www.maledatimes.com የማለዳ ወግ…ስለ ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ያገባናል ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማለዳ ወግ…ስለ ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ያገባናል !

By   /   October 6, 2015  /   Comments Off on የማለዳ ወግ…ስለ ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ያገባናል !

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 31 Second

====================================
* ትናንት እኔም በወህኒ ነበርኩ ፣ ከእውነት ጋር ነበርኩና ዛሬ ነጻ ነኝ
* የከበደው ወህኒ ስቃይ ጽዋ የዛሬው ተረኛ አንተ ትሆን ዘንድ ግድ ሆኗል

የግሩም መታሰር ዜና …
===============

በሳውዲ ሚና ጀማራት ስለሞቱና ስለቆሰሉት መረጃ ለመሰብሰብ ካንድ የሳውዲ ጤና ጥበቃ ኃላፊ ጋር ቁጭ ብየ የአንድ ብርቱ ወዳጀ መታሰር መረጃ ደረሰኝ ፣ ደንገጥ አልኩ … ኃላፊው በወጋችን መካከል ስልኬን ተመልክቸ ቀና ስል ፊቴ ሲለዋወጥ ተመልክተው ኑሮ ” ምን ሆነሃል?”  አሉኝ ። “ከቤተሰብ መልዕክት ደርሶኝ ነው ” በሚል ጉዳየን በቤተሰብ ጉዳይ ጥያቄያቸውን አድበስብሸ ከቢሯቸው ወጣሁ  ! የጋዜጠኛ ግሩሜን ባለቤትና የማውቃቸው የሚያውቁት ወዳጆቸን ስልክ አፈላልጌ ወደ የመን ሰንአ ስልክ ደወልኩ  …!

አዎ ወዳጀን በእኔ የደረሰው የፈራነው ደርሶበታል ፣  ብርቱው ጋዜጠኛ ግሩም ዛሬ ነጻ አይደለም ። ዘብጥያ ወርዷል የሁቱ አማጽያን በሚያስተዳድሯት የመን ዋና ከተማ በሰንዓ ለእስር ተዳርጓል። በማይመች ፣ በማይደላው ፣ ህይዎት በሰቀቀን በሚገፋበት የየመን ስደት ለወገኖቹ ብቸኛ ተጠሪ አምባሳደር የነበረው ጋዜጠኛ ግሩም ከሳምንት ፍለጋና አሰሳ በኋላ ዛሬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። ተጨባጭ መረጃው እንደ ደረሰኝ የመያዝ መታሰሩን ዜና ከቤተሰቡና ከባለቤቱ ከገጣሚ ጸሀይ በየነ ለማረጋገጥ ችያለሁ !

የእኛ ሰው ጋዘጠኛ ግሩም በየመን … !
=========================

በሽዎች የሚቆጠሩ የእኔ ቢጤ ተስፈኛ ወገኖቻችን ሰርተው ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ ፣ አለያም እራሳቸውን ለመቀየርና ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ ” ወደ ተስፋዋ ምድር”  ወደ ሳውዲ ይሰደዳሉ። ስደቱ እስካሁን ድረስ አላቆመም ። ታዲያ መከራ ሰቆቃን ችለው በሚያደርጉት ግሩሜ ”  የሞት ጉዞ !” በሚለው ስደት  ከቀይ ባህርን ማዕበል ፣ ከየመን በርሃ ሀሩርና ከደላሎች የሚደርሰውን አበሳ ችለው የመን ይደርሳሉ !  በማይመቸው የየመን ጉዞ እድል ቀንቷቸውና ከሞት ጋር ተፋጠው በየመን ሲኦል ምድር የተረፉት ብዙዎች የየመን ስደተኛውን አባት ጋዜጠኛ ግሩም ያገኙታል ። ግሩም የተቸሩትን ፣ የተከፉትን እማኝ አድርጎ ዘር ሀይማኖት ሳይለይ ድምጻቸውን የሚያሰማ ፣  የሚያስተጋባ ብቸኛ የግፉአን ድምጽ ሆኖ አመታትን በየመን ገፍቷል ። ጋዜጠኛ ግሩም እንደ ስደተኛ ጋዜጠኛ ድምጻቸውን ከማሰማት ባሻገር የተቸገሩትን በመርዳት ፣ የተራቡትን በማብላት ፣ የታተዙትን በማልበስ ፣ የታመሙትን በማሳከም ፣ ወህኒ የወረዱትን በመጠየቅ ታላቅ ሰብአዊ ተግባር በመከዎኑ የማከብረው ጉምቱ ሰብአዊ ወንድምም ነው  !

ግሩሜን ማን አሳሰረው  ?
================

ከቶ ብርቱው ሰው ግሩሜን ምን ገጠመው ? ማንስ አሰረው?  ማንስ አሳሰረው ? ብየ ጠየቅኩ … መልስም አገኘሁ ፣ ያገኘሁት መልስ ግን ያማል  !  ተቸግሮ የደገፈው ፣ ታርዞ ያለበሰው ፣ በቤቱ አሳርፎ የጭንቅ ቀንበሩን ከላዩ ላይ ያወረደለት ”  አንድ የሃገሩ ልጅ ስደተኛ ነው ጠቁሞ ያሳሰረው !”  አሉኝ ፣ ምን ብሎ ? አልኳቸው ” በስደተኛው ስም እርዳታ ይሰበስባል ፣ ስለየመን የተለያዩ መረጃዎችም ወደ ውጭ ያቀብላል ” ብለው እንደደፈደፈበት አጫወቱኝ  ! በእጁ የበላው የዚያ ከሳሽ ተንኮል አልደነቀኝም ፣ የገረመ ፣  የደነቀኝ የከሳሽ ምስክሮች እንጅ … በቅርቡ በተከሰተው የየመን ጦርነት አካላቸው የጎደለ ወንድሞች በደጋፊያቸው ፣  አጽናኝ የክፉ ቀናቸው በግሪሜ ላይ ለተለጠፈው የውሸት ክስ  ” እማኝ ምስክሮች ናቸው ”  ሲባል መስማት ግን ልብን ይሰብራል ! ያማል … ያማል… ያማል  !

ትናንት ከቀትር በኋላ መታሰሩን እንደ ሰማሁና ከዚያም አመሻሹ ላይ ማምሻውን ውድ ባለቤቷን ጋዜጠኛ ግሩምን  ካለበት እስር ቤት የጠየቀችው ገጣሚ ጸሃይን በስልክ አግኝቻት ስለታሰረበት ጉዳይ ፣ ከፖሊስ ስለ ተሰጣት መልስና ስለ ከሳሽ ምስክሮች ዘርዘር አድርጋ አጫውታኛለች  !  እኔም አልኩ …ግሩሜን ማሰር ይቻላል ፣ እውነቱን ከውስጡ ፣ እምነቱን ከውስጡ መቅፈፍ ግን የሚቻለው የለም  !

ስማኝ ወዳጀ ግሩም …
===============

ትናንት እኔም በወህኒ ነበርኩ ፣ ከእውነት ጋር ነበርኩና ዛሬ ነጻ ነኝ … ግን አሁንም እውነትን ይዠ ስጓዝ ፣ መረጃ ለወገኔ ሳቀብል ምን እየተዶለተልኝ አላውቅም ፣ የሚጠብቅ ፈጣሪ ስለ እውነት ይጠብቀኛል እንጅ በሰው ልጅ አስተማማኝ ጥበቃ ላይ አይደለሁም ፣ ጠባቂው የእውነት አምላክ ነው  ! … ከስደት መከራው አልፎ የከበደው ወህኒ ስቃይ ጽዋ የዛሬው ተረኛ አንተ ትሆን ዘንድ ግድ ሆኗል ፣ ይብላኝ ለከሳሽ መስካሪዎች እንጅ አንተም እኔም መታሰርክን እናቀው ነበር ፣ አይዞህ ግሩሜ የጨለመው ወህኒ የከበደው ቀንና መአልት ያልፋል ፣ ነገም ሌላ ቀን ነውና ይነጋል  ! የምትጠበቀው በፈጣሪ ነውና አይክፋህ  !

ወዳጆቸ
አቅም በፈቀደ መጠን ከባለቤቱ ጋር ያደረግኩትን ቃለ ምልልስ በቅርቡ አጋራችኋለሁ  !

ስለ ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ያገባኛል ፣ ያገባናል!
#YemenFreeGirumTekelaimanot

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on October 6, 2015
  • By:
  • Last Modified: October 6, 2015 @ 10:06 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar