www.maledatimes.com ዘለቀ ገሠሠ:- ወደ ሃገሩ ሲመለስ ችካጎ “እፎይ… እፎይ…!” ተነፈሰች የተባለለት ቤዝ ጊታር ተጨዋች! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዘለቀ ገሠሠ:- ወደ ሃገሩ ሲመለስ ችካጎ “እፎይ… እፎይ…!” ተነፈሰች የተባለለት ቤዝ ጊታር ተጨዋች!

By   /   September 16, 2015  /   Comments Off on ዘለቀ ገሠሠ:- ወደ ሃገሩ ሲመለስ ችካጎ “እፎይ… እፎይ…!” ተነፈሰች የተባለለት ቤዝ ጊታር ተጨዋች!

    Print       Email
0 0
Read Time:17 Minute, 37 Second
  • እመቤት ጸጋዬ ከቺጋጎ

በዚህ በያዝነው ወር የመጀመሪያው ሳምንት ላይ የአዲስ አድማስ ጸሃፊ አቶ መንግስቶ አበበ የተሰኘው የአዲስ አድማስ የድህረ ገጹ እና የጋዜጣው አምደኛ በአንድ እውነታን ባልጨበጠ እና በሬ ወለደ አይነት የመንደር ወሬ ይዞ ብቅ ማለቱ አንዲቱን ብቻም ሳይሆን ግዙፉን አለም አስገርሞ አስደንግጦአልም። ይኸውም የነገሩ እውነታን ማጣት እና የበሰለ የወሬ ቅንብር አለመኖሩ ለዘመናት አዲስ አድማስ ያካበተውን ትልቁን ዝና በተለይም ከእነ አቶ አሰፋ ጎሳዬ ጠንካራ ጀርባ የነበራቸውንም ስራም ሆነ በነ ነብይ መኮንን ስልታዊ ጥበብ የነበረውን እድገት ይዞ በአንድ ጊዜ ወደ ከንቱ ጉድጓድ እንዲጠልቅ እና እንዲቀበር አድርጎታል ፤ምክንታያዊ ሁነቶቹ ምንድናቸው ተብሎ ቢጠየቅ ምርምራዊ ጋዜጠኝነት የጎደለው እና ስነ ምግባራዊ ሂደት ያልታከለበት የለብለብ ጋዘጠኛ ስራ ሆኖ መቅረቡ ሲሆን ምናልባትም ይህንን ስራ እንዲቀርብለት የፈለገው ግለሰብ በተወሰነች አልባሌ በሆነች ጉርሻ ስሙን ለማግዘፍ እና የህብረተሰብ ትኩረትን ለማግኘት ሲል የሰራው ትልቅ ሴራ እንደሆነ ለመረዳት ይቻላል ፤ እንዲህም ሆኖ ግን ጋዜጠኛውን አያስተችም ተብሎ ሊያሰኝ አይችልም ፣በሚገባ ሊያስተች እና ሊያስገመግም ወይንም የጋዜጠኝነቱ ሚና ምን እንደሆነ እና ከየት የተማረው የትምህርት ማእረጉ ምን እንደሆነ ሊያሳውቅ ወይንም ሊያስጠይቅ የሚገባው መንገድ እንደሆነ የሚያመላክት ጎዳና ነው ።
zeleke Gesese
ስለ ጉዳዩ ጠለቅ ብለን ከማየታችን በፊት ጋዜጠኝነት ምን ማለት እንደሆነ መዳሰሳችን ጥሩ ነገር ነው ፣ምክንያቱም በየትኛውም ሃገር የሚከበረው እና ከመንግስት በላይ ሊፈራ እና ሊወደስ የሚገባው የጋዜጠኝነት ሙያ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን በመግስት ሲረገጥ እንዲሁም በሙያተኞቹ ሲገለበጥ እና ሲረገጥ ሲናቅ እና ሲወድቅ የሚታይበት ሙያ መሆኑ አንዳንድ ጊዜም ሙያውን እንዲጠላ ያደርገዋል ፣በተለይም በአፍሪካ ይበልጡኑም በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ፣ይህም የሆነው የመንግስታቶች እንቢተኝነት እና ጨለምተኝነት ስሜት ፤ በውስጣቸው ያለውን ድብቅ ሴራም ፣ ሆነ በሃገሪቱ ላይ የሚፈጸመውን ድብቅ ደባ ፤ አልያም የሃገሪቱን ሃብት ምዝበራ ፤ ሆነ የመንግስት ጉልበት መንኮታኮትን ፤ የመረጃ ማእከሎች ከሰሙት ወደ ክፉኛ ደረጃ ያደርሱታል፤ የሚለው ስጋታቸውም ብቻም አይደለም መረጃ ማእከሎችን እንዲዘጉ እና ጋዜጠኞች ለእስር ወይንም ለስደት እንዲበቁ የሚያደርጉት ፣የስልጣን እድሜአቸውን ለማራዘም እንዲረዳቸውም ጭምር ነው ። ታዲያ የእኛ አገሮቹ ማስ ሚዲያ ግን ናሮ ካስቲንግ ናቸው ይህም ማለት በተወሰኑ ሰዎች ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ ስለዕነዚያ ስዎች ብቻ የሚያወራ የሚለፈልፍ አጋኖ የሚያወራ የሚል አይነት ትርጉዋሜ ይሰጠዋል።

በማስ ሚዲያም ሆነ ብሮድካስቲንግ ወይንም ናሮ ሚዲያ ያለው ልዩነት ሰፊ ነው ፣ ናሮ ሚዲያ የሚባሉት ብዙውን ጊዜ በውጭው አለም በስፖርቱ ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚዘግቡት ሚዲያ ብቻ ናቸው እነዚህም እንደ ኢ ኤስ ፒ ኤን ኤ (ESPNA) የተሰኘው የስፖርት ጋዜጠኞች ድርጅት ነው ። ማስ ሚዲያ የሚባሉት ደግሞ የሬዲዮን ቴሌቪዥን፣ጋዜጣ እና ኦንሊን ላይ ድህረ ገጽ ኖሮአቸው በተለያዩ መልኩ መረጃን ለአለም የሚያቀብሉ ሲሆኑ በአሁኑ ሰአትም የሶሻል ኔትዎርኮችንም በመጠቀም ዘገባዎችን በቀላሉ ለአለም ማሰራጨት ስለሚችሉ የሶሻል ኔትዎርኮችንም የሚጠቀሙትንም ያካልላል፣ ወደ ብሮድካስቲንግ ደግሞ ከመጣን ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ከህትመት ድርጅቶች ጋር ብቻ በመፎካከር ሊሰሩ የሚችሉ ድርጅቶች ናቸው ስያሜውን የሚያገኙት አሰራራቸውም ሆነ የስራ ደረጃቸውም ፈቃዳቸውም ሁሉም ይዘታቸው ልክ እንደየ ስማቸው የሚለያይ ሆኖ ሳለ ። ይህንን ጥሬ ትርጉዋሜአቸውን ይዤ ያቀረብኩት ሲሆን ስለ እያዳንዱ ጥልቀት ያለውን ስራ ይዤ ልቅረብ ብል ሃሳቡን በሙሉ ስቶ ወደ ሌላ አቅጣጫ ይገባል እና በተወሰነ መልኩ ብቻ ለማስረዳት እሞክራለሁ ።

ሆኖም ታዲያ ልክ በብዙ ጥቃቅን እንደተሞላ ጋዜጠኛ በእንግሊዘኛው (Embedded journalists) (የጦር ሜዳ ዘጋቢ) ወይንም ኢምቤድድ ጆርናሊስትስ የእኛ አገሮቹም በጉርሻ የተሞሉ ሆነው የማይሆን እና አላስፈላጊ ነገሮችን ሲሰሩ ይታያሉ ፤ብዙ ጊዜ የወታደራዊ ጋዜጠኞች የሃገርን ክብር እና የውስጣዊ ደህንንነት ስጋት ለመጠበቅ ሲሉ ያልሆነውን ነገር ሆነ ብለው እንደሚያወሩት ሁሉ የእኛ አገር በገንዘብ ተኮር የሆኑ ጋዘጠኞቻችን financial target journalists እየሰሩበትን ያለውን ስራ አዘጋጆቻቸው ትኩረት ሰጥተው አለማየታቸው ይበልጡኑ መገናኛ ብዙሃኖችም ጭምር የንግድ ጥቅማቸውን ብቻ ያተኮሩ እንጂ የአንባቢያኖቻቸውን ህልውና ያተኮረ አለመሆኑን ያስረዳል ፤ ለዚህም ነው መርምራዊ ጋዜጠኝነት አስፈልጎ ጥልቀት ባለው ነገር ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ የሚገባው ዋነኛ ስራ ከመውጣቱ በፊት ትልቅ አርትኦት የሚጠይቀው ፣አለበለዚያ ማንኛውም ሰው ቢሆን ከተጠያቂነት አይድንም ።

ምርምራዊ ጋዜጠኝነት ትርጉሙ ምንድነው የሚለውን በቀጥተ ከእንግሊዘኛው ቃል ላይ ብናየው ምንም ሳልጨምር ሳልቀንስ ትርጉሙን ላስቀምጥላችሁ “ Investigative means journalism the use of in-depth reporting to unearth scandals, schemes, which at times put reporters closer to political leaders.” ጋዜጠኞች በጥልቅ ምርምራዊ ስራ ልዩ የሆነን ተሰምቶ የማይታወቅን እና የሚያስገርሙ ጉዳዮችን ፈልፍሎ የሚያወጣ በተለይም የተለያዩ የባለስልጣናቶችን ጉቦ ቅሌትcorruption scandal ፣ወይንም የወሲባዊ ቅሌት sex scandal ,እፈረታዊ ድርጊቶችን ፣በሃገር ህልውና ላይ በድብቅ ሴራ የሚደረጉ ጥፋቶችን ወይንም ሃገርን አሳልፎ ለሌላ ችግር የሚሰጡ የባለስልጣናትንም ሆነ የግለሰቦችን ሴራ ፣ስለ ተደበቁውይንም ጠፉ አለበለዚያም በሚስጥራዊ ስለተያዙ ስራዎች በመመራመር እና በመፈለግ በቅርበት ከፖለቲከኞች ጎን በመሆን እየተከታተለ ሙሉ ሚስጥራዊ ዘገባን በማንኛውም ወቅት እና ሰአት ለህዝብ ምንም ሳያወላዳ የሚያቀርብ ንጹህ ጋዜጠኝነት ነው ።

በኢትዮጵያ ውስጥ የጎደለው ይህ ነው ፣ይህንን ደግሞ ለማወቅ ከተፈለገ አሁንም ባሉት የህትመት ድርጅቶች ላይ ማየት የሚቻል መሆኑን በግልጽ እና በገሃድ ከመንግስት ከሚያስተዳድራቸው ጋዜጦች እና ሌሎች የሬዲዮ እና የቴሌቪዝን ባሻገር እንደ እነ ሪፖርተር እና አዲስ አድማስ ወይንም ፎርቹን አልያም ሌላ በግለሰብ የሚታተሙ ወይንም በሬዲዮ ስርጭት የሚሰራጩ መገናኛ ብዙሃኖች ምንም የምርምራዊ ስራ ብቃት የሌላቸው ወይንም ሃይሉ ያነሳቸው አለበለዚያም በመንግስት ጫና ስራውን እንዳይሰሩ የተገደቡ ሆነው ስናያቸው በሌላም ጎዳና ስንሄድ ሙያተኞቻቸው ከሙያ ጋር ሳይሆን ከጥቅም ጋር የተሳሰሩ ግለሰቦች መሆናቸውን ሁላችንም እንረዳለን ።

ከዚህ በላይ ያለውን ሃሳብ እንደ መንደርደሪያ ሃሳብ አድርጌ ስለጋዜጠኞቻችን የሙያ ባህርይ ጉድለት መነሻ ሃሳብ ሆኖ እና ላሉበት መንገድ ፍንትው ያለ ነገር መግለጽ የማልችልበት ጥቃቅን እና የተሰባበሩ እነዚህ ሃሳቦች ተጠግነውም ቢሆን የነገውን እየወደቀ ያለውን የመገናኛ ብዙሃን ጉዞ ሰሩ ተነቅሎ ከተጣመመበት ቀና ከማይልበት ቦታ ላይ ሸከፍ አድርጎ እንዲይዘው ሊያደርገው የሚችል ባላ ለማስደገፍ የተሞከረች እንጂ ጥልቀት ያለው እውቀት ኖሮኝ አይደለም፣ነገር ግን ይህንን ሃሳብ ባላቀርብ የመገናኛ ብዙሃኑ ውድቀት በሰፋ ጊዜ ሁልጊዜም ሊከነክነኝ ስለሚችል ይህንን ነገር መናገርን መርጫለሁ ታዲያ ለዚህ መነሻ የሆነኝ ዋነኛ ምንጭ በአቶ ዘለቀ ገሰሰ ላይ የተሰራው ናሬሽን ስቶሪ ቴሊንግ ድምቀታዊ ታሪካዊ ንግርት ስለሆነ ወደ ቁምነገሩ ምን እንደተከናወነ እኔም የበኩሌን ለመናገር ቃጣሁ !
ወደ ዋናው ቁምነገር ልምጣ እና በሳለፍነው ሳምንት አዲስ አድማስ ያሳተመው የድህረገጹ ስራ ላይ በንግድ እና ኢኮኖሚ አምዱ ላይ “ወደ አገሩ ሲመለስ “አዲስ አበባ አሸነፈች፤ ቺካጐ ተሸነፈች” የተባለለት አርቲስት” አስገራሚ ስራን አይተን ተደነቅን መቼም ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንደሚባለው ፣ለሰሚው ግራ ገብቶታል ፣ተናጋሪውም ከብዶታል ማንነቱንም ቆልሎአል ፤ እሱነቱንም እረስቶአል ጋዜጠኛውም ለተሰጠው መረጃም ምንም አሳማኝ መረጃ ሳይጠይቅ በስራዎቹ ተደንቆአል ፤በእርሱም ኮርቶአል ከብሮአል ጋዜጠኝነቱንም አስመስክሮአልም ። እንዲህ ነው የኛ ጀግና ጋዜጠኛ ፤ እንዲህ ነው የኛ ባለሃብት አሰኝቶልናል ። እንኳን ደስ ያላችሁ ደስ ይበለን እስኪ እኛም ታሪክ ይዘን መጣን አብረን እልል እንበል ብለን እኛም ፣ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ ብለን እውነታውን እንዲህ ልናቀርበው ከእናንተ ጋር ተፋጠናል እስኪ እናንተም እውነታውን ይዛችሁት ኑ እኛም ይሄው ብለን ዛሬ ብእራችንን ልናሾል ወደድን።

ከመጀመሪያው አረፍተ ነገር ለመነሳት ያህል በቁጥራቸው ከ30 በላይ ለተዘዘሩት የትምህርት ቤት ማሰራት እና የተሰሩበት ቦታዎች ያልተገለጹበት እና በማን ሃይል እንደተሰሩ እና ገንዘቡ ከየት ተገኘ የሚለውን የማያካትት ጥያቄ ሳይነሳ 225 ሺህ ዜጎችን የፈራበትን ትምህርት ቤት የት እንደተመሰረቱ ፣መቼ እንደተመሰረቱ ፣የተመሰረቱት ትምህርት ቤቶች የንግድ ፈቃዳቸው በማን ነው ፣ያሰራቸውስ ሰው ወይንም ድርጅት ማን ይባላል ብለን በጥልቅ ማወቅ እና መረዳት ተገቢ ነው ፣ለዚህም ለእያንዳንዱ ግብረ ሰናይ ድርጅት NGO ሊሰጣቸው የሚገባውን የስራ እና የስም ድርሻ ሳይዘነጋ አቶ ዘለቀ ገሰሰ የሰሩት ተብሎ እንዴት ሊሰየምላቸው ተሰኘ ? ለመሆኑ የንግድ ፈቃዱ በእጃቸው ይገኛልን ? በሌላም አቅጣጫ ሊያስጠይቅ የሚችል ጥያቄ ቢኖር በየአመቱ ለ15 አመታት እንኳን በየ አንዳንዱ ክፍል ማለትም ከአንደኛ ክፍል እስከ ስምንተኛ ደረጃ ድረስ 375 ተማሪዎች ቢኖሯቸው እስካሁን ድረስ 45.000 የሚሆኑ ተማሪዎችን ለማስተማር ይችላሉ ሆኖም ግን አሃዝ ተሳስታችሁ ይሆን ወይንስ እያንዳንዳቸው ክፍሎች በተናጠል ከ 500 በላይ የሚይዙ ክፍሎች ነበሯቸው ?አለበለዚያ ግን ልክ እንደ ጋዜጠኛው እና እንደ አቶ ዘለቀ ስታትስቲክ ስሌታዊ አካሄያድ በአንድ ክፍል ውስጥ 2000 ተማሪዎችን የሚያስተናግድ ክፍል ነበራቸው ያም ማለት ለእያንዳንዱ ከ 1 እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ማለት ነው ይህም ሲሆን በጠቅላላው በ 15 አመታቱ 240.000 የሚሆኑ ተማርዎችን አስተምረዋል ማለት ነው ?

ለመሆኑ ግን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲስ በአንድ ክፍል ውስጥ 2000 የሚይዝ የተማሪውች ቦታ አለውን እንዴ ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደን ይሆናል ? በዚህም መሰረት ላይ በአንድ ክፍል ውስጥ 200 መቶ ተማሪዎች እንኳን ቢቀመጡ ምን ያህል ትምህርት ቤቶች እንዳሉ እና በትምህርት ገበታቸው ላይ ሊኖሩ የሚችሉትን ተማሪዎች እንኳን ብናነጻጽር በአስራአምስት አመታት ከምን ያህል ትምህርት ቤቶች 225.000 ተማሪዎች ሊወጡ እንደሚችሉ ማስላት የሚቻል ይመስለኛል ለዚህም ይህንን ከግንዛቤ እንዲገባ ማድረግ ይቻላል ይህንን በትክክለኛው የስታትስቲክስ አሰራር በግራፍ አቅርብልን የምትሉም ከሆነ ምን ያህል ሊመጣ እንደሚችል እያንዳንዷን ቁጥር በግላጭ በሚያሳይ ዳታ ሰርቼላችሁ ልልከው እችላለሁ ። በሌላው አቅጣጫም እንመልከተው ከተባለ ለ 30 ትምህርት ቤቶች ውስጥ አሉ የተባሉትን የአሃዝ ቁጥር ከተመለከትነው በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ውስጥ 7500 ተማሪዎች አሉ ማለት ነው ፣በሚገርም ሁኔታ በአመት ይህን ያህል የሚያፈራ ትምህርት ቤት ካለን ሃገሪቱ ካላት ህዝብ ብዛት አንጻር እና የትምህርት ማግኘት የተሳናቸው እጥረት ቢያንስ 0.355 ፐርሰንት ቀንሶልናል ማለት ነው ። ይህንም በትክክል ካሰላነው በጣም ትልቅ እድል ነው ምክንያቱም የሃገሪቱ መንግስት እንኩዋን በ 25 አመታት ውስጥ ባስገነባቸው የትምህርት ቤቶች ላይ እንዲህ አይነት ፈጣን የሆነ ለውጥ ለማሳየት ያልቻለበትን ሁኔታ አቶ ዘለቀ ፈጥነው ደርሰውበታል ። ታዲያ ይህም ሆኖ ግን አንድ አባባል ትዝ አለኝ “ዝም የምለው ሳላውቅ ቀርቼ አይደለም ሁልግዜ ትርጉም ከሌለው ቃላት ምክንያት ያለው ዝምታ ስለሚበልጥ ነው” እንዲህም ሲባል ሞኝነት ያለ ይመስላችሁ ይሆን ዝምታን ብንመርጥ አቶ ዘለቀ ገሰሰ እንዲህ አይነት ወሬ ሊያወሩን የቻሉት?

በሌላም በኩል ከ30 በላይ ጋንግስተር ብለው ለተናገሩት አሁንም በግልጽ ልናገር የምችለው እውነታ እንዳለ ይረዳሉ ይህንን እውነታ ደግሞ አልሆነም አልተደረገም አይኔን ጨለማ ያድርገው ብለው እንደማይሉ አውቃለሁ ፣ምክንያቱም እውነተኛውን ታሪክ ወደ ጋንግስተር ስለለወጡት እንጂ ፣ምናልባትም መስመሩን ባልቀው በሳለፍነው ሁለት አመታት ተመልሰው ወደ ችካጎ አቅንተው በመምጣት በከተማዋ የጃማይካውያን አባላቶች በክፉኛ ተደብድበው በጩቤ ተጫጭረው በድብቅ ሆስፒታል ከርመው ከሆስፒታል የተኙበት መረጃዎች ያመለክታሉ ፣ለዚህም ደግሞ በቅርበት እርስዎን ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ የረዳዎትን ግለሰብ ጠንቅቀውት የሚረዱት ይመስለኛል እንዴት አምቡላንስ አስጠርቶ ህይወትዎን እንዳተረፈልዎ ይህንን እንደ ምስክር ማቅረብ ከተቻለ እናቀርባለን ሆኖም ግን ለአደረጉት ውለታ ጀማይካውያኖች አደረግነው የሚሉት ጉዳይ ቢሆንም የምእራብ አፍሪካውያኖችም እጅ አለ የሚባለውም ነገር እንዳለ አይዘንጉት።

ከዚያም ውጭ ቆዳው ጥቁር ውስጡ ነጭ እየተባለ የሚጠራው እና ከፍተኛ የዘረኝነትን መንፈስ የሚያራምደው ይሄው ግለሰብ እንደመሆኑ መጠን እና በእራሱ በወገኖቹ በኢትዮጵያኖች ላይ አይናቸው ላይ ከፍተኛ ሃይል ያለውን የባትሪ መብራት በማብራት እና በጥቁር የሰኩሪቲ ጋርዶች እየተገፉ እንዲደበደቡ የሚያደርገው ይሄው አቶ ዘለቀ ገሰሰ ፤ እራሱን እንደጲላጦስ ከደሙ ንጹህ ነኝ እኔ መልካም አድራጊ እና ፈጣሪ ነኝ ብሎ እንደ ጣኦት አምልኩኝ ብሎ መነሳቱ በጣም አስገራሚ የታሪክ ብዥታ ነው ። ለእንደዚህ አይነቱ ድርጊቶቹ ደግሞ የሃገርን ልጅ በሃገር ልጅ ብለው የዳሎል ባንዶች ያቁዋቋሙትን የዋይልድ ሄር ባር ወይንም ቡናቤትን የእኔ የብቻዬ ነው እናንተን እንደፈለገኝ አደርጋለሁ እያለ ሲዝብት በዝምታ እየታየ እና ወንዱን ቀሚስ አስለብሶ ሴቱን ወንድ ባደረገበት በዚህ በሰሜን አሜሪካ ዝምታን የለበሰው ወጣት የኢትዮጵያ ወንድ ፤ምን ያህል ትእግስተኛ እና ፍቅር ለበስ ህዝብ ሆነን እንደተፈጠርን ያሳዩበት ትልቅ አጀንዳ እንዳለ መረሳት የለበትም ለዚህ ደግሞ ለቀድሞው ለዳሎል ባንድ አባላት ለአቶ አስራት እና ሩፋኤል ወልደማርያም ይግባቸው እና ዋይልድሄር በቁሞ ለረጅም ዘመን እንዲጓዝ አድርገውታል አሁንም እያደረጉት ይገኛሉ ። ታዲያ ኢትዮጵያኖቹ እንደ መዝናኛ እና እንደራሳቸው ሃብት ተጠቅመው የሃገራቸውን ልጆች ያቋቋሙትን ትልቅ ድርጅት ለመርዳት እና ለመዝናናት ሲሄዱ ከፍተኛ ግፊት እና እንግልት የደረሰባቸው ኢትዮጵያኖች ብቻ የትየለሌ ናቸው ፣እንደዚህ ልንጠቁማችሁ የወደድነው ግን ለምን ጃማይካኖች እና የምእራብ አፍሪካውያኖች በአቶ ዘለቀ ገሰሰ ላይ ጥቃት ሰነዘሩ የሚለውን እንደመጠይቅ ካነሳን በራሱ ወገኖች ላይ የለመደውን ድርጊት በሌሎቹም ላይ መፈጸሙ ሲሆን ፣ በከንቲባው ጸሃፊም ላይ ፈጽሞት ድርጅቱ እንዲዘጋ ፒትሽን ሁሉ እንደተፈረመበት እና አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ እንደነበር የሚረሳው አይመስለንም።ሌላው ልናሳውቃችሁ የፈለግነው የዘለቀ ውሸት ለኢትዮጵያን ወገኖች በጣም አዲስ እንደመሆኑ መጠን የተወራው ሁሉ እውነት ሳይሆን ሃሰት ነው የሚለውን እና ፣ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ የሚለውን ሃሳብ ለመሰንዘር ሲሆን ፣አገራችንንም ከእንደነዚህ አይነቶቹ ዳግም ዶ/ር ኢንጂነር ዘሚካኤል ዓይነቶቹ ለመታደግ ስንል እውነታውን አፍረጥርጠን መናገሩን ወደድን።

በሌላም በኩል በችካጎ ፖሊስ ዲፓርትመንት አባላት ለጥበቃ በተሰማሩ ፖሊሶች በአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚነቱ ተይዞ ማን እንደሚሸጥለት የማይጠቁም ከሆነ በአደገኛ ሁኔታ ወደ መቀመቅ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል በፖሊሶች ተነግሮት እና በእጃቸው ላይ ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ የእጽ አዘዋዋሪ ሃይሎችን እየጠቆመ ከፖሊስ ጀርባ የአዘዋዋሪዎች ሰላይ ሆኖ እንዲሰራ መሰየሙን አገር ያወቀው ጸሃይ የሞቀው ታሪክ ነው ፤ ይህንን አሉባልታ ሳይሆን እውነታውን ለመናገር ያህል መስመር ለማስያዝ እንጂ ከዚያ ውጭ ከማንኛውም ነፍሰ በላ ሰው ጋር እንዳለገጠሙ ያውቁታል ፤ እንዲያውም በአንድ ወቅት በቡሽቲዎች(ጌይ) ባር ለመዝናናት ገብተው ፤ቆነጃጅቶችን አገኘን ብለው የወንድ ወይዘሮዎችን አቅፈው እየሳሙ ሲደንሱ ቆይተው በመጨረሻው ወቅት ላይ ድምጾቻቸውን ሲሰሙ እና ከእንቅስቃሴ ብዛት መደባበስ እና ስሜት ውስጥ መገባባት ሲጀምሩ በዳንስ ክፍሉ ውስጥ የወንዱን ብልት አፈፍ አድርገው ይዘው ማንነታቸውን ሲያውቁ እግሬ አውጭኝ የፈረጠጡበትን እና ጌዎቹም ያዙልን እያሉ እንደተከተሉዋቸው በገሃድ የሚታወቀውን ታሪክ ጋንግስተሮች ናቸው ብሎ ማደናበር ተገቢ አይደለም እና ይህንን እውነት ባንደብቀው ጥሩ ነው ።
ወደ ሌላው አረፍተ ነገር ስንገባ የዋይልድ ሄር ባር በወቅቱ የነበረው የደንበኞች ኮታ በመጀመሪያው ፎቅ ላይ 75 ሰው ከዚያም በምድር ላይ ያለው ላይ ደግሞ 300 ሰው በኢሊኖይ ስቴት ዲፓርትመንት የሲቲ ኦፍ ሺካጎ የንግድ ፈቃድ ላይ የተመዘገበው የቀድሞው ፈቃድ በግልጽ እንደሚያሳይ ጠንቅቀው የሚያውቁት ነው ፤ ይሄው የዳሎል ባንድ ክለብ እንዴት ተብሎ ቢገመት ይሆን አንድ ሺህ ሰው የሚይዝ ተብሎ ሊነገር የበቃው ? በነገራችን ላይ የዋይልድ ሄር ክለብ የአቶ ዘለቀ ገሰሰ ክለብ ሳይሆን ዳሎል ባንድን አንድ ጣልያናዊ ሲያሰራቸው ቆይቶ በህግ ጉዳይ ቤቱ እንዲዘጋ ሲደረግ እንደገና ዳሎል ባድ የሼር ኩባንያ በመፍጠር በጋራ የከፈቱት እና በአቶ ዘለቀ ገሰሰ የስም ማጭበርበር ስሌት የተነጠቁበት ሁኔታ ያለ ሲሆን እስከመጨረሻው የሽያጭ ወቅት ድረስ አባሎቹ የድርሻቸውን አግኝተው የተለያዩ መሆናቸውን በግልጽ በቅድሚያ ለመጠቆም እወዳለሁ፣ለዚህም ደግሞ በተደጋጋሚ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የእኔ ክለብ ነው ብለው የገለጹት ይሄው ክለብ በአባልነት ማን ማን እንደነበረ የሚገልጸውን ስም ዝርዝር ወደ ሁላ ይዤ እቀርባለሁ እና ይህንን ጉዳይ በጥሞና ይከታተሉት ዘንድ የአክብሮት ግብዣዬ ከወዲሁ ነው ።

ለዚህም ክለብ መውድቅ እና የገንዘብ መጥፋትም ሆነ የገንዘብ ኪሳራ መዳረግ ዋነኛ ተጠያቂው አቶ ዘለቀ ከጥቂት አመታት በፊት ከ 50% በላይ የሼር ሆልደርነቱን በቅምጣቸው (እማማ) አማካይነት ገንዘብ ተሰጥቶአቸው ሲቆናጠጡ ከሁለቱ የዳሎል ባንዶች በአሁን ሰአት በህይወት የሌሉትን ወንድሞች የሼር ሆልደርነታቸውን መሸጥ ሲፈልጉ ገዝተው መሆኑ እንዲታወቅ ያሻል ፤እንዲህ ሆኖ ሳለ በህጉ መሰረት ከ50 % በላይ ሼር ሆልደርነቱን የያዘው ሃላፊ ይሆናል የሚለውን ቦታ ተረከቡ ከዚያም የተለያዩ ነገሮችን በስማቸው ለማድረግ እንዲያስችላቸው እና ውሳኔ አሳላፊ ሆነው እንዲረዳቸው እድሉን ተጠቀሙበት በዚህም ሁኔታ ፣ በወቅቱ ቅምጣቸው የነበሩት እና ቢሊየነሯ አሮጊት እናት በየጊዜው ብድር እያበደሩ ስራቸውን እንዲያስኬዱ ያደርጉላቸው ነበር ሆኖም ግን ለስም እንጂ ገንዘቡ የሚውለው ለሌላ ተግባር መሆኑን ያልገባቸው ሼር ሆልደሮቹ ምንም ከመናገር ተቆጥበው ኖረዋል።

አሁን ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ ባንዱን ለማናገር የሚነሳ የመገናኛም ብዙሃንም ሆነ ግለሰብ ቢኖር አንደበታቸው ዝም ነው የሚለው። ዝምታ ነው መልሴ ብለው የውስጣቸውን በውስጣቸው ይዘው እንዲሄዱ የተደረገበት ዋነኛ ሴራ በተለያዩ አጋጣሚዎች የተሰሩት ድብቅ የሆኑ ተንኮሎች እና በህግ እንዲደነገጉ የተደረጉት አንዳንድ ቴክኒክ እና ታክቲኮች በመሆናቸው ማናቸውንም የመገናኛ ብዙሃን በዚህ ጉዳይ ላይ ለማናገር በራቸው ዝግ ነው። ይህንንም ጉዳይ የሚያውቀው አቶ ዘለቀ አንደበቱን ከፍቶ ክለቡ የኔ ነው ለማለት ያስደፈረበትም ክንያት ይህ ሳይሆን እንዳልቀረ በችካጎ የሚገኘው ህብረተሰብ እንደመነጋገሪያ አድጎ ሰሞኑን ሲወያይበት ከርሞአል ፤በእርግጥም በየመጠጥ ቤቱ እና ቡና መጠጫ ቤቱ የውሸቱ ልሂቅነት ልዩ መወያያ ርእስ ሆኖ መክረሙ እኔ ዶክተር ነኝ እያለ የመንግስትን መስሪያቤት ጭምር ሲያጭበረብር ከነበረው ዘሚካኤል የሚበልጥ ትልቅ ውሸት የውሸት መናሃሪያ ሲሉት ተሰምተዋል።

በእዳ መብዛት መንግስት ከቀድሞው የቅምጥ ሚስትዎት (እማማ) ጋር አብሮ በእዳ እጅዎት ተጨማልቆበት የነበረውን ገንዘብ ለማጥራት ሲሉ የዳሎል ባንድ ለዘመናት ያፈራውን ድርጅት የግሌ ነው በማለት ከሴትዮዋ ጋር እየተበደሩ በእኩይ ተግባርም ሆነ በእድሳት ወይንም በስራ ማስኬጃ መልክ ያጠፉትን ገንዘብ ፣በመያዦነት እንዲወረስ እና እንዲሸጥ ሲወሰንብዎት እርስዎ ግን በሙሉ አፍዎት ሸጨው ነው ብለው ማለትዎ እውነት በችካጎ ያለው ህዝብ አይፋርድዎትም ፣›?
የፔን ፕሪስከር የኤክስፕረስ ኢን ሆቴል ኮርፖሬት ባለቤቶች ለተወሰነ ጊዜ የመጡበት ምክንያት በቀድሞው ጊዜ ዘለቀ ገሰሰ ይዞአት የነበረችው የእድሜ እና የገንዘብ ባለጸጋ ሴትዮ የቅርብ ወድጆች በመሆን ክለቡን ለማየት በቅተዋል ።

ከዚያ ባሻገር ግን የአሜሪካው ፕረዚዳንት ሴናተር በነበሩበት ወቅት እንኩዋን አይደለም ሊጎበኙት ቀርቶ የሴናተርነት ስራቸውን ተጠምደው በቆዩበት ስፕሪንግ ፊልድም ሆነ በስተት ዲፓርትመንት ጊዜአቸውን በመሰዋእትነት ማሳለፋቸውን ማንም የሚረዳው ሲሆን ለክለብ መዝናናት ጊዜም ያለነበራቸው ናቸው ለዚህም ደግሞ በክለቡ ውስጥ በአባልነት ወይም ሽርክና የነበራቸው የዳሎል ባንድ አባላት እንኳን የመጡበትን ጊዜ የማስታወስም እድሉ እንዳልነበራቸው ለማወቅ ችያለሁ ።
በሌላም ጉዳይ ልይ እንምጣ እና አቶ ዘለቀ ገሰሰ ያልገለጻቸው እና የባንዱ አባል የነበሩት እነማን እንደነበሩ ለማሳወቅ የሚያስገድደኝ ሲሆን እነዚህንም አንድ ባንድ የስም ዝርዝራቸውን ማቅረቡ ተገቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ። ዋና ዋናዎቹ አስራት አምሮ ስላሴ የዋይልድ ሄር የሼር ሆልደር የነበረ አሁንም ዋይልድ ሄርን በመምራት ላይ ያለ ፣ሩፋኤል ወልደማርያም የዋይልድ ሄር የሼር ሆልደር የነበረ አሁንም ዋይልድ ሄርን በመምራት ላይ ያለ ፣መላኩ ረታ የዋይልድ ሄር የሼር ሆልደር የነበረ (በህይወት የሌለ) ሙሉገታ ገሰሰ፣ ደረጀ መኮንን (በህይወት የሌለ) የዋይልድ ሄር የሼር ሆልደር የነበረ ፣ ዘለቀ ገሰሰ፣ ንጉሴ አስፋው ችካጎ ላይ የተቀላቀለ እና ጴጥሮስ መኩሪያ በችካጎ የሚኖር ፣በዚህ ዝርዝር ውስጥ የአቶ መላኩን እና ደረጀ መኮንን የሼር ሆልደርነት በመግዛት ከፍተኛውን ድርሻ በመያዝ ከ 51% በመቶ በላይ ይዞ ሃላፊነቱን ለመያዝ የበቃው አቶ ዘለቀ ገሰሰ በሃላፊነት ተቀመጠ እንጂ የድርጅቱ ባለቤት በመሆን በማንኛውም ዘመን አልመራም ፣ለዚህም እንደምሳሌ ሆኖ ጠቀስ የሚችለው ክዋይልድ ሄር ሼር ሆልደር በመሆን የነበረው አንዱን አካል የህግ ባለሙያ የነበረው አሜሪካዊውን ባለሃብት( በህይወት የሌለ )ብቻ መጥቀስ ተገቢ ነው ፣ምክንያቱም በዚህ ጉዳይ ላይ የዳሎል ባንዶችን እንደ ባለቤትነት አባል ለመጥቀስ ያልወደደውን አቶ ዘለቀን ለማሳመን እና እውነታውን ለማውጣት ትልቁ ምሳሌ እና ሊጠቀስ የሚገባው ሰው መሆኑን ማወቅ የገባናል ።

ይህም ብቻም አይደለም ዋይልድ ሄርን ወደ ውድቀት የዳረገውንም አቶ ዘለቀ ሸጥኩት ያለበትን ምክንያት ዝርዝር ሲተነተን በእዳ ተይዞ በባዶ ወደ ሃገሩ ተሸኘ የሚለውን ቃላት ብንመነዝረው የሚያወጣ ትርፍ እና ኪሳራ ያለው ሲሆን በአሁን ሰአት ላይ ግን ዋነኛ ትግሉ በሃገሪቱ ላይ በኢንቨስተርነት ስም የተመዘገበው ይሄው ባለ እዳ በሃገሪቱም ውስጥ ገብቶ ባንኮችን ለማጭበርበር የሚያመቸውን ስትራቴጂ እየነደፈ እንጂ በማናቸውም ሁኔታዎች ዘለቀ ገሰሰ ዋይድ ሄርን በባለቤትነት አልመራም። በሼር ሆልደር የአባልነት ስምምነት ግን የድርጅቱ አመራር አካል ወይንም ማናጀር በመሆን አገልግሎአል ይህንን በምንም መልኩ የማይታበይ እውነተኛ ቃል ነው ።

ለዚያም በባንካራብሲ bankruptcy ሰበብ የኢሊኖይስ የታክስ ኢንቬዥን (ታክስ ማጭበርበር )መዝገብ ላይ እንዲሰፍር የተደረገበት እና ከፍሎ ያልጨረሰውን እዳ እና ከስሬአለሁ ድርጅቱንም ዘግቻለሁ ብሎ ያለበትንም በመላው አሜሪካ ብቻ የሚደመጠውን የችካጎ ፐብሊክ ሬዲዮ በወቅቱ በኪሳራ የዘጉ ድርጅቶችን የ3 ደቂቃ የአየር ሰአት ሰጥቶ ጠቅለል አድርጎ በአወራበት ሰአት ስለ ዋይልድ ሄር የተገለጸውን ሃሳብ ብቻ መጠቆም ይበጃል።

ሆኖም ግን ዛሬም ቢሆን ዋይልድ ሄርን አስተዳድረዋለሁ የባለቤትነቱም ዘርፍ የኔ ነው ብሎ የሚለው አቶ ዘለቀ ፣ በቀድሞዋ የቅምጥ ሚስቱ እዳ መብዛት እና ይህችው ሴትዮ ገንዘቤን እፈልጋለሁ ክፈለኝ በማለት ወጥራ በመያዟ ምክንያት እንዲሸጥ ከተደረገ በሁዋላ እና በአሁን ሰአት ምግብ ቤት የሆነ ሲሆን ፣የሼር ሆልደሮቹ የሚገባቸውን ገንዘብ ወስደው እስከ ወዲያኝው የሄደበትን መንገድ ላይረግጡ ተሰነባብተው ዛሬ ስማቸውንም በክፉም ሆነ በደግ ማንሳት እስኪቀፈው ድረስ እና እራሱ የሰራው በደል እና ክፉ ሴራ ለእራሱ እስኪከረፋው ድረስ ሆኖ ሳለ በሌላው ወገን ደግሞ እነርሱ ስሙንም እንደገና በማደስ ዛሬ ከቀድሞው በተሻለ ሁኔታ ህይወቱን ዘርተውበት ዋይልድ ሄር ችካጎ ከሚገባው በላይ ያለመለመ ትልቅ ባር መከፈቱን ማብሰራችን የማይቀር ነው ። ለዚህም ደግሞ በባለቤትነት የሚመሩትን ሰዎች ሙሉ በሙሉ ከመጥቀስ ይልቅ በቀድሞው የዋይልድሄር አባሎች እና የዳሎል ባንድ ቀዳሚ ሰራዊት የሚባሉትን አቶ አስራትን እና የቴዲ አፍሮ ባንድ ላይ በከበሮ መችነት የሚያገለግለውን ሩፋኤል ወልደማርያምን ብቻ መጥቀሱ ምስክርነትን ሊሰጥ ይችላል።

በሌላም መስመር ወድ ዳሎል ባንድ መለስ ብለን የኋላ ትዝታ እንዲህ በቀላሉ እንጫር ካልን ፣ዳሎል ባንድ እንዲፈርስም ዋነኛ ምክንያት የሆነው እራሱ አቶ ዘለቀ መሆኑን የሚረሳ አይደለም ።መቸም ሙት አይወቀስም ወይም አይከሰስም አለበለዚያም ለምስክርነት አይጠራም እንጂ ሟች ደረጀ መኮንን አቶ ዘለቀን ካለው አንድ አጭር አረፍተ ነገር ለትውስታው ያህል እንዲታወሰው ማድረጋችን ተገቢ ነው “ዘለቀ ይህንን ትልቅ ህብረተሰብ እና ይህንን ትልቅ ባንድ ምስቅልቅሉን የምታወጣው እና የምትበጠብጠን አንተ ነህ ፤አንተ ቤዝ ጊታር ተጨዋች እንጂ ዘፋኝ አይደለህም ! ዘፋኝ ነኝ እዘፍናለሁ ካልክ እኔ ባንተ ድምጽ ሙዚቃን ሰርቼ አላበላሽም እና ካንተ ጋር አልሰራም ! የሙዚቃም ችሎታውም የለህም” የምትለዋን አጭር መስመር ቃል በዚያች ትንሽዬ አዳራሽ ውስጥ በመናገሩ ጥርስ ተነከሰበት ከዚያም ዳሎል ባንድን በዓንድ እግሮ ቆሞ እንዲፈርስ ተደረገ እና ተለያይተው ጊዜ ባንድ እንዲፈጠር ተደረገ ።

ስለ ዳሎል ባንድ ከ ዚጊ ማርሌ እና ሜሎዲ ሜከርስ ጋር የነበራቸውን ጉዞ ለማስታወስ ያህል ከአስር አመታት በላይ ሳይሆ የተጓዙት ከ1986 እ.ኤ.አ እስከ 1990 ሲሆን ሁለት አልበም አሳትመዋል እነሱም conscious party 1988 One bright day..1989 Both won Grammies And sold over a million copies of each ከዚያም 3ኛውን ሙዚቃ በ1996 የተሰራው ሲሆን የግራሚ አዋርድ አሸናፊ የሆኑበት እንደሆነ ይታወቃል በዚህም የዳሎል ሙሉ ባንዱ እና የዚጊ ማርሌ ባንዶች በጋራ በሚሰሩት ስራ የዚህ ሽልማት ባለቤቶች ሆነዋል ። ከዚያም በመቀጠል እስከ 2000 እ.ኤ.አ ሩፋኤል ወልደማርያም (የአሁኑ የቴዲ አፍሮ ከበሮ ተጨዋች) ከዚጊ ማርሌይ ጋር አውሮጳ እና አሜሪካ ቱር ያደረገ ሲሆን ሌሎቹ በተለያዩ አጋጣሚዎች ተገለው ነበር ከዚያም ቀጥሎ grateful dead.. የተሰኘ ግሩፕ መቋቋሙ የሚታወስ ነው ።

ወድ ኢትዮጵያ ኮሙኒቲ እንምጣ እና የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ የተመሰረተው ከ32 አመታት በፊት ሲሆን ምክንያቱም አቶ እስክንድር ወይሳ የተባለ ሰው በድንገተኛ ሞት በመነጠቃቸው ምክንያት ኮሙኒቲውን ለመመስረት በቺካጎ እና አካባቢው የነበሩ ጥቂት ኢትዮጵያኖች እና ኢትዮጵያን ወዳጆች ተሰባስበው መክረው ያደረጉት ሲሆን በዚህ ተሳትፎ ላይ ግን ዶ/ር እርቁ በዶክትሬት ዲግሪያቸው ላይ ዴዘርቴሽን (የመመረቂያ ስራቸውን) በመስራት ላይ ሳሉ እያለ መሆኑ ያለኝ መረጃ ያመለክታል።

እርሳቸውም በሚሽጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የነበሩ ሲሆን በመስራችነት ላይ የተመዘገቡ አይደሉም በዚህም መሰረትም አቶ ዘለቀም በዚሁ መስራችነት ላይ አልነበረም ፣ዶ/ር አብርሃም ደመወዝም የተቀላቀሉት ከተመሰረተ ረዘም ካለ አመታት በሁዋላ እንደሆኑ ታሪካዊ ስራዎቹ ያስረዳሉ ። ታዲያ እንዲህ ያሉት ዝባዝንኬዎችን እንዲጠቀሱ እና አቶ ዘለቀ ገሰሰን ሰማይ እንዲደርስ የሚያደርጉት እነዚህ የቃላታዊ እጀባ ስራዎች ያልሰራቸውን ስራዎች ሰርቶል በማለት ተአማኒንነትን በህብረተሰቡ ውስጥ በመፍጠርም ሆነ በባንኮች አካባቢ ትልቅ ትኩረትን በመስጠት በሚገኙት የሃገሪቱ የእድገት መሰረት እና የኢንቨስተሮች ግብዣ ሳጥን ውስጥ በመግባት የገንዘብ ብድር እዳ እንዲያገኝ የሚያስችል ስልት ነው እንጂ ዘለቀ ገሰሰ ሰራሁዋቸው የሚላቸው ትክክለኛ እና አንጡራ የሆኑ ስራዎች አይደሉም።
በእርግጥ ነው በእውነተኝነት እና በተአማኒነት የሰራ ሰው ይመሰገናል ፣ይሞገሳል ፣ይካባል ፤ይደገፋል፤ክብር ያገኛል ። ለዚያም ነው ተበዳዮቹ የዳሎል ባንድ አባላቶች ዛሬም ድጋሚ በከፈቱት በዚህ ትልቅ የሙዚቃ አዳራሽ ውስጥ በችካጎ የሚገኙት ኢትዮጵያኑ እየሄዱ እንኳን እናንተ ሆናችሁልን በሰላም ዳግም ዋልድሄርን መለሳችሁልን የሚሉዋቸው ፣በእርግጥም ወደ ሃገሩ ሲመለስ ችካጎ ተሸነፈች ሳይሆን የተባለው ፣ችካጎ ተነፈሰች ፣እዳ በኪነጥበቡ ቀለለላት መሆኑንስ ትገነዘቡት ይሆን …….ሁላችንም እፎይ ተመስገን ብለን ማለታችንንስ እንዴት ታውቁት ይሆን ….?

የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ በየአመቱ በሚያደርገው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮራም ላይ በሚደረገው የድጋፍ ጥሪ ላይ አቶ ዘለቀ ገሰሰ ብዙውን ጊዜ ከ10.000 በላይ የአሜሪካ ዶላር እለግሳለሁ እያለ ለዘመናት የኮሙኑቲውን አመራር አካላት እና አባላቶች በማጭበረበር አንድም ቀን ለ32 አመታት ሲጓዝ የነበረውን ኮሙኒቲ ቃሉን ጠብቆ 10,000 የአሜሪካን ዶላር ያልሰጠ መሆኑን እና እስከዛሬ ድረስ ቃል የገባውንም የገንዘብ ስሌት ኮሙኒቲው በመዝገቡ ውስጥ አስፍሮት የሚገኝ መሆኑን እና ብዙውን ጊዜ ለእራሱ አቤቱታቸውን ማቅረባቸውንም ጠንቅቆ የሚያወቀው ጉዳይ ነው ታዲያ እንዲህ ሆኖ ዛሬ ለ33 አመታት መሰረቱን ይዞ የሄደውን እና ከተለያዩ አለማት ስደተኞችን ወደ ሶስተኛ ሃገራት እንዲመጡ ከፍተኛ ጥረት በማረግ ከኢሚግሬሽን አካላቶች ጋር በጥምረት በመስራት ታላቅነቱን እና አጋርነቱን አግኝቶ በኢሚግሬሽን ዲፓርትመት አመታዊ በጀት የሚንቀሳቀሰውን ይሄንኑ ኮሙኒቲ ከመስራቾቹ አንዱ ነኝ ብሎ ላለው ጉዳይ ፤ከመስራቾቹም ዋና ዋና የሚባሉት በአሁን ሰአት በቦርድ አባልነት ያሉ ሲሆን ታላቅ የቤቱ ሃውልት እና ምስክሮች ናቸው እና፣ውሸትን ደበቅ እናድርገው ይሉናል ።

በሌላው በኩል ስለ ጀሲ ጃክሰን የፖለቲካ ሂደት እና የፑሽ ኪሚቴ ተብሎ የተወራው የንፋስ መንገድ በጣም አስገራሚ በመሆኑ የአሜሪካን የፖለቲካ መንፈስ ለማይረዱ ሰዎች ወደ ፖለቲካው ለመግባት እንዲህ ተባልኩኝ ብሎ ማውራት በጣም የሚያስቅ በመሆኑ ዝርዝር ሃሳብ መስጠቱ ተገቢ ስላልሆነ በይለፍ ብናልፈው ተገቢ ነው ፤ለምን ቢባል አሜሪካኖች ስለ እራስቸው ፖለቲካ እንኩዋን የውጭ ሰው የራሳቸውንም ጥላ የማያምኑ ዜጎች ናቸውና ነው !።

ማጠቃለያ ፤ ባሳለፍነው 2007 የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምርጫ ላይ የቅንጅት አመራሮች እና ጋዜጠኞች በገዢው መንግስት በወያኔ ክስ ተመስርቶባቸው ወደ ማረምያ ቤት ከተወረወሩ በሁዋላ ፣ጋዜጠኞችንም ሆነ የተቃዋሚ ፓርቲውን በነበረው ሁኔታ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ጋር የሰላማዊ ድርድር በማለት የሃገር ሽማግሌዎች በመሆን ሽምግልናውን የጀመሩትን ሰዎች ዕነማን እንደሆኑ መጥቀስ የሚያሻ አይመስለኝም ሆኖም ከተፈለገ አንድ ሶስቱን እና ዋነኞቹን መጥቀሱ ተገቢ ነው ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረ ስላሴ ፣ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ ፣አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ ዋናዎቹ በመሆን አጀንዳውን ይዘውት ይነቀሳቀሱ የነበሩ ሲሆን ከሙስሊሙ ማህበረሰብ እና ክክርስትናውም ማህበረሰብ የተውጣጡ የእምነቱ አመራር አካላቶችም በጋራ በመሆን መስራታቸው የሚታወስ ነው ታዲያ አቶ ዘለቀ ገሰሰ በየትኛው የሽምግልና መስመር ላይ ነው የሃገር ሽማግሌ በመሆን አቶ መለስ ዜናዊን ለማነጋገር የበቁት ? እስኪ የአዲስ አድማስ ጋዘጣ የቀድሞ 2007/2008 እነደ ኤሮጳውያን አቆጣጠር ያላችሁን የጋዜጣ ማህደራችሁን ፈተሽ አድርጋችሁ በዳኛ አድል መሃመድ የተፈረመውን ደብዳቤ የያዘውን ሪፖርታችሁን አይታችሁ ለማንበብ ሞክሩት እና የሃገር ሽማግሌዎች እነማን እንደ ነበሩ መስክሩ ። የኢትዮጵያ ባንክች መቼም እንዲህ አይነቱን ታሪክ እያያችሁ የእዳ መዝገባችሁን ከፍታችሁ እንኩዋን ደህና መጣችሁ እንደማትሉ አምናለሁ ስለሆነም እውነትኛ ባለሃብት የሚሰራውን ያውቃል እና በእውነት መንገድ እንጓዝ
“ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” እግዚአብሄር ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
የእውነት መንገድ ብትቀጥንም አትበጠስም
የውሸት ጋሪዎች ግንበእውነተኛው መንገድ በቀን እየተደናበሩ በጨለማ በጭንብል እንደተገፉ ይኖራሉ !
አበቃሁ ቸር እንሰንብት

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46730#sthash.jQYTJN3d.dpuf

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on September 16, 2015
  • By:
  • Last Modified: September 16, 2015 @ 11:01 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar