0
0
Read Time:39 Second
ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲረጋገጥ፤ ብሎም ለአዲሱ የፕሬስ ትውልድ ፈር ቀዳጅ የነበረው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ለብዙዎች የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች እና ቤተሰቦች መሪር ሃዘን ነው። ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በአንደበቱ እውነትን የመሰከረ፤ በሰላ ብዕሩ ሃቅን የፈነጠቀ ለኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ምሳሌ ሆኖ ያለፈ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ነው። ጋሽ ሙሉጌታ ሉሌ በህይወት በነበረበት ወቅት መልካም ነገርን ሰርቶ አልፏልና በመልካም ተግባሩ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ታሪክ ሲነሳ፤ የነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች ታሪክ ይወሳል። የነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች ገድል ሲታወስ ደግሞ፤ የጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ መልካም ስም እንደ ፈርጥ ያንጸባርቃል። በውጭ አገር የምንገኝ የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች፤ ጋሽ ሙሉጌታ ሉሌን እንደታላቅ ወንድም፤ እንደሙያ አጋር እና እንደ ጥሩ ምሳሌ እያነሱ መልካም ተጋድሎውን ያስታውሳሉ። መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይውላልና የጋሽ ሙሉጌታ ስራ እና ስም ለዘለአለም በክብር ይታወሳሉ። አምላክ ነፍሱን ይማር። በውጭ አገር የሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating