www.maledatimes.com ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የልብ ሰፔሻሊስት አስራለች። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የልብ ሰፔሻሊስት አስራለች።

By   /   October 2, 2015  /   Comments Off on ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የልብ ሰፔሻሊስት አስራለች።

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 50 Second

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የልብ ህክምና ስፔሻሊስት አስራለች — የልብ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት የነበሩትን ፕሮፌሰር አስራት ወ/የስን ለእስር ዳርጎ በልብ ህመም ይሰቃዩ በነበሩ ዜጎች ህይወት የፈረደው የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ከአስራት በኋላ በኢትዮጵያ የታዩትን የዘርፉ ባለሞያ ዶክተር ፍቅሩ ማሩን በሙስና ወንጀል ጠርጥሪያቸዋለሁ በማለት ካሰረ አመታት ተቆጥረዋል፡፡ የገቢዎች ሚኒስትር ከነበሩት የብአዴኑ አቶ መላኩ ፈንታ ጋር ለእስር የተዳረጉት ፍቅሩ በልብ ህክምና ስፔሻላይዝድ ያደረጉት በስዊዲን አገር ቢሆንም አገሬን ማገልገል እፈልጋለሁ በማለት አዲስ የልብ ህክምና ማዕከልን ከፍተው ነበር፡፡ዶክተሩ በራሳቸው ወጪ ዶክተሮችን ወደ ስዊዲን በመላክም በዘርፉ ስፔሻላይዝድ የሚያደርጉ ባለሞያዎች እንዲፈጠሩ ማድረጋቸውም ይነገርላቸዋል፡፡ ዶክተሩ ከአንድ የሞያ አጋራቸው (ዶክተር በቀለ ጋር በሽርክና )በከፈቱት ሆስፒታል የልብ ምታቸው የቀነሰ ታካሚዎች ምታቸው እንዲስተካከልና የተዘጉ የልብ የደም ስሮችን የሚያፍታታ ህክምና መስጠት ጀምረው የነበረ ቢሆንም ከታሰሩ በኋላ ህክምናውን የሚሰጥ ባለመገኘቱ እየተመላለሱ ይታከሙ የነበሩ ህሙማን ችግር ውስጥ ወድቀዋል፡፡ አርቴፊሻል መሳሪያ ተገጥሞላቸው በየስድስት ወሩ እየተመላለሱ ህክምናቸውን ያደርጉ የነበሩ የልብ ህሙማን ፍቅሩን ማግኘት ባለመቻላቸው ለሞት የተዳረጉ መኖራቸውንም የሚናገሩ አልጠፉም፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ስኩል ፍቅሩ ያለ ክፍያ እውቀታቸውን ማካፈልም ጀምረው ነበር፡፡በስዊዲን ዩኒቨርስቲዎች ዳጎስ ያለ ገቢ ይዝቁበት የነበረን የመምህርነት ሞያቸውን ለአገር ፍቅር የገበሩትን ፍቅሩን በሙስና ማሰር ቤት እንደማይመታ የቅርብ ሰዎቻቸው ይናገራሉ፡፡ ዶክተሩ የህክምና አገልግሎት ሲሰጡባትና ሲያስተምሩባት ከነበረችው ስዊዲን ጋር ጠንካራ ግኑኝነት የነበራቸው በመሆኑም ስዊዲናዊያን የልብ ሐኪሞች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የልምድ ልውውጥ ሲያደርጉ ነበር፡፡ከዶክተሩ እስራት ጀምሮ ግን ስዊዲናዊያኑ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አያውቁም፡፡ የዶክተሩ መታሰር ብዙ ችግር እንደፈጠረ የተረዳው የኢትዮጵያ የግል ሐኪሞች ማህበር ለፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለፍትሕ ሚኒስቴር፣ ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ለዳያስፖራ ዴስክ ደብዳቤ ደብዳቤ በመጻፍ ዶክተር ፍቅሩ እንዲፈቱ ተማጽኗል ፡፡ እንደ ሪፖርተር ዘገባ ከሆነ ደብዳቤው በማኅበሩ የተጻፈው ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ቢሆንም፣ እስካሁን ከማናቸውም ምንም ዓይነት ምላሽ አለማግኘቱ ታውቋል፡፡ዶክተር ፍቅሩ በስዊዲን ነዋሪ የሆነች አንዲት ሴት ልጅ አለቻቸው፡፡ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አሊ ሱሌይማን ለሪፖርተር በሰጡት ቃለ ምልልስ ትልልቆቹን አሳዎች የማናጠምደው ‹‹ልማቱ እንዳይደናቀፍ በማሰብ ነው››ማለታቸው አይዘነጋም፡፡በዶክተሩ መታሰር የስንቱ ህይወት እየተደናቀፈ መሆኑስ አልታያቸው ይሆን? መቼም ወንጀል የፈጸመ ሰው መታሰር የለበትም በማለት ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው ሊከራከር ባይችልም እንደ ኢትዮጵያ ለፖለቲካ ገረድ የሆነ ፍርድ ቤት ባለበት አገርና ንጹሐን ለዓመታት እየታሰሩ ነጻ ናችሁ መባላቸውን እየተመለከትን የእስራታቸው መንስኤ ሙስና ነው ለማለት አንደፍርም፡፡ በሙስና ተብለው የታሰሩ የከተማችን ሐብታሞች እስር ቤቱን ማደሪያ ብቻ ሲያደርጉት እየተመለከትን በዶክተሩ ላይ በር ቆልፎ በቀጠሮ እየተመላለሱ ህክምና ያገኙ የነበሩ ህመምተኞችን (በሽታው ጊዜ እንደማይሰጥ እየታወቀ) በሞት መቅጣት ለዜጎቹ ዋጋ ከሚሰጥ አካል የሚጠበቅ አይደለም::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on October 2, 2015
  • By:
  • Last Modified: October 2, 2015 @ 8:35 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar