====================================
* ከ100 በላይ ሞተዋል ፣ ከ200 በላይ ቆስለዋል
* በኢትዮጵያውያን ላይ ጉዳት አልደረሰም
የአረብ መገናኛ ብዙሐን መረጃዎች በአደጋው ዙሪያ …
=================================
መካ ውስጥ በሚገኘው በታላቁ የካዕባ መስጊድ የህንጻ መስሪያ ክሬን ወድቆ ወደ 100 የሚጠጉ መሞታቸው ሲዘ ገብ ከ 200 በላይ ጸሎተኞች መቁሰላቸው ተጠቁሟል ! ጉዳዩ ተጠርቶ በይፋ እስኪታወቅ የአረብ መገናኛ ብዙሃን የሚሰጡት መረጃ እንደየ ምንጮቻቸው የተለያየ ሆኖ ተስተውሏል … ያም ሆኖ እስከ ንጋት ያሉትን መረጃዎች መሰረት በማድረግ በዛሬው የማለዳ ወግ አንኳር አንኳር መረጃዎችን እንመለከታለን!
በአደጋው የሞቱ የቆሰሉት ቁጥር …
=======================
የሞቱትን ሰዎች በሚመለከት አደጋው ከተፈጠረ ጀምሮ የሚወጡት ቁጥሮች የተለያዩ ሆነው ተስተውሏል ። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከታዋቂ የሳውዲ ታዋቂ ጋዜጦች መካከል አረብ ኒውስ #arabnews የሞቱት ቁጥር 87 ፣ የቆሰሉት 201 መድረሳቸውን ሲያደርሰው ሳውዲ ጋዜጥ #saudigazette በበኩሉ የሞቱት 107 የቆሰሉት 238 መድረሱን ዘግበዋል ። የአልአረቢያ በበኩሉ የሞቱት ቁጥር ከ100 ከፍ እያለ መሆኑና የቆሰሉትም ከሁለት መቶ ማሻቀቡን ጠቁሟል ! እየተሰማ ነው ።
የአደጋው መንስኤ…
=============
አርብ ጳግሜ 6 ቀን 2007 ዓም ከምሽቱ 5:10 pm ገደማ የተከሰተው አደጋ መንስኤ በኮረብታማዋ ቅዱስ ከተማ የጣለውን ከፍተኛ ዝናብና ነፋስ 400,000 ስኩየር ሜትር ለሚያካልለው የመካ ማስፋፋት ስራ በተዘረጋ ግዙፍ ክሬንን አናግቶት መውደቁ እንደ ዋና ምክንያት ይጠቀሳል። አደጋው በመላ ሀገሪቱና በመካከለኛው ምስራቅ በያዝነው ሳምንት የተከሰተውን የአቧራ ማዕበል ተከትሎ የጣለው ከባድ ዝናብ ከመላ አለምና ከሀገር ውስጥ ለአመታዊው የሐጅ ጸሎት የተሰባሰቡ ሙስሊም በመቶ ሽዎች የሚገመቱ ሙስሊም ምዕመናን በተሰባሰቡበት አጋጣሚ መከሰቱ ብዙዎችን አስደንግጧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የመካው አሚር ልዑል ካልድ አል ፈይሰል በአደጋውን ቦታ የጎበኙ ሲሆን የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ በአስቸኳይ እንዲጣራ አዘዋል ። የመካ ዙሪያ የአደጋ ጊዜ ተወርዋሪ ግብረ ሀይል በተጠንቀቅ እንዲዘጋጅ ሲታዘዝ ፣ የህክምና ጣቢያዎችም ቀይ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ምልክትን ከፍ በማድረግ የተጎዱትን በመርዳት አስፈላጊውን ጥረት እንዲያደርጉ ታዘዋል !
በአደጋው የተጎዱ ዜጎች…
=================
በአደጋው ከሞቱት መካከል የፖኪስታን የህንድና የባንግላዲሽ ዜጎች ይገኙበታል ። እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያውያን በአደጋው አልተጎዱም ! ከመካ የደረሱኝ ቪዲዮዎች በከበድ የጣለው ዝናብ አውራ መንገድ መኪኖችን ለማስተላለፍ ሲያስቸግር ተመልክቻለሁ ! በአደጋው የሞቱት ቁጥርና ዜግነታቸው ጭምር በቀጣይ እየተጣራ ይፋ እንደሚሆን የሳውዲ መንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች አስታውቀዋል።
ስለአደጋው መግለጫ የሰጡት የቅዱስ ቦታዎች ቃል አቀባይ ሀይለኛውን ዝናብና ንፋሱን ተከትሎ የወደቀው የህንጻ እቃዎችን አቅራቢ በመካከለኛው ምስራቅ በግዙፍ ነቱ ቀዳሚ የሆነው ይህ ክሬን ሲወድቅ የካብአን መስጊድ አንድ ክፍል መጉዳቱን አስረድተዋል። ጉዳት የደረሰበት ቦታ ሶፋና መርዋ Mount Safa and Marwa (mas’a) ተብሎ በሚታወቀው የመስጊዱ ክፍል ጸሎት ሲያደርሱ በነበሩት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
የመካ ካብአ መስጊድ ማስፋፋት ስራ …
=========================
የመካ ካዕባ ባንድ ጊዜ 2.2 ሚሊዮን ጸሎት አድራጊዎ ችን ለማስተናገድ ምቹ እንዲሆን ተብሎ ከአመታት በፊት የተጀመረው ማስፋፋት ስራ በሀገሪቱ ታሪክ እጅግ ግዙፍ ከሚባሉት ፕሮጀክቶች ቀዳሚ መሆኑ ይጠቀሳል። የ 400,000 ስኩየር ሜትር የሚሸፍን ማስፋፋት የመጨረሻ ምዕራፍ ስራ እስካሁን እንዲህ የከበደ አደጋ አልደረሰም ተብሏል ። አደጋው የደረሰበት መትሃፍ mataf ጸሎት ቦታ ለግንባታ ከተዘጋበት ስራው ተጠናቆ የተከፈተው አደጋው በደረሰበት ቀን መሆኑም ተጠቅሷል።
የግንባታው ተቋራጩ መረጃ …
====================
የመካ ካዕባን ማስፋፋት ግንባታ የሚያካሂደው ተቋራጭ የሳውዲ ቢላዲን ግሩኘ ም/ዳይሬክተር መሀመድ ሙኒብ በሰጡት መግለጫ ሰጥተዋል ። ባለስልጣኑ በመግለጫቸ ው የማስፋፋቱ ስራ ለሐጅ ጸሎተኞች እንዳያውክ በሚል በዋና ዳይሬክተር ነዋፍ በክር ቢላዲን ትዕዛዝ ከጽዳት ሰራተኞች ውጭ አብዛኛው ሰራተኞችና ስራው አደጋው ከመድረሱ ካንድ ቀን በፊት ስራ አቁመው እንደነበር ተናግረዋል።
የዘንድሮው ሐጅ ጸሎት …
==================
የሐጅ አመታዊ የጸሎት ሥነ ሥርአት እጎአ ሴፕቴምበር 21 ቀን 2015 ሊጀመር አስር ቀናት ነው የቀረው ። በዚህ ታላቅ የሐጅ ጸሎት ከ2 ሚሊዮን የሚደርሱ ምዕመናን ከመላ አለም ለመሳተፍ ወደ ሳውዲ በመግባት ላይ ናቸው ። ከሐጅ ተጓዦች መካከል ወደ 8 ሽህ ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ሳወዲ መካና መዲና መግባታቸው ከመካ የደረሰኝ መረጃ ያስረዳል ! ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች መግባት እንደጀ መሩ መጠነኛ የምግብ አቅርቦት ችግር ያጋጠማቸው መሆኑ በማህበራዊ ድህረ ገጾች የተሰራጨ ቢሆንም ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን መስተንግዶው የተሻሻለ መሆኑን መረጃዎች ደርሰውኛል ! በአደጋው ዙሪያ ያነጋገ ርኳቸው ሐጃጆች የመደናገጥ ስሜት የተፈጠረባቸ ው ሲገልጹ አሁን በተረጋጋ ስሜት ላይ እንደሚገኙ ገልጸውልኛል!
የሞቱትን ነፍስ ይማር ፣ የቆሰሉ የተጎዱትን ፈጣሪ በምህረቱ ይጎብኛቸው !
ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 1 ቀን 2008 ዓም
Average Rating