www.maledatimes.com መከራ ሲመጣ አይነገርም ዐዋጅ … - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

መከራ ሲመጣ አይነገርም ዐዋጅ …

By   /   October 30, 2015  /   Comments Off on መከራ ሲመጣ አይነገርም ዐዋጅ …

    Print       Email
0 0
Read Time:19 Minute, 45 Second

     

ነፃነት ዘለቀ

ውድ አንባቢያን ዛሬ ትንሽ ለየት ባለ ሁኔታ የልብ የልባችንን ነው የምንጫወተው፡፡ መደባበቅ ብሎ ነገር አይኖርም፡፡ ለምኑ ብለን? ለየትኛው ጊዜስ ብለን እንወሻሽ? “በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ” – መተዛዘብን ለዛሬ እንርሳት፡፡

 

መጠጥ እወዳለሁ፤ እናም እጠጣለሁ፡፡ አሁን አሁን እያረጀሁ ስመጣና በያውም ላይ መጠጢቱ ዋጋዋ በብርሃን ፍጥነት ሽቅብ እየተወነጨፈ በመምጣቱ አወሳሰዴ ቀነሰ እንጂ ዱሮ የሰጠ አይመልሰኝም ነበር – ባናት ባናቱ፡፡ የሀገር ንዴቱ አለ፤ የቤት ውስጥ ጓዳጎድጓዳ አለመሟላቱ አለ፤ አንዳንዴ ደግሞ የመሥሪያ ቤት ጣጣም ይታከልበታል፤ የምኞት አለመሣካት ይደመርበታል፣ የሕይወት ተንሻፍፎ መጓዝ ይጨመርበታል … ብቻ በሰበብ አስባቡ ከጓደኞች ጋር እጠጣለሁ – አሁንም፡፡ እርግጥ ነው – እንዳመቺነቱ እንጂ የሠርክ ጠጪ አይደለሁም፤ ያን ያህል የሱሱ ተገዢ የሆንኩም አይመስለኝም፡፡ ለመተው ብፈልግ ባይሆን ለጥቂት ቀናት አፋሽጌ የመጠጥ ጓደኝነቴን በቀላሉ የማቋራጥ ይመስለኛል፡፡ ለማንኛውም ስናደድም እጠጣለሁ፤ ስደሰትም እጠጣለሁ – አንዱ ትምክህተኛ ባል ለሚስቱ “አንቺ ብትቆጪኝም እመታሻለሁ፣ እኔ ብቆጣሽም እመታሻለሁ” እንዳለው ነው፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለች የኔና የኔን መሰሎች ሕይወት ትቀጥላለች፡፡ የደከረተ ማኅበረሰብ ዋና መገለጫዎች ደግሞ ሰካራምነትና አስደንጋጭ የሕዝብ ቁጥር መጨመር መሆናቸው አይካድም፡፡ ዜጋው ጊዜውን በምን ያሳልፍ? እንደገናም ዕብደትና ልመና፣ ቦዘኔነትና ሴተኛ አዳሪነት (ሌልኛ አዳሪነትም እየተስፋፋ ነው አሉ)፣ በረንዳ አዳሪነትና የበርካታ ሃይማኖቶች በየሥርቻው እንደ አሸን መፍላት … ሊዘነጉ የማይገባቸው የከሰረ ኅብረተሰብና ዕድገቱ የጫጫ ሀገር ገመናዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ጉድፎች በስፋት የሚከሰቱት ደግሞ ለሀገር ተቆርቋሪና ለወገን ቅን አሳቢ መሪዎች ሥልጣን ላይ ሲወጡ ነው አሉ፡፡

ማንም ሰው አልኮል ሲጠጣ መስከሩ አይቀርም፤ ለስካሩ ፈጥኖ ወይ ዘግይቶ መከሰት ግን የሚጠጣው የአልኮል መጠጥ ዓይነትና መጠን እንዲሁም የመጠጣት ልምድና የሰውነት አቋም ይወስኑታል፡፡ አንዳንዱ ቶሎ ይሰክራል፤ አንዳንዱ ደግሞ እንደኔ አካፋይ ጋን ይሆንና በቀላሉ እጅ አይሰጥም – መስከሩ ግን አይቀርም –  ሰው ነውና፡፡ እኔም ሆንኩ ጓደኞቼ ስንጠጣ ታዲያ ከፍ ሲል በየትኛዋ ብርጭቆ ዝቅ ሲል ደግሞ በየትኛዋ ጉንጭ(sip) እንደምንሰክር አናውቅም – በጭራሽ!! ብዙ ሰው ጉድ የሚሆነው እንግዲህ እይህ ላይ ነው፡፡ አንዳንዱ ሰው ሰክሮ ሲወላገድና ብዙ ጉዳት ሲደርስበት ይታያል፡፡ በበነገታው ሲጠየቅ ግና መጠጣቱን እንጂ መስከሩን እንደማያውቅ ይናገራል – “ውኃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው”ና፡፡ አንዳንዱ ጉረኛ ሰካራም “ሄይ! እኔ የፈለግሁትን ያህል ብጠጣ ስካር ብሎ ነገር አይነካካኝም” ይላል – ይህም ውሸት ነው፡፡ ጥምብዝ ብሎ የማይሰክር የለም – ግን የመጠጡ ፍጆታ አሁንም ወሳኝ ነው፡፡ በሁለት ብርጭቆ ድራፍት ክልትው የሚል ጀማሪ ሰካራም የመኖሩን ያህል በሃያ ጃምቦ ድራፍት ንቅንቅ የማይል ፉስቶ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ብሎም ቢሆን የትኛዋ ጃምቦ ላይ እንደሚሰክር እሱም ሆነ እኛ አናውቅም እንጂ ይህ ፉስቶ ሰክሮ መወላገዱ አይቀርም፡፡ እንዲያውም የርሱ ስካር አያድርስ ነው – የዞረ ድምሩን ይከፍላል፡፡ ልብ በሉ እንግዲህ – የምሰክርባትን ጉንጭ መጠጥ አላውቃትም እያልኳችሁ ነው፡፡ አንተም ጠጪ ከሆንክ የምታውቃት አይመስለኝም፡፡ ፀጉር ሲመለጥና ነገር ካፍ ሲያመልጥስ መች ይታወቃል? ይሁንና ፀጉርም ይመለጣል፤ ነገርም ከአፍ አምልጦ በሽመል ያዠልጣል ወይ ሰውን ያስቀይማል፡፡ ይህ ነባራዊ እውነት ነው፡፡

ከኔ መነሻ ጋር የምትመሳሰል የፈረንጆች ፈሊጣዊ አባባል ደግሞ እንካችሁ፡- “The last straw that breaks the camel’s back.” ትላለች፡፡ ገለባ የምትሸከም ግመል ልትቋቋመው የምትችለው የገለባ መጠን አለ፡፡ ከዚያ ሲያልፍ እንደፈሊጡ ወገቧ ለሁለት እንክት ባይልም ሸክሙ ከአቅሟ በላይ ይሆንባትና አልነቃነቅ የምትልበት ሁኔታ (state of stalemate) ይፈጠራል፡፡ ያቺ ግመሏን ወደዚህ የእምቢታ ደረጃ የለወጠች ገለባ የትኛዋ እንደሆነች ግን ማንም ማወቅ አይችልም፡፡ ምናልባት በፊዚክሳዊ የሒሣብ ቀመር ሊደረስባትና ልትታወቅ ትችል ይሆናል፡፡ ባለሙያዎቹን መጠየቅ ነው፡፡

ቆንጠጥሀና ኮርኩመህ ያሳደግኸው የገዛ ልጅህ ጭካኔህ ሲበዛበት ያንተን አባትነት ባፍንጫየ ይውጣ ብሎ እግር አውጪኙን የሚጠፋበት ከፍ ሲልም ግምባርህን ብሎ ወደሚቀርብህ የመቃብር ስርፍራ እንድትሸኝ የሚያደርግበት አጋጣሚ ሊከሰት ይችላል – አያድርስ ነው፡፡ ያሳደግኸው ውሻ የምትፈጽምበት ግፍና በደል ሲበዛበት ፍጹማዊ የተፈጥሮ ታማኝነቱን በመተው ሥጋህን ዘልዝሎ ቁጭትና እልሁን የሚወጣበት ጊዜም  ያጋጥማል – አሁንም አያድርስ፡፡ ለሁሉም ነገር ገደብ አለው፡፡ ገደቡን ሲያልፍ አደጋ አለው – ገደቡን ያለማወቃችን ምሥጢር ብዙዎችችንን እየጎዳን እንደሚገኝ ደግሞ የዓለማችን ወቅታዊ ገጽታ ቁልጭ አድርጎ እያሳየን ነው፡፡ የአንድን ነገር የወደፊት ዕጣ ፋንታ አስቀድሞ በመገመት ከወዲሁ የሚረዳና ተገቢውን ጥንቅቃቄ የሚያደርግ ምንኛ የታደለ ነው!

የተጣደ ወተት በየትኛዋ ቅጽበት ገንፍሎ ከድስቱ እንደሚወጣና እሳቱን እንደሚያጠፋው አናውቅም፡፡ ወተትን ስታፈላ ልባምነትን ይጠይቃል – አለበለዚያ በተወደደ ወተት ኪሣራ ነው(ዱሮ ብዙውን ጊዜ በነፃና ገበያ መውጣት ሲጀምር ግን ከአሥር ሣንቲም በታች በሆነ ዋጋ ይገኝ የነበረው አንድ ሊትር ወተት ዛሬ ከ20 ብር መብለጡን ታውቃለህ?)፡፡ የተጣደ ውኃ ቀድሞ ለስ ይላል፤ ለጥቆ ለብ ይላ፤ በማስከተልም ሞቅ ይላል፤ ከዚያም ተክተክ ይላል፤ ያልተቆጣጠሩት እንደሆነ በስተመጨረሻው እሱም ሆድ ይብሰውና የተነነው ተንኖ (የሞተው ሞቶ) ቀሪው እንደወተቱ በመገንፈል ሰላም የነሣውን በሥሩ የሚገኝ እሳት ያጠፋዋል፡፡ ይህን እውነት ከነፍካሬያዊ ፍቺው መካድ ልበ ሥውርነት ነው፡፡…

ከሦስት ዓመታት በፊት ኢሣት አስተላልፎት የነበረውን የዚያን የብርቅዬ ልጃችንን የታማኝን ዝግጅት ዛሬ በድጋሚ አየሁ፡፡ በጣም ተናደድሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች በመጨረሻው “ ‹ወጥ በወጥ› ያደርጉን ይሆን?” ብዬም ተጨነቅሁ፡፡ ይህን የታማኝን ዝግጅት እነፕሮፌሰር መስፍንና መሰሎቹ  በወያኔው መንግሥት የ“ትግሬ አልተጠቀመም”ና “ወያኔ የትግራይን ሕዝብ አይወክልም” ዘፈን አቀንቃኞች እንዲመለከቱት በጣም ወደድኩ፡፡ ይመልከቱትና አንጎል ካላቸው እውነቱን ከሀገራችን ጋዜጠኞች ብቻ ሣይሆን ከውጪዎቹ የሰብኣዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የበላይ ኃላፊዎች አንደበት ይረዱት፡፡ እውነት ብትመር ብትጎመዝዝም ምርጫ በምናጣበት ወቅት ዶሮ ማታ ብለን መጨለጥ ይገባናል፡፡ እንዲህ ስናደርግ አንድም ከተጣባን ኮሶ እንሽራለን  አሊያም ሌላ አማራጭ እንፈልግና ከህመማችን እንፈወሳለን፤ እየተዝረጠረጥን መኖር ግን አይገባንም፡፡

ከዚህ ዝግጅት በጣም የሳበኝ አንዱ ፈረንጅ የትግሬውን አገዛዝ “Internal Colonialism” ሲል የገለጸው ነው፡፡ እኛም እንዳቅሚቲ ከዚህ አልፈን ይህን ሥርዓት ጥቁሮች በጥቁሮች ወንድሞቻቸው ላይ የጣሉት አፓርታይድ እንደሆነ በተደጋጋሚ ጮኸናል – ጊዜው አልደረሰ ሆኖ ሰሚ ጠፋ እንጂ፡፡ ዘመኑ ሲብትማ ሣሩ ቅጠሉ ጆሮም አንደበትም አለው – የወር ተረኛን የድል ብሥራት ዜና ለዱር ለገደሉ ለማወጅ፡፡

አዲስ የቅኝ ግዛት ዓይነት ነው የገጠመን፡፡ አዲስ የአፓርታይድ ዓይነት ነው የተጣለብን፡፡ የዚህ ጭራቃዊ ቅኝ አገዛዝና አፓርታይድ የመጨረሻ ውጤት የሚሆነው የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እንጂ ከሦርያ የበለጠ ዕልቂት ነው፡፡ የናቁት … አስረግዞ 85 ሚሊዮን ሕዝብ እንዲህ ካስደገደገን የተናቀው 85 ሚሊዮን ሕዝብ ከእንቅልፉ ሲነቃ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ማሰቡ ይዘገንናል፡፡ ግን ግን ፈጣሪ ከጎናችን አይለይ፡፡ የእስካሁኑ በቃችሁ ብሎ ለሌላ ውርጅብኝ አይዳርገን፡፡ ጸሎት መያዝ አሁን ነው፡፡ ከሆነ በኋላ መቆላጨት ዋጋ የለውም፡፡ በልጅነቴ የሰማሁት በኢትዮጵያ ላይ በኋለኛው ዘመን ይደርሳል የተባለ ሟርት ይሁን ትንቢት እንዳይፈጸም ሁላችን በያለንበትና እንደየሃይማኖታችን ይትበሃል እንጸልይ ወንድሞቼና እህቶቼ፡፡ የፈሩት መድረሱ፣ የጠሉት መውረሱ የነበረ ነው፡፡ ደግሞም እኮ እንዲህ ይባላል፡- “ እንዲህ ጨሶ ጨሶ የነደደ እንደሆን፣ ያመዱ ማፍሰሻ ሥፍራው ወዴት ይሆን?” ገና ሌላም አለ – “የማን ቤት ፈርሶ የማን ሊበጅ፣ ያውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ”፡፡ አዎ፣ የአበቅቴው መዘግየት የመቅሰፍቱን እስከወዲያኛው ተሠውሮ መቅረት አያመለክትም፡፡

 

ያለንበት አገዛዝ የትግሬ ቅኝ ገዢ አገዛዝ ነው፡፡ ይህን ማስተባበል አንድም የሞትን ዕድሜ ወድዶ ማራዘም ነው፡፡ አንድም መዋሸት ነው፡፡ አንድም ጭልጥ ያለ አድርባይነት ነው፡፡ ሀገሪቱ ከግርጌ እስከ ራስጌ በትግሬ ወያኔ ተቀፍድዳ ኤሎሄ እያለች ሳለ “ትግሬ እየገዛን አይደለም፤ ትግሬዎች አልተጠቀሙም” ብሎ መወሽከት ታሪክ ይቅር የማይለው የለየለት እብለት ነው፡፡ እንዲህ የሚሉ ወገኖች ግና በርግጥ ዐይንና ጆሮ ይኖራቸው ይሆን? ለምን አዲስ አበባ አይመጡምና የመንግሥት ተብዬውን የወያኔ መናኸሪያ ጓዳ – ከተፈቀደላቸው – አይጎበኙም? ታማኝ የሠራው የዳሰሳ ቅኝት ራሱም እንደጠቆመው አባይን በጭልፋ ዓይነት ነው፤ የትኛው የመንግሥት ቤት ነው ከወያኔ ቀጥተኛ ቁጥጥር ነፃ የሆነና በሌሎች ኢትዮጵያውያን የሚተዳደር?ኢ-ትግራውያን ሠራተኞች የወያኔ ባርያና ሽቁጥቁጥ ሎሌዎች አይደሉም እንዴ? በሁሉም መሥሪያ ቤት እንደልቡ የሚዘባነነው ማን ነው? ማነው አዛዥ ናዛዥ? ይህን የፈጠጠ እውነት ማየት የማያስችል ምን ዓይነት ደምባራነት ነው?  (በአንድ የመንግሥት – (“የመንግሥት” ስል እንዴት እንደሚቀፈኝ ብታዩ) – የጦር ሆስፒታል አንድ ወቅት ስታከም እንደታዘብኩት ፈረቃቸው ደርሶ የተቀያየሩት ዘጠኙም የክፍሉ ሐኪሞችና ነርሶች ከጽዳቶቹ ጭምር ትግሬዎች ናቸው(ግን ገራገርና ጥሩዎች ናቸው) – ይህ ምን ዓይነት አጋጣሚ ይሆን? ይህን የማፊያ ሥርዓት ላይገባው የራስን ክብር አዋርዶ በውሸት ለማባበል መሞከር መናኛነት ይመስለኛል – ወይንም በአንዳች አእምሯዊ ግርዶሽ መሸፈን ነው፡፡ የንግዱንና ኢንዱስትሪውን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ወያኔ ትግሬ ይዞት ለትግሬዎች እያዳላ ለሌላው ግን ግብርና ቀረጥ እንዲሁም የቤት ኪራይ እየቆለለ ከሥራም ከሀገራዊ የዜግነት መብትም ውጪ ሲያደርግ እያየን ምኑ ላይ ነው ትግሬ አልተጠቀመም የምንለው? ምን ዓይነት አሽቃባጭነትስ ነው ገጥሞን ያለ ጎበዝ!)

ይልቁንስ በኔ በጠባቢቱ ዓለም ትግሬዎችን በሁለት ከፍዬ እንደማያቸው ባጭሩ ልናገርና ላስረዳ፡፡ ትግሬ በአንድ ትልቅ ቅርጫትና በሌላ ትንሽዬ ዘምቢል በድምሩ በሁለት ሊከፈል ይችላል፡፡ በትልቁ ቅርጫት ያለው ሕወሓትና ደጋፊዎቹ ናቸው፡፡ እነዚህ ብዙ ናቸው፡፡ ብዛታቸውም ከመቁጠር አቅም በላይ ነው፡፡ በጥንጥዬ ዘምቢል ውስጥ የከተትኳቸው ትግሬዎች መጠናቸው በጣም ጥቂት ነው፡፡ ግፋ ቢል ከአንደኛ ክፍል የሒሣብ መጽሐፍ የአራቱ መደቦች ክፍለ ትምህርት ውስጥ ሊካተት የሚችል መጠን ቢኖራቸው ነው – ማንም ሕጻን ሊደምር/ሊቀንስ የሚችለው አነስተኛ አኃዝ ነው፡፡ እነዚህ ቢበዙልን የመከራ ደብዳቤያችን በቶሎ ይቀደድልን ነበር፡፡ የነዚህ ሚዛን ግን ገና በጣም እንዳጋደለ ነው፡፡

ቀልድ አንቀልድም ብያለሁ፡፡ ብዙኃኑ የምላቸው ተጋሩ ወደዱም ጠሉም ሕወሓትና የህወሓት ናቸው፡፡ ይህን ስል የስንቶች ቅስም በሀዘን እንደሚሰበርብኝና እንደሚያዝኑብኝም አውቃለሁ፡፡ ግን ምንም ማድረግ አልችልም፤ እግዚአብሔር ይመስገን አሁን በራሴም ላይ ከመፍረድ ወደኋላ የማልልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ – ተስፋ መቁረጥ ግን እንዳይመስላችሁ፡፡ (በነገራችን ላይ  ከወያኔ የወጡና በአገዛዙ ብዙም የማይደሰቱ በተራ ገቢና ከቀድሞ ድርጅታቸው ውጪ በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ትግሬ ጓደኞቼ በመለስ ሞት ጊዜ እንዴት እንደሆኑ ታዝቤያለሁ – ቤታቸው በርሱ ፎቶ ተሞልቶና ማቅ በማቅ ሆነው ከርመዋል – ይህን እያወቅሁ ስለትግሬ ማንም ሊነግረኝ አይችልም፡፡ በቃ፡፡)  እናም አብዛኛው ትግሬ ተጠቀመም አልተጠቀመም በፕሮፓጋንዳው ተሸንፎ ወያኔ ሆኗል ወይም መስሏል፡፡ ይህ አባባል ትግሬን ከሌላው ለመለየት ምናምን እንደሚባለው ለመሆን አይደለም – እውነት ስለሆነ ነው፤ ደግሞም እኮ ዐማራና ትግሬ ሲለዩ ታየኝ፡፡ ወያኔዎችን ልፉ ቢላቸው እንጂ የትኛቸው ነው ከየትኛቸው የሚለየው?… ለማንኛውም አምባሻ ሻጯ፣ ቁራሌው፣ መጥረጊያ አዟሪው፣ ወዘተ. እየተራበና እየተጠማም ቢሆን ህወሓትን ከልቡ ይወዳል፡፡ (ለስለላ ሣይሆን ለእንጀራ ብለው በጠራራ ፀሐይ በየመንደሩ በእግራቸው የሚኳትኑትን ማለቴ ነው) ዘር መጥፎ ነው፡፡ “ዘር ከልጓም ይስባል” ወይም “ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ ትወጋ” የሚባለውም ለዚህ መሆን አለበት፡፡ በአንጻራዊ አነጋገር ዐማራው ይሻል እንደሆነ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁን ሥልጣን የሚይዘው ግለሰብ የመጣበት ነገድ “የኔ ሰው ተሾመልኝ” በሚል መደሰቱ የሚቀር አይመስለኝም –  ይህን ሁኔታ በአእምሮ ዕድገት ምክንያት ንቀው ካልተውት በስተቀር ተፈጥሯዊም ይመስለኛል፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ ብዙኃኑን ተጋሩ የዶልኩበት ቅርጫት ብዙ ሕዝብ ያለበትና በትግሬ ሥልጣን ላይ መቀመጥ የማይከፋ ብቻ ሣይሆን የሚደሰት ነው፡፡ በኢኮኖሚ ያልተጠቀመም ቢያንስ በሥነ ልቦና “እየተጠቀመ” ባዶ ሆዱን ተኮፍሶ ይውላል – “ደቅታትና አድ ገዛኢ ኾይኖም” እንዳበለ ዝኮርህ ቁጽሪ ትግራዋይ ቀሊል ከምዘይኮነ ንብኣለይ ብደምቢ እየ ዝፍልጥ፡፡ ብካልዕ ወገን ድማ ብመገዲ አገዛዝኣ ወያነ ህርቅ ዝብሉን አዚዮም ዝሃዝኑን ብዙኃት ተጋሩ ከመዘለው ፍሉጥ ኢዩ፡፡ ግና ካብዚኣቶም  ገፊህ ቁጽሪ ዘለዎም ሰባት ካብ አራት ኪሎ ዝተፈላለየ ውድብ ወያነ ምርዐይ ከምዘይደሉ ድማ ይፍለጥ፤ እዎ፣ ዘሎና ጥሜትን ሽግርን እዚዮም ተጋሩ ከምዝፍልጡ ንፍልጥ፡፡ ወያነ ክውገድ ግና አይደልዩን – ዝግበር ዘሎ ቃልሲ ፀረ ወያነ ንምትህብባርውን መብዛህቶም ድፍረትን ለባምነትን ዘለዎ አይመስልን ጥራህ እንተዘይኮነስ ብሃፈሻ የብሎምን ምባልውን ይከኣል፡፡ ስለምንታይ ኢልና እንተሀተትና ወያነ ካብዝገበሮ ብረታዊ ቃልሲ ብዘገደደ ብዋነኝነት እዚ ብአእምሮ ውሽጢ ሕዝቢ ትግራይ ዘቀመጦ ህማቅ ፕሮፓጋንዳ ምኋኑ ንርድዕ – እዙይ ፕሮፓጋንዳ ድማ “ንህና ካብ ሥልጣን እንተወሪድና እቲዮም አምሃሮ ክመፁ ኢዮም፤ ንሳቶም እንተመፅዑ ድማ መኩሪዕ ሕዝቢ ትግራይ ዝሆነት ውድብ ሕወሓትናን ምስ ሃፋሽ ህዝቢ ከጥፍዑ ኢዮም፡፡ ስለዚህ በዝኮነ መገዲ እዚ ማዕከላዊ ሥልጣን  ካብ ዕድ ተጋሩ ከምዘይወፅ ምርግጋፅ የድልየና፡፡” ብዝብል መርዘኛ ፕሮፓጋንዳ ጠርኒፎም ስለዝሃዞም እዩ …፡፡ Dear Ethiopian readers, look how we are interwoven and happen to be the two facets of the same coin; look how our languages are similar. Which is different from whom? Which one is the trunk? Which one is the branch? Don’t you believe that these two tribes had evolved from the same linguistic, religious, and cultural background? Who created this seemimgly bitter animosity, then, between these fraternal entities? When and by whom was this ugly cleavage wrought? Time will tell us the whole mystification anyhow, but, believe me TPLF will definitely clear the bill for its involvement in the exacerbation of the alleged hostility between these lovely tribes in the 21st century. I feel the scales are under making.

የሥነ ልቦና ነገር እጅግ አስቸጋሪ ነው አኅዋተይ፡፡ ሠለጠኑ የተባሉ የዓለም ዜጎች ሣይቀሩ በደመነፍስ የሚዘፈቁበት መጥፎ አረንቋ ነው፡፡ አስታውሳለሁ – በ83 ዓ.ም ወያኔ አዲስ አበባ እንደገባ በወያኔ ሬዲዮ የትግርኛ ፕሮግራም ስለትግራይ ሕዝብ በወያኔ ሥልጣን መያዝ ተጠቃሚነት የተጠየቀ አንድ ትግሬ ባለሥልጣን “የመጀመሪያው ጠቀሜታ ሥነ ልቦናዊ ነው፡፡ ‹የኔ ሰው ሥልጣን ያዘልኝ› ብሎ ማሰቡ በራሱ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ሁለተኛ ….” እያለ በኩራት ይደሰኩር ነበር፡፡ እየተናገረኩት ያለሁት ጉዳይ  እነሱ በተግባር ሲፈጽሙት የሚኮሩበትን፣ እኛ ግን ስንናገረው እንኳን በሀፍረት የምንሸማቀቅበትን የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ ሌላው የዚህ ተፃራሪ እውነት ደግሞ አንበርብር ሥልጣን ይዞ ጓንጉልና አበጋዝ በርሀብ የሚገረፉ የመሆናቸውን ያህል ጎይቶም ሥልጣን ይዞ አብረኸትና ሀፍቶም በርሀብ ሳቢያ ከቀያቸው የመፈናቀላቸው አጋጣሚ ሲጤን ሥልጣንና ነገድ ያላቸውን ልል ዝምድና አጉልቶ ማሳየቱ ነው፡፡ ሕይወት እንዲህ ናት – ዕንቆቅልሽ፡፡

የትግራይ ኤሊቶችም እንደማንኛውም የትግራይ ሕዝብ ጤናማ ኅሊናን መሠረት ባደረገ ምርጫቸው ወይንም በይሉኝታና ለግል ጥቅም ሲሉ ከነዚህ ከሁለቱ ጎራዎች አንዱን ወይ ሌላውን የሚቀላቀሉ ናቸው፡፡ ወደ ዘምቢሉ የሚገቡት ግን በጣት የሚቆጠሩ ናቸው ብዬ አምለሁ፤ ብዙዎቹ ይቺን “የዐማራ ጨቋኝ ብሔር” አይወዷትም – ከንቀታቸው ብዛት የተነሣ ደግሞ በአነስታይ ፆታ ነው የሚጠሯት – ግን ምን ዋጋ አለው በነሱው ብሶ “በትግሬይቱ ጨቆንቲ ብሔር” ተክተዋት ዐረፉና እያሳቀቁ አሣቁን፡፡ ትምህርታቸው ከወረቀት ያላለፈ የምሁር ማይሞች፣ በሰው ልጅ እኩልነት የማያምኑ የአእምሮ ጉንዲሾች፣ ዕይታቸው ከአላውኃ ወንዝ ጎጥ-ሰቀል አድማስ ያልዘለለ የአእምሮ ስንኩላን የሆኑ የትግራይ ኤሊቶች ይህን በዘረኝነት ደዌ የተመታና ሀገርን የሚያወድም ወያኔ መደገፋቸውን ስናይ ከዕውቀትና ከጥበብ ለሚመነጭ አስተዋይነት መገዛታቸውን ሣይሆን እንደውሻ ደምና አጥንት እያነፈነፉ ወደሚከረፋው የሆድ ውስጥ ዕቃ ወደጨጓራና ጅብ አይበላሽ መውረዳቸውን እንገነዘባለን፡፡ ከዚህ አኳያ ብዙ ኅሊናቸው የታወረ ተጋሩ “ምሁራን” አሉ፡፡በዚህ የሰው ልጆች ታላቅ የሥልጣኔ ዘመን እንዲህ ዓይነት “ሐጎስ ከአምባቸው ይበልጥብኛልና ከርሱ በፊት ያድርገኝ! በነስንሻው መቃብር ላይ የሀፄ ዮሐንስ ሥርወ መንግሥት ያብባል!” የሚል መፈክር ያነገበ ደንቆሮ ምሁር ሲታይ በርግጥም የሰው ልጅ በተለይም ኢትዮጵያውያን ምን እንደገጠማቸው ለማወቅ አዲስ ጥናት መደረግ ይኖርበታል ባይ ነኝ፡፡

ለማንኛውም ተቀበልነውም አልተቀበልነውም ተጋሩ በሁለት መከፈላቸውንና ድንበሩም አንዳንዴ እጅግ ጠባብ መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ አንድ የኤርትራ ተወላጅና በደርግ ዘመን መጨረሻ አካባቢ በኤርትራ የወጣቶች ማኅበር ሊቀ መንበር የነበረ የዚያኔው ጠምበለል ሸበላ ወጣት አንድ ቦታ ተገናኝተን ስናወራ “የሕወሓት ቫይረስ አደገኛ ነው፡፡ በማንኛውም ትግሬ ውስጥ የመገኘቱ ዕድል ደግሞ ከፍተኛ ስለሆነ ተጠንቀቁ” ያለኝን መቼም ልረሣው አልፈልግም፡፡ ይህን አባባል የጣሱ ንጹሕ ኢትዮጵያውያን ትግሬዎችን – እኔ የማውቃቸውን ብቻ – ቁጠር ብባል የአንድ እጄን ጣቶች እንኳን በቅጡ የምጨርስ አይመስለኝም፡፡ የሚያስጨንቀኝ እንግዲህ ይህ ነው፤ ደግሞም ስንቶች ምሁራን ተብዬዎች ወያኔን እየደገፉ ባሉበት ሁኔታ ተራው ማይም ዜጋ ከዚህ መርዘኛ አስተሳሰብ ነፃ እንዲሆን መጠበቅ የተምኔታዊነት ምርኮኛ መሆን ይመስለኛል፡፡ እንቅልፍ የሚነሳኝ ታላቅ የዘመን ዕንቆቅልሽ ነው – ስታምነው የሚከዳህን ጠላት ፈጣሪ ካልያዘልህና ካላሶበረልህ በተለይ በእንደኛ ዓይነቱ በመልክም በሰውነት ቅርጽም በቋንቋም በባህልም በሃይማኖትም … በተመሳሰለ ማኅበረሰብ ውስጥ በሬን ካራጁ ለመለየት እጅግ በጣም ከባድ ነው፤ ይህም ችግራችን ይመስለኛል ጣራችንን ያበዛውና የነፃነታችንን ዕለት ያዘገየው፡፡ ለዚህም ነው ለነፃነት የሚደረግን እንቅስቃሴ በመሸሽ በ“ጎመን በጤና” የራስህን አድን መፈክር ተጀቡኖ መኖር ባህል ሊሆን የቻለው፡፡ ይህ ዓይነቱ አካሄድ ግን ማብቂያ አለው፡፡ የከረረ ይበጠሳል፤ የላላም ይከራል፡፡ ከዚህ አኳያ ሦርያንና ኢራቅን፣ ሶማሊያንና የመንን፣ ሊቢያንና የቀድሞ ዩጎዝላቪያን፣ ሩዋንዳንና ብሩንዲን… በምናቤ እያየሁ እንቅልፍ አጣለሁ፡፡ እንዲህም የምሆነው ለራሴና ስለራሴ ነው – የወለደ አልጠደቀ፡፡ የልጆቼ መፃኢ ዕድል ከሁሉም በላይ ያስጨንቀኛል፡፡ ቤተሰቤን እንደነመስፍን ሥዩም እንደነ አንደሆም ቴንደሮስ ቻይናና ታይላንድ መላክና ከዕልቂት ማዳን አልችል አቅም የለኝም፡፡ እነሱ በደህናው ቀን ሁሉን ነገር አሰናድተዋል፡፡ ይብላኝ ለኔ ቢጤው ከርታታ ዜጋ፡፡ እነሱ በኛ ስቃይ ይደሰታሉ፤ እኛ የነሱን ስቃይ እኛው ላይ ደርበን ዕጥፍ ድርብ  እንሰቃያለን፡፡ እነሱ ወደያዘጋጁት ጎሬ እየተወተፉ ለማምለጥ መሞከራቸው አይቀርም፡፡ ሞት ግን የትም ሀገሩ ነውና ተደብቀው አያመልጡትም፡፡

ስሜት ብዙውን ጊዜ መጥፎ ነው፡፡ በስሜት ያለቀን ነገር ኅሊናና ምክንያት በቀላሉ አሸንፈው አይመልሱትም፡፡ በስሜት ንግሥና ወቅት ቋንቋና አመክንዮ ዋጋ የላቸውም፡፡ ወያኔዎችና ጭፍሮቻቸው ከምክንያትና ከሎጂክ ጋር ተቆራርጠው በስሜት ፈረስ መነዳት ከጀመሩ 40 ዓመታትን ደፍነዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ጀሌያቸው የነሱን ስብከትና የጥላቻ ፖለቲካ እየኮመኮመ እንደነሱው 40 ዓመታትን በመጓዙ ሠላሣ ምክንያት እየደረደርክ “አብረን ነበርን፤ ወንድማማቾችን ነን…” ብትለው አይሰማህም፡፡ መስሚያው በወያኔ ጥጥ ተደፍኗል፤ “ተደጋግሞ የተነገ ውሸት ከእውነት ይቆጠራል” እንዲሉ በወያኔ የዘር ጥላቻ ቅስቀሳ አብዛኛው ትግሬ ሰክሯል ቢባል ማጋነን አይደለም፡፡ ጥቂት የማይባል ትግሬ ደግሞ በመሀል እየዋለለ ነው – እንኳን ትግሬውና ሆዳሙ ዐማራና የተጋቦት ትግሬው ሁሉ ከወያኔ ጋር አብሮ እያደሸደሸ በሚገኝበት የነሆድ አምላኩ ዘመን የዐድዋውና የተምቤኑ “ንጡሕ” ትግሬ ለምን ወያኔ ይሆናል ብሎ መውቀሱም ፋይዳ የለውም – ፍርድ ከራስ ነውና ገነት ዘውዴ ያልተጸየፈችውን ወያኔነት የሽሬው አይተ ገብሩ ተስፋጋብር አቅፎ ቢስመው አይፈረድበትም፤ “ልሃጫም ዐማራ” እያለ ጌቶቹ በጋቱት ስድብ እመራዋለሁ የሚለውን ሕዝብ በስድብ የሚሞልጨው አለምነው መኮንን እያለ ኪሮስ አረጋዊን በወያኔነት መጠርጠር ሞኝነት ነው፡፡ በሕወሓት ፕሮፓጋንዳ የተጠለፈው አብዛኛው ትግሬ በትምህርቱ የገፋ ባለመሆኑ ሆዱ ከሞላና የሀብት ጥማቱ ከረካ ለሌላው ነገር ግድ ሊኖረው አይችልም፤ ስለመብት የሚታሰበው ደግሞ መብት ምን መሆኑን ሲያውቁ እንጂ ከእረኝነትና ከተኩስ ወረዳ በቀጥታ ቤተ መንግሥት ለገባ ሰው የዜግነትም በለው ሰብኣዊ መብት ከቀልድ ፍጆታነት አያልፍም – ለዚህም ነው እኮ ህገ መንግሥቱን ጠቅሰው መብታቸውን ሊያስከብሩ ለሚሞክሩ “የህግ” እሥረኞች “ለምትሉትን ህገ መንግሥት ለእንትናችሁን ፅረጉበት፤ ከፎሎጋችሁም ቆቅላችሁ ብሉት…” እያሉ ያለሀፍረትና ያለአንዳች ይሉኝታ በማን አለብኝነት የሚናገሩት – ከጥንቱ ጨዋ የትግራይ ሕዝብ እንዲህ ያሉ ማጋጣዎች መፍለቃቸው በውነቱ ሁል ጊዜ ይገርመኛል – ኣ! “ላም እሳት ወለደች…” አሉ፡፡

በመሠረቱ ለሕዝብ ነፃነት የሚያስብ ሰው ከሆድና ከቁሣዊ አስተሳሰብ ራሱን አስቀድሞ ነፃ ያወጣ መሆን አለበት፡፡ ትግራይን ጨምሮ ብዙው ኢትዮጵያዊ ግን ቁርስ እንደነገሩ ቀምሶ ለምሣና ለራቱ የሚጨነቅ በመሆኑ ስለነፃነት ያለው ዕውቀትና ግንዛቤ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ የትኞቹም መንግሥቶቻችን ለመብት ማስጠበቅ ትግል አላበቁንም፡፡ እንዲያውም ይበልጥ እያደነቆሩ ይገዙናል እንጂ፡፡ ወያኔዎች ይህንን እውነት አሳምረው ያውቃሉ፤ እንደሚጠቅማቸውም ስለሚረዱ ለሕዝብ መራብና በማይምነት የጨለማ አዙሪት መዳከር ሌት ተቀን ተግተው ይሠራሉ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ነፃነት ከሆድ ትበልጣለች፤ ከትምህርትም በላይ ነች፡፡ ስለሆነም እንኳንስ ባልተማረ ኅብረተሰብ፣ እንኳስ በተራበ ማኅበረሰብ ሻል ባለ ደረጃ በሚገኝ ሕዝብ ውስጥ እንኳን ይህን የነፃነት ጽንሰ ሃሳብ ለመረዳትና ተረድቶም ተግባራዊ ለማድረግ እጅግ ውስብስብና አስቸጋሪም ነው፤ ብዙ ዋጋም ስለምታስከፍል ደፍሮ የሚገባባት ወገን ጥቂት ነው፡፡

በወያኔው ለነገ የሚተርፍ ጦስ ምክንያት የሚያሩና የሚተክኑ ለጊዜውም ቢሆን  በሁለት እሳት እየነደዱ የሚገኙ ጥቂት ትግሬዎች ከሁሉም የሚያሳዝኑ የእግዜር ፍጡራን ናቸው፡፡ ትናንትናን ጠንቅቀው እንደሚያውቁ ነገንም በሚገባ ይረዳሉና እነዚህኞቹ ትግሬዎች የገጠማቸው ፈተና እጅግ ከባድ ነው፡፡ እንደ ወያኔ ሥራ ከሆነ እውነት ነው ይህ ዘመን በአፍራሽ ሁኔታ ከተለወጠ በትግራይ ወገኖቻችን ላይ ሊደርስ የሚችለው መከራና ስቃይ ሲያስቡት ከአሁኑ ያስቃዣል፡፡ ይህን የማይቀር የታሪክ ፍርድ ነበር በታማኝ ዝግጅት እየተመለከትኩ የነበረው፡፡ ፈረንጆቹ የሩዋንዳን ዕልቂት ካለፈ በኋላ ”ቀድመን እናውቅ ነበር” ብለው በሰዎች ስቃይ መዘባበታቸውን እናስታውሳለን፡፡ ያን የመሰለ ኃላፊነት የጎደለው ትዕቢታዊ ቃል የተናሩት “ካወቃችሁ ለምን አስቀድማችሁ አንድ ነገር አታደርጉም ነበር?” ብሎ በኃላፊነት የሚጠይቃቸው ምድራዊ ኃይል አለመኖሩን በእግረ መንገድ ለማሳየት ነው፡፡ እንዲያ በማድረጋቸውም ትዕቢታቸውን የሚያለዝቡበት አንድም የሞራል ዕሤት እንደሌላቸው በጎንዮሽ ተረድተናል፡፡ ከወፈሩ ሰው አይፈሩ ነው ነገሩ፡፡ የኛን ጉዳይ በሚመለከት ግን እግዜር ይስጣቸውና እንደነማንትስ እስታንተን የመሰሉ ምዕራባውያን ከወዲሁ እያስጠነቀቁን ናቸው፡፡ የማስጠንቀቂያው ደወል ለሁላችንም ነው፡፡ በጣም አስጨናቂ ጊዜ እየመጣብን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር ናት መባሏ መጽናናትን ይሰጠን ይሆናል እንጂ አደጋው ከሚታሰበው በላይ አስደንጋጭ ነው፡፡ የአበራሽን ጠባሳ ያዬ ደግሞ በእሳት ሊጫወት አይገባውም፡፡ የወያኔ ዐይንና ጆሮ ማታት ግን መንስዔው ምን ይሆን? ምንድን ነው እንዲህ ያጀገናቸው ማለቴ ያደደባቸው?

አዎ፣  ወያኔ በቤቱ ዐማሮችን ጨርሻለሁ ብሏል፡፡ “ዓሣን ለማጥፋት ባሕሩን ማድረቅ” ከሚለው ብሂል በመነሣት የዐማራ ኤሊቶች የሚፈልቁባቸውን አካባቢዎች አምክኜ ጨርሻለሁና ከእንግዲህ የዐማራ ኤሊት ተፈጥሮ ለሥልጣኔ አያሰጋኝም ብሏል፡፡ ዐማራውና ሌላውን የሚያቆራኘውን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አውድሜ ድራሹን አጥፍቻለሁ ብሏል፡፡ ታዋቂና ተሰሚ የዐማራ ምሁራንንና የሀገር ሽማግሌዎችን ገድዬ ጨርሻለሁ ብሏል፡፡ የኢትዮጵያዊነት ምልክቶችን ሁሉ አንድባንድ ደምስሻለሁ ብሏል፡፡ በተቃውሞው ጎራ የሚገኙ ዐማሮችን ለቃቅሜ አይቀጡ ቅጣት በመስጠት – በስድብ፣ በግርፋት፣ በወፌላላ፣ በግብረ ሶዶም፣ በወሲብ ጥቃት፣ በጥፍር ንቅላትና በፈላ ዘይት ጥብሳት … ስብዕናቸውን በማዋረድ መቼም እንዳያንሠራሩ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡ የዐማሮችን ቅስም ሰባብሬ ዳግመኛ ወደ ሥልጣን ዝር እንዳይሉ በአካልም በመንፈስም ኮድኩጃቸዋለሁ ብሏል፡፡ በአዲሲቷ ሕወሓት ሠራሽ ኢትዮጵያ ዐማራ ምንም ዓይነት ቦታ እንዳይኖረው በማድረግ በምትኩ ግን ሆድ አምላኩ የሆኑ ታዛዥ “ዐማሮችን” ሹሜ ከማካሂደው የዐማራን ዘር የማጽዳት ታሪካዊ ኃላፊነት የተረፉና ቀናቸውን የሚጠብቁ የዋሃን ዐማሮችን በዘዴ እስከጨርሳቸው አታልላለሁ ብሏል፡፡  … ብዙ ብሏል – ያላለው ነው የሌለው ይልቁንስ፡፡ ወያኔዎች ያሉት ሁሉ እውነት ቢሆን ኖሮ በጣም ደስ ባለኝ ነበር – በሰው ስቃይ መደሰት ኃጢኣትና ነውር ቢሆንም፡፡ ወያኔ ከመነሻው እስካሁን የደከመበት ዐማራን የማጥፋትና የሚቃወሙትን ሁሉ የመደምሰስ የዘወትር ተግባሩ እውን ቢሆን ኖሮ እኮ በአሁኑ ሰዓት እኛ የወያኔ ኢትዮጵያውያን አልፎልን ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ እንኳን በቅጡ ራሳችንን መመገብ እንችል ነበር፤ ሌላው ይቅርና ቢያንስ የሚራብ ትግሬ አይኖርም ነበር፤ ቢያንስ በባዶ እግሩ የሚሄድ ትግሬ አይኖርም ነበር፤ ቢያንስ የሚሰደድ ትግሬ አይኖርም ነበር…ብዙ “ቢያንሶችን” መደርደር ይቻላል፡፡ ችግሩ ወያኔ ያደረሰውን ያህል ጥፋትና ውድመት በተለይ በዐማራው ላይ ቢያድርስም ይህን “ጨርቅ” ሕዝብ ከምድረ ገጽ ማጥፋት አለመቻሉ ነው – አንዱን ስትነቅለው ሌላ አራት አምስት ቦታ እንደሚበቅለው የፊት ላይ ኪንታሮት ሆነበት፡፡ ስለዚህም ወያኔም ሆነ ሀገሪቱ ሰላም አላገኙም፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ደግሞ አንድን ሕዝብ ማጥፋት በፍጹም አይቻልም፡፡

ከሞት የተረፉ ዐማሮች ጊዜያቸው ሲደርስ ከያሉበት እየተጠራሩ መሰባሰባቸው ደግሞ አይቀርም፡፡ ሞትና የዘር ዕልቂት የታወጀባቸው ዐማሮች ከእንቅልፋቸው ነቅተው በቃን የሚሉበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርም፡፡ አባታቸው፣ ልጃቸው፣ ወንድማቸው፣ እህታቸው፣ባላቸው፣ ሚስታቸው … የሞቱባቸው ጠንቀኛ ዐማሮች ከተኙበት ጠሊቅ እንቅልፍ ሲነቁና ካጠገባቸው የነበሩ ዘመዶቻቸውን ሲያጡ ለነፍሳቸው በመፍራት በሚችሉት መወራጨታቸው አይቀርም፡፡ “ደቂሰይ ነይረይ ተበራቢረይ” ከተዘፈነ በኋላ “ዕደይ ሰዲደይ ሰዓት ሀሲረይ” በሚለው ባህላዊ የትግርኛ ዘፈን ምትክ “ተኝቼ ነበር ነቃሁ፤ እጄን ሰድጄ ክላሼን ታጠቅሁ” የሚል የዐማርኛ ዘፈን መቀንቀኑ አይቀርም፡፡ “በሎ እዙይ ሀድጊ” የሚለው ሥልት ተለውጦ “ይህን ዘረኛና ጎጠኛ ወያኔ አሳደህ በለው” የሚል ቅኝት መለቀቁ አይቀርም፡፡ እዚህም ብዙ “አይቀሩሞችን” መኮልኮል ይቻላል፡፡ …

ያኔ ነው ሰው የሚያስፈልገን፡፡ ያን አስጠሊታ የታሪክ ገጽታ ለመለወጥና ኃይላችንን ለመጠፋፋት ሣይሆን ለመልሶ ግንባታው ማዋል እንድንችል የሚያደርግ ጥበበኛ ሰው ነው ያኔ የሚያስፈልገን፡፡ ለዚያ ዓይነቱ መጥፎ አጋጣሚ የሚሆኑንን ሰዎች ከአሁኑ ማፈላለግ አለብን፡፡ እርግጥ ነው – ብሂላችን “ደም ትነጽሕ በድም” ቢልም መስዋዕቱ ቀለል እንዲልና በቶሎ ወደተረጋጋ ማኅበራዊና ቤተሰባዊ ሕይወት እንድንገባ አስተዋይ ዜጎች ከየብሄረሰቡ በእጅጉ ያስፈልጉናል፡፡ የሃይማኖት አባቶችም በዚህ ረገድ ቅኝታቸውን አስተካክለው እነሱ ራሳቸውም ወደ ፈጣሪ ፊታቸውን በመመለስ “ታጥበውና ታጥነው” ሊጠብቁ ይገባቸዋል – አሁንም በሕይወት አለን ብለው የሚያስቡ ከሆነ ለማያቃቸው እንዲታጠኑ እመክራቸዋለሁ – አላወቁትም እንጂ የሉም፡፡ “ሠርገኛ መጣ…” እንዳይሆንብን ሁላችን በተጠንቀቅ እንቁም፡፡ እነዚህ ጉዶች የሠሩት ሥራ የሚያቀባብር ባለመሆኑ ከሀሙራቢ የዐይንን ለዐይን ኦሪታዊ ህግ ታቅበን በይቅር ባይነትና በመቻቻል አጥፊዎችን መቆጣጠር ይኖርብናል፡፡ ቀኑ መሽቷል፡፡ ብዙ ሳይጨልም ማንኛውም ወገን ራሱን እየመረመረ የጤንነቱን ደረጃ ይወቅና የእርምት እርምጃ ይውሰድ – ትግሬ፣ዐማራ፣ ኦሮሞ … ሳይባባል ነው ታዲያ፡፡

በትልቁ ቅርጫትና በትንሹ ዘምቢል ውስጥ የሚገኙ ትግራውያን ወገኖቼም ቆም ብለው የሚያስቡበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ የጉሽ ጠላ ስካር መጥፎ ነው፡፡ ክፉኛ ያነበርራል፡፡ አሁን በየቦታው በሥልጣን ኮርቻና በሀብት ማማ ላይ የምናያቸው ትግሬዎች ኅሊናቸውን ስተው ነፍልለዋል፤ ኢትዮጵያን ብቻ ሣይሆን ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ሣይቀር እነሱ የፈጠሯቸው ያህል እየተሰማቸው በጣም ነሁልለው ይታያሉ – ቆሽተ ቀላል ሆኑና ሊከሉት ይቻል ለነበረ ትዝብት ተጋለጡ፡፡ የጥጋብና የትዕቢት መሸፈኛ ሱቲያቸው የፍየል ጅራት ሆነባቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ገለባነታቸው ገሃድ ወጥቶ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ገመናቸው  በአደባባይ ታዬ ፡፡ ፍትህና ርትዕ የነሱ ዕጣ ክፍል እንዳልሆነች ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ በሚያሳዝን ሁኔታ ለመላው ዓለም አሳዩ፤ ሌላው ሕዝብም ከነሱ ስህተት ትልቅ ዋጋ በመክፈል ጭምር ዘላለማዊ ትምህርት ቀሰመ፡፡ …

በሁሉም ሥፍራ በሁሉም ጉዳይ እንደ እርጎ ዝምብ ጥልቅ እያሉ ነገር ሲፈተፍቱ፣ ሸፋፋ ፍርድ ሲሰጡ … ለሚያያቸው ሰው የነዚህ ምሥኪን ዜጎች ታሪካዊ የኃላፊነት ሸክም ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መረዳት አላዳገተውም፡፡ አለመማር መጥፎ ነው ወንድሞቼ – ብዙዎቹ ደናቁርት በመሆናቸው ምን ይሉኝን አያውቁም፤ በዕድርና በሰምበቴም ጭምር እኮ ነው ሕዝቡን የሚያምሱት፡፡ ከዕውቀት ዕውቀት የለ፤ ከልምድ ልምድ የለ፤ ከአስተዋይነት አስተዋይነት የለ፤ ሀፍረት የሚባል አልፈጠረባቸው፤ ይሉኝታ የላቸው …. ሱቅ ውስጥ እንደገባ ሕጻን ሁሉንም ለኔ በሚል ፋሽን የሀገሪቱን አንጡራ ሀብት እስከነዘር ማንዘራቸው በመዥገራዊ መንቆር ቦጠቦጡት – ዕድሉን ያገኙና የተጠቀሙበት ወያኔ ትግሬዎች፡፡ እንደነሱ የሚገርም ፍጡር በምድር ላይ ቢገኝ ለማነጻጸሪያት እንኳን በጠቀመን ነበር፡፡ መበዝበዛቸውና ሁሉንም ነገር መቆጣጠራቸው ብቻ ቢበቃቸው መልካም በሆነ፡፡ ግን የማይነጋ እየመሰላቸው ሕዝብን በዘርና በሃይማት እየከፋፈሉ ከማናቆራቸውና በጄኖሳይድ ከመጨፍጨፋቸው በተጓዳኝ በኢትዮጵያ ምሥጢራዊ ጓዳዎች ሁሉ ጥሬ እንትናቸውን እየከመሩ ሀገሪቱን ለከፋ ዓለም አቀፋዊ ግማትና ክርፋት እየዳረጓት ይገኛሉ፡፡ ብላችን “ከመጠምጠም ማወቅ ይቅደም” ይል ነበር፡፡ እነሱ ግን ምንም ሳያውቁና ለማወቅም ጥረት ሳያደርጉ በጀብደኝነትና በጉልበት በሚቆጣጠሯቸው የመንግሥት ሥራዎች ላይ በቀላሉ የማይፋቅ ታሪካዊ ጠባሳ እያሳረፉ ናቸው – የሚኒስትር መሥሪያ ቤቶችን ወደ መቶ ሊያደርሷቸው እንደሆነም ካልተረጋገጡ ምንጮች እየሰማን ነው፡፡ ኢትዮጵያ በሁሉም ረገድ የምትገርም ሀገር እየሆነች ነው፡፡

ዲፕሎማሲያችን ከድጥ ወደማጥ እየሄደ መሆኑንም እየተገነዘብን ነው፤ አሁንማ ብለው ብለው የአሜሪካንን ድምፅ ጋዜጠኞች ሰብስበው በEBC4 ሥር ሊያዋቅሯቸውና አንድን ዜና ወይ ሀተታ ከማስተላለፋቸው በፊት በኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር አማካይነት ሳንሱር እንዲያስደርጉ አስጠንቅቀዋቸዋል የሚል በምሥጢር አፈትልኮ የወጣ ወሬም ደርሶን እየሰማን ነው – ለነገሩ አንድን ጋዜጠኛ ከዋሽንግቶን ቀርቶ ከመንግሥተ ሰማይም ቢሆን አፍንጫውን ይዘው ማምጣት እንደማይሳናቸው የሚፎክሩ ጦርነትን ሠሪ ወያኔዎች ምን የሚያቅታቸው ነገር አለ? (መለስ በሞተ ጊዜ እንዴት እምቢ አሻፈረኝ ብለው በአግዓዚ ጦር የመላከ ሞትን ደረት በጦር አልነደሉትም? ኣ! ድንገት አምልጧቸው መሆን አለበት! አሃ! ለካንስ የአግዓዚ ሠራዊት ባልነበረበት ቤልጂየም ውስጥ በሰው ሀገር ነው የሞተው)፡፡

ወያኔ ትግሬዎች የሚፈልጉትን ሀብትና ሥልጣን ካገኙ በኋላ ታሪክንና ሕዝብን ማጥፋት ለምን እንዳስፈለጋቸው ራሳቸውን ቢጠይቁ መልካም ነው፡፡ በተረፈ ኢትዮጵያ ነፃ ትወጣለች፡፡ ለራሳቸው ይጨነቁ፡፡ ሌላው ይቅርና እሳት መጫጫርም እንደብርቅ የሚታይበት ዘመን እንደሚመጣ ይረዱ፡፡ የዱባ ጥጋብ ካለስንቅ እንደሚያዘምት የታወቀ ቢሆንም አንዳንዴ ማስተዋልን ገንዘባችን ብናደርግ ለዘላቂው ጥቅምና የአብሮነት ኑሮ ይበጃልና ማሰብ እንጀምር፡፡ የሚያብለጨልጭ ሁሉ ወርቅ አይደለም፡፡ ይቺ ዓለም ለቀ.ኃ.ሥና ለመንግሥቱም አልተመለሰችላቸውም፡፡ለሂትለርና ሙሶሊኒም አልሆነችም፤ ለቢስማርክና ለእስታሊንም አልበጀችም፤ ለዚያድባሬና ለኢዲያሚንም አልከፈለቻቸውም፤ ለሞቡቱ ሴሴኮና ለቻርለስ ቴይለርም አልራራችላቸውም፤ ለጋዳፊና ሣዳምም ፊቷን አልሰጠችም፡፡… እንኳንስ በመስተዋት ቤት ውስጥ ለሚኖሩ የእፉኝት ልጆች! ታያላችሁ በበላሁት ጮማ ምትክ ምነው አፈር በበላሁ፤ በጠጣሁት ውስኪ ምትክ ምነው የአህያ ሽንት በጠጣሁ የሚሉበት ዘመን ይመጣል፡፡ በህግ ጥላ ሥር የሚገኙ ዜጎችን በዘራቸውና ለመብታቸው በመታገላቸው ምክንያት ሊሰሙት በሚዘገንንና ከባህላዊ ዕሤቶቻችን በእጅጉ ባፈነገጠ ሁኔታ የሚያሰቃዩ ሰይጣናውያን የወያኔ ገራፊዎች ዋጋቸውን የሚከፈሉበት ወቅት ደርሷል፡፡ ወዮላቸው!

በዚህ አጋጣሚ ሀገራችን መሪ እንደሌላት ብጠቁም ደስ ይለኛል፡፡ መለስ ከሞተ ወዲህ ወንበሩ ባዶ ነው፡፡ ደግነቱ ጠያቂ የለም እንጂ አንድም ተጠያቂ የለም፤ ሀገሪቱ በዘፈቀደና በደመነፍስ እየተነዳች ትገኛለች፡፡ ለረጂም ዓመታት ካለመሪ በጭፍን የተጓዘች ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ናት፡፡ ይህን ማስመሰል እንኳን እንዳይችል ሶፍትዌሩ በምሥጢር ኮድ የተቆለፈበት ኃይለማርያም የተባለ ጅላንፎ እንደመሪ ቆጥሮ “የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር” የሚል ወገን ካለ ራሱ ከሰውዬው የበለጠ ጅላንፎ ነው፡፡ “የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ” እየተባለ ሲነገር እንደግሥላ በጣም ነው በንዴት የምንጨረጨረው፤ እኔ ስናደድ በዚያው ልክ የወያኔ ቱባ ባለሥልጣናት አንጀታቸው በደስታ ቅቤ ሲጠጣ ይታየኛል – አንደኛው ዓላማቸውም ይሄው ነው – በዜጎች ሞራል መረማመድ፤ ሌላኛው ዓላማቸው ደግሞ ሲም ካርዱን ዋና ዋናዎቹ ወያኔዎች ይዘው ሰውዬውን በቀፎነት መጠቀም ነው፡፡

እውነተኛው መሪ ደብረጽዮን ይሁን፣ አባይ ፀሐዬ ይሁን፣አቦይ ስብሃት ይሁን፣ ዐርከበ ይሁን፣ … በውል አይታወቅም፤ ነፍሱን ይማርና ጋሽ ሙሉጌታ ሉሌ እንዳለው አምባገነንነቱ በጉልህ ይታያል – አምባገነኑ ግለሰብ ግን አይታይም – ምናልባትም ከመጋረጃ በስተጀርባ ነው፤ ይህን ሁኔታ “የቡድን አምባገነንት” ይለዋል ሙሌ፡፡ በሞባይል ስልክና በአጭር የጽሑፍ መልእክት (SMS) የምትመራ ብቸኛዋ የዓለም ሀገር ደግሞ ኢትዮጵያ ናት፡፡ የራሽያው ሜድቬዴቭ እንኳን ፑቲን ከበስተኋላው ቢሆንም በተወሰነ ደረጃ የራሱም የአመራር ችሎታ በተግባር ይታይ እንደነበር ሲነገርለት ነበር፡፡ የዚህኛው የኛው ጉድ ግን ሌላው ቀርቶ ለጸሎትና ለመጸዳጃ ቤትም ከጌቶቹ ሳያስፈቅድ የሚቀር አይመስለኝም፡፡ እንደሚባለው የዚህ ሰውዬ ሚና ከአንድ ዘበኛና ቤት ጠባቂ የሚያልፍ አይደለም – ሮቦት ቢጤ ይመስለኛል፡፡ እግዜር አልህ አይበለኝ እንጂ ሰውዬው የቋንቋም የሃሳብም ድህነት የሚያሰቃየው በፈረንጅኛው የቃላት አጠቃቀም አለማወቁን የማያውቅ “ሞሮን” ቢጤም ይመስለኛል፤ በቤተ መንግሥት ጠባቂዎች ላይ ይቅርና በውሾቹና በድመቶቹ ላይም ሥልጣን ያለው አይመስለኝም፡፡ በነገራችን ላይ በርሱና መሰል ኮንዶሞች ላይ የሚያካሂዱት ቀልድ በኛም ላይ እንደተካሄደ ይቆጠራል፡፡ ካልጠፋ ሰው የመቶ ዓመት ዕድሜ የዊልቼይር ተጠቃሚ ጃጃታም ሽማግሌ በፕሬዝደንትነት ያኔ የሾሙልን እኮ ሲያሾፉብን ነው – ዓለም እንዴት ይስቅብን እንደነበር መቼም አይረሳም – ከ80 ሚሊዮን ሕዝብ አንድ ታማኝ ቤት ጠባቂ ጠፍቶ ያንን ሰው ሲያደርጉ ኢትዮጵያን ለማዋረድ መቋመጣቸውን እናውቅ ነበር፡፡ ወያኔዎች በሰውና በሀገር መቀለድ በጣም ይችላሉ፡፡ ለማንኛውም ኢትዮጵያን የገዙ ሰዎች በታሪክ ሲሰፍሩ ከመለስ በኋላ እስከሚቀጥለው ራሱን የቻለ የትግሬ ጠ/ሚኒስትር ድረስ(በዘመነ ሕወሓት ከሆነ) ወይም እስከቀጣዩ እውነተኛ የኢትዮጵያ መሪ ያለው ቦታ በመለስ የሙት መንፈስ ወይም እንዲሁ በክፍተት እንዲተው መጠቆም እወዳለሁ፡፡ እንጂ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ተብሎ ቢጻፍ በበኩሌ ስቄም አላባራ፤ ደግሞም ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቴን ተጠቅሜ እፋረዳለሁ፡፡ ለነገሩ ለራሱም እንደስድብ የሚቆጥረው ይመስለኛል – እስከዚያን ጊዜ ከቆዬና ትንሽ ልብ ከገዛ፡፡ … ሰላም ሁኑልኝ፡፡

 

በበጎ የሚፈልገኝ ካለ nzeleke35@gmail.com

 

“መከራ ሲመጣ አይነግርም ዐዋጅ፤

       ሲገሰግስ አድሮ ቀን ይጥላል እንጂ፡፡”

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on October 30, 2015
  • By:
  • Last Modified: October 30, 2015 @ 6:17 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar