0
0
Read Time:38 Second
- በ ጋዜጣው ሪፖርተር
በጋምቤላ ክልል በተለይም በአማራ ተወላጆችን (ደገኞች) ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ በማፈናቀልና በመግደል ወንጀል የተጠረጠሩ 46 የቀድሞ የክልሉ ሹማምንት ክስ ሰሞኑን በአዲስአበባ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተረኛ ችሎት ቀረበ። ከቀበሌ እስከ ዞን በአመራርነት እርከን ነበሩ የተባሉት ተከሳሾች ባቀጣጠሉት ግጭት 126 ሰዎች በግፍ የተገደሉ ሲሆን ከ7 ሺህ የሚልቁ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።
የፌደራል አቃቤ ህግ በ2006 እና በ2007 ዓ.ም “ደገኞች ከክልላችን ይውጡልን” በሚል በጋምቤላ ክልል ማዣንግዞን፣ ጎደሬ እና ሜጢ እንዲሁም በሌሎችም ቀበሌዎች የወንጀል ፈጽመዋል ባላቸውና ከቀበሌ እስከ ዞን በአመራርነት እርከን፣ በሚሊሻነት እና በተለያዩ የግል ስራ የተሰማሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር በማዋል ክስ መስርቷል።
አቃቤ ሕግ ተከሳሾች ዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ዜጎችን በማስታጠቅ አንዱ በሌላው ላይ የጦር መሳሪያ እንዲያነሳ አነሳስተዋል የሚለውን ወንጀል አንቀጾችን ጠቅሶባቸዋል። በተጨማሪም የእርስ በእርስ ግጭት እንዲነሳሳ ለማድረግ በመስማማት፣ በማደም በወንጀል ድርጊቱ ተሳትፈዋል ብሏል።¾
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating