www.maledatimes.com “በአሽባሪነት ተጠርጥሮ “የታሰረው ታዳጊ የፕ/ት ኦባማ ልዩ እንግዳ ሆኖ ተጋበዘ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

“በአሽባሪነት ተጠርጥሮ “የታሰረው ታዳጊ የፕ/ት ኦባማ ልዩ እንግዳ ሆኖ ተጋበዘ

By   /   September 17, 2015  /   Comments Off on “በአሽባሪነት ተጠርጥሮ “የታሰረው ታዳጊ የፕ/ት ኦባማ ልዩ እንግዳ ሆኖ ተጋበዘ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 15 Second

“ልጄ በት/ቤት ጓደኞቹ ፊት በካቴና በመታስሩ በጣም አዝኛለሁ” ወላጅ አባት
የ 14 አመቱ አህመድ መሃመድ ገና ታዳጊ፣ የሙስሊም እምነት ተከታይ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በ እርሱ እድሜ ሊሰሩ አይደለም ሊታሰቡ የማይሞከሩትን የኢሌክትሮኒክስ ቁሶችን መገጣጠም የእለት ተገባራቱ ናቸው ። ታዲያ ይህ በአሜሪካው የቴክሳሱ ግዛት በኢቪርንግ ከተማ የ ማክአርቱር ከፍተኛ ደረጃ የመጀመሪያ አመት ትምህርቱን ሰሞኑን የጀመረው ታዳጊው አህመድ ባለፈው ሰኞ ወደ ት/ቤቱ አንድ እንግዳ ነገር ይዞ ጎራ ሲል ያለጠበቀው እና ያልገመተው ችግር ይገጥመዋል።አህመድ ከፈጠራ ሰራዎቹ መካከል አንዱ የሆነው የማንቂያ ሰአት ለመምህሩ ለማሳየት እና ችሎታውን ለማሰመረቅ ቢሞክርም መምህርቱ የአህመድ እቃ ሰአት ሳይሆን “ቦምብ ይመሰላል” ከሚል ጥርጣሪ ላይ በመወደቃቸው ፖሊስ ተጠርቶ አህመድም አጁ በካቲና ታስሮ በቁጥጥር ሰር ይውላል።
ከ ሱዳን ተሰደው በ አሜሪካ ከ 30 አመት በላይ የኖሩት ወላጅ አባቱ መሃመድ ኢል ሁሰን መሃመድ በልጃቸው ላይ የደርሰው የሰበኣዊ መብት ረገጣን በማሰመልከት ሲናገሩ “ ልጄ ያለበቂ ምክንያት በተማሪዎች ፊት እጁ በካቴና የፊጥኝ በመታሰሩ በጣሙን አዝኛለሁ። ይህ አይነቱ ድርጊት እኔ በማወቀው አሜሪካ መሬት ላይ ይካሄዳል ብዩ በፍጹም አልጠብቅም። ይሁን እንጂ ህዝቡ ከጎናችን በመቆሙ በጣሙን ተደሰተናል።ለጄ ጉብዘናውን ለ አለም ለማሳየት የሚጥር በሩህ አይምሮ ያለው ነው።” ብለዋል ። የወላጅ አባቱን ሞባይል ስልክ ፣መኪና ፣ ኮምፒውተር እና የመሳሰሉትን እንደነበሩ አደርጎ የሚጠግነው አህመድም “በራሴ ጥረት የሰራሁትን ሰአቴን ለአስተማሪዩ በማሳየት ላስገርማት ብሞክር በአስተማሬ ተጠርጣሪነት(የውሸት ቦምብ ነው ብላ በመሰጋቷ ) የተነሳ ለእስራት በመዳረጊ እጅጉን አዝኛለሁ።ከዚህ በሁዋላ በዚህ ትምህርት ቤ/ት መማር በጭራሽ አልፈልግም ት/ቤቱን ለቅቄ መሄድ እሻለሁ።” ብሏል። አህመድ በ አሁኑ ወቅት ከት/ቤቱ መታገዱም ታውቋል።
የአህመድ በ አራት ፖሊሶች በጥር ጣሪ ታስሮ ወደ ወጣቶች ጽባይ ማረሚያ/ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ የጣት አሻራ ሰጥቶ መለቀቅ በሺዎች የሚቆጠሩ የማህበራዊ ድህረ ገጾችን ያጨናነቀ እና ተከታዮችን ያስቆጣ ሲሆን ለአብነት ያህል ፕ/ት ባራክ ኦባማ በቲዊተር አካውንታቸው “ አህመድ ድንቅ ሰራ ነው የሰራሀው ። ይህን የለፋት ወጤትህን ወደ ዋይት ሃወስ(ቤተ መንግስታቸው ) ይዘሀው እንደትመጣ ትፈልጋለህ? ።በአንተ ትጋት ብዙ ታዳጊዎች በሳይንስ ትምህርት እንዲማረኩ ታደርጋለህ ። አሜሪካ ማለት የታላቅ ጥረት ውጤት አገር መሆኑን አስመሰክረሃል ።”በማለት ጥረቱን አወድሰውታል።የፕ/ት ኦባማ ቢሮም በበኩሉ እሮብ እለት ባወጣው መግለጫው በመጪው ጥቅምት 19 2015 እኤአ በቤተመንግስታቸው/ዋይት ሃውስ ውስጥ በሚደረገው የ ሰነ ኮዋክበት ባለሙያዋች ምሽት ላይ ታዳጊው አህመድ አዳሩን በክበር እንግድነት ከሳይነቲስቶች፣ ከኮዋክብት አጥኝዎች፣ ከኢንጅነሮች ከአስተማሪዎች እና ከተማሪዎች ጋር ኣንዲያሳልፍ ጋብዞታል ። የፊስ ቡክ መሰራቹ ወጣቱ ማርክ ዙኩር በርግ እንዲሁ በሰጠው አስተያየት “አህመድ ለሰራው ፈጠራ እስራት ሳይሆን ሽልማት ነበር የሚገባው ።ለማንኛውም የሚቸግርህ ነገር ካለ ወደ ፊስ ቡክ ጎራ በል፣ ላገኝህ እወዳለሁ ” ብሎታል ። ታዋቂዎቹ እነ ጉግል እና ቲዊተርም አህመድን “በርታ ከእኛ ጋር መሰራት ከፈለግህ በሩ ሁሌም ለአንተ ክፍት ነው”ሲሉ ጋብዘውታል ። አንዱ በር ሲዘጋ ሌላኛው ወለል በሎ ይከፈታል ነው ነገሩ።
አንዳንድ ወገኖች አህመድን ሰሙ እና ሃይማኖቱ ለጭፍን ተጠርጣሪነት እና ለእሰራት ሳይዳርገው እንዳልቀረ ይገምታሉ። ይሁን እንጂ ፖሊስ ግን ወቀስውን አሰተባብሏል ። “ከክስተቱ ብዙ ተምረናል ፣ክሱንም ወድቅ አድርገነዋል “ብሏል። አሜሪካዊው አህመድን ሰናሰብ በእኛም አገር ቢሆን ያለበቂ ማሰረጃ ለእሰራት እና ለመንጓጠጥ የሚዳረጉ ከታሰሩ በሁዋላለምን እና እንዲት እንደተፈቱ እንኳን የማያውቁ አያሌ ወገኖች መኖራቸውን አንዘንጋ። ቢያንስ ለእርምጃ አንቸኩል ፣ከሆነም ይቅርታ ለመጠየቅ አንዘግይ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on September 17, 2015
  • By:
  • Last Modified: September 17, 2015 @ 10:21 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar