on ጦማሪያኑ ለአራተኛ ጊዜ ለብይን መቀጠራቸውን ተቃወሙ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 4 Second

9f63d0258a66cac66fe763a18892b271_L‹‹አንድ ዳኛ ምንም ማድረግ አይችልም›› ዳኛ ዘሪሁን ደሳለኝ

‹‹ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል›› በእስር ላይ ያሉ ጦማሪያን

በተጠረጠሩበት የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸው በኋላ የከሳሽ ዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ቀርቦባቸው ለብይን የተቀጠሩት አራት ጦማሪያን፣ ለአራተኛ ጊዜ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ተቃወሙ፡፡

ተከሳሾቹ ጦማሪያን ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፍ ብርሃኔና በፍቃዱ ኃይሉ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ብይን እንደሚሰጥ የጠበቁ ቢሆንም፣ ጉዳያቸው በሦስት ዳኞች የሚታይ ከመሆኑ አንፃር በዕለቱ አንድ ዳኛ አቶ ዘሪሁን ደሳለኝ ብቻ የተገኙ በመሆናቸው ብይኑ ሳይሰጥ ቀርቷል፡፡ ብይኑ ተሠርቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ ዳኞች ባለመሟላታቸውና በመዝገቡ ላይ ባለመፈረማቸው ብይኑ ሊነገር እንደማይችል ዳኛ ዘሪሁን ገልጸዋል፡፡

በዳኞች አለመሟላት ለሁለተኛ ጊዜ መቀጠሩ ያበሳጫቸው ተከሳሾቹ፣ ‹‹እኛ ከዳኞች ጋር ምንም ችግር የለብንም፡፡ ከማን ጋር እንደተጣላን ገብቶናል፡፡ የምንፈልገው ቁርጥ ያለው እንዲነገረን ነው፡፡ ወይ በነፃ እንሰናበት ወይም ተከላከሉ እንባል፡፡ ብይን ለመስጠት በሚቀጠሩት ቀናት መካከል ያለው ጊዜ ለእኛ ሕመም ነው፤›› በማለት ቅሬታቸውን ተናግረዋል፡፡

የጦማሪያኑ ጠበቃ አቶ አመሀ መኰንን ‹‹ዳኞች እንዲሟሉ መተባበር ያለብን ነገር ካለ እንተባበር ወይም ለፍርድ ቤቱ አስተዳደር እናመልክት፤›› የሚል ሐሳብ ለዳኛ ዘሪሁን አቅርበዋል፡፡ ዳኛው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹የሚቻል ከሆነ ሞክሩ፤›› ብለዋል፡፡ እሳቸውም ብይኑ ቢሰጥ እንደሚመርጡ፣ ተጠርጣሪዎቹን ዓይናቸውን ባያዩ ደስ እንደሚላቸውና (በተደጋጋሚ በመመላለሳቸው) በግላቸው እንደሚከብዳቸው ተናግረዋል፡፡

ያልተሟሉት ዳኞች በተለያዩ ምክንያቶች መቅረታቸውን በመጠቆም፣ እንደተሟሉ እስከ መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ለማረሚያ ቤቱ ተነግሮ ብይኑ ሊሰጥ እንደሚችል በጽሕፈት ቤት አስታውቀዋል፡፡

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on September 9, 2015
  • By:
  • Last Modified: September 9, 2015 @ 12:20 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar