www.maledatimes.com የትግራይ ክልል ካቢኔ ሥርነቀል ሹም ሽር አካሄደ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የትግራይ ክልል ካቢኔ ሥርነቀል ሹም ሽር አካሄደ

By   /   September 23, 2015  /   Comments Off on የትግራይ ክልል ካቢኔ ሥርነቀል ሹም ሽር አካሄደ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 31 Second

  • በ  ጋዜጣው ሪፖርተር

     የትግራይ ብሔራዊ ክልል መንግስት ካብኔ ትናንትና ባካሄደው ስብሰባ ከምክትል ፕሬዝደንት እስከ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ድረስ ሥርነቀል ሹም ሽር ማካሄዱ ታውቋል።

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ፓርቲ በመቀሌ የሰማዕታት አዳራሽ ባካሄደው 12ኛ የሕወሓት ጉባኤ ላይ ከፓርቲው ጓዶች እንዲሁም ከትግራይ ከተለያዩ ወረዳዎች የመጡ የሕብረተሰቡ ወኪሎች ባሰሙት የመረረ የመልካም አስተዳደር ችግር መነሻነት የትግራይ ብሔራዊ ክልል መንግስትን ለማስተዳደር ኃላፊነት የወሰደው ህወሓት የተጣለበትን ኃላፊነት ከስሩ ለመፍታት ሥርነቀል የካቢኔ ሹም ሽር ማድረግን በመሰረታዊ አማራጭነት መውሰዱን ምንጮች ጠቁመዋል።

በተደረገው ሹም ሹር መሰረት፣ አምባሳደር ዶክተር አዲስ ዓለም ባሌማ የክልል መንግስቱ ምክትል ፕሬዝደነት፣ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር (ሞንጀሪኖ) የክልሉ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ እና አቶ ዓለም ገብረዋህድ የክልሉ ጽ/ቤት ኃላፊ ተደርገው ተሹመዋል። እንዲሁም የቀድሞ የክልሉ ምክትል ፕሬዝደነት የነበሩት አቶ በየነ ምክረ የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት ኃላፊ ሆነው ተዛውረዋል።

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በመቀሌ የሰማዕታት አዳራሽ 12ኛ የሕወሓት ጉባኤ ወቅት ባካሄዱት ምርጫ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ አቶ አባይ ወልዱን ሊቀመንበር አድርገው መምረጣቸው የሚታወስ ነው። እንዲሁም ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት 50 አባላት ታጭተው 45 አባላት የተመረጡ ሲሆን፤ የአቶ ዓባይ ወልዱ ባለቤት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማርያም እና የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከንደያ ገብረሕይወት ከቀደሙት የማዕከላዊ አባላት መካከል በድጋሚ ሳይመረጡ ቀርተዋል፡፡ ሌላው ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት በተካሄደው 11ኛው የሕወሓት ጉባዔ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው ከተመረጡት መካከል አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ፣ ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማርያምና አቶ ገብረመስቀል ታረቀ በሥራ አስፈፃሚነት ሳይቀጥሉ ቀርተዋል።

ይህን ተከትሎ የም/ፕሬዝደንት፣ የድርጅት ጉዳይ እና የጽ/ቤት ኃላፊዎችን በአዲስ ሥራ አስፈፃሚዎች እንዲተኩ የተደረገው አግባብ ህወሓት ለመሰረታዊ ለውጥ ራሱን እያዘጋጀ መሆኑ አመላካች ተደርጎ ተወስዷል።

ህወሓት በ12ኛ ጉባኤው ዘጠኝ አባላትን ለህወሓትና ለኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ  አባላት አድርጎ መምረጡ ይታወሳል። እነሱም፤ አቶ አባይ ወልዱ፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ አቶ በየነ ምክሩ፣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ አቶ ዓለም ገብረዋሃድ፣ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ዶክተር አዲስዓለም ባሌማ እና ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ናቸው።

አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማና ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር አዳዲስ የሥራ አስፈፃሚ አባላት ሆነው የተመረጡ ናቸው።¾

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on September 23, 2015
  • By:
  • Last Modified: September 23, 2015 @ 11:06 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar