www.maledatimes.com ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በአሜሪካን ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  AFRICA  >  Current Article

ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በአሜሪካን ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላት

By   /   November 7, 2015  /   Comments Off on ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በአሜሪካን ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላት

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 47 Second

ባለፉት አምስት አመታት በጨቋኙ መንግስት የጭቆና ቀንበር ላይ ወድቃ በእስር ላይ ስትሰቃይ የነበረችው ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በጁላይ 9 2015 አካባቢ ከእስር መለቀቋ ይታወቃል በአሁን ሰአት ላይ ደግሞ በዋሽንግተን ዲሲ washington dulles airport በተለያዩ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያን ወዳጆች ዘንድ ከፍተኛ አቀባበል እየተደረገላት ይገኛል ። ከማለዳው 8፡00 ሰአት ጀመሮ እስከ አረፈችበት ሰአት ድረስ በዲሲ የሚገኙት ኢትዮጵያኖች ስራቸውን በመተው ለርዮት አለሙ ያላቸውን ክብር ለመግለጸ ሲሉ የኢትዮጵያን መገለጫ የሆነውን አረንጓዴ ቢጫ እና ቅይ ባንዲራ እያውለበለቡ መቆየታቸውን መረጃው ይጠቁማል። ርዮት በአሁን ሰአት ከእህቷ ጋር አብራ መሆኗን እና በሰላም መድረሷን በደስታ ገልጻለች፣ኢትዮጵያም ላሉት ወገኖች ለነበራት ጊዜ እና ላሳለፈችው መከራ  አብረዋት በመቆየታቸው ከፍተኛውን ምስጋና አቅርባለች

በከፍተኛ ሁኔታ በጡት በሽታ ስትሰቃይ እና ያለ አግባብ በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥራ ምንም አይነት መረጃ ሳይገኝባት በፍትህ እጦት ምክንያት ስትሰቃይ መክረሟ የሚታወስ ነው ሆኖም ግን ከረጅም ጊዜ በሁዋላ በነጻ መለቀቋ ተሰምቶአል ።

በተለያዩ ስቪል ሶሳይቲ ፣እንዲሁም አለም አቀፍ መገናኛ ድርጅቶችም ሆነ አለም አቀፍ መንግስታቶች የሰበአዊ ጥሰት እንደተፈጸመላት የተነገረላት እና ከፍተኛ ትኩረትን ከመሳብ በላይ ብዙዎች የአለም አቀፍ አዋርድ እጮ ለማድርግ ያበቁዋት ድንቅ ሴት መሆኗ ይታወቃል ከእነዚህም ውስጥ የዩኒስኮ ፕረስ ፍሪደም አዋርዱ ከፈተኛ ተጠቃሽ እና ምስክርነትን ሊሰጥ ይችላል።

ርዮት አለሙ የጋዜጠኝነት ስነምግባር በተከተለ ደንብ ጋዜጠኝነትን ስታራምድ የቆየች ድንቅ ሴ ስትሆን በመምህርትነቷም ደግሞ ተደናቂነትን ካተረፉት እና የተቸገሩ ተማሪዎችን በመርዳት ትልቅ ስራ በመስራት የምታወቅ ምርጥ ወጣት እንደሆነች መረጃዎች ያመለክታሉ ፣ከዚይም ባሻገር የጺዮን በስተጀርባ በተሰኘው ፊልም ላይ በደራሲነት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ስለሺ ሃጎስ ጋር በእጮኝነት ተሳስራ ለረጂም ጊዜያት አብራው እንደኖረች እና በጉዋደኝነት ህይወታቸው ውስጥ መልካም እና ጥሩ ህይወት የሰመረበት ህይወት ውስጥ እንዳሉ ከጋዜጠና ስለሺ በተለያዩ ወቅቶች በስሟ በገለጸው የነጻነቷን መጠየቂያ ብሎግ ላይ ማስፈሩ ይታወሳል። ከጺዮን በስተጀርባ የተሰኘው ፊልም ያጠነጥን የነበረው በዝዋይ ህይቅ ማዶ ይገኙ በነበሩ ዛየን በተሰኙ ብሄረሰቦች ላይ የሚያተኩር እንደነበር የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ይገልጻል

በሌላም በኩል ከርዮት አለሙ ጋር አብሮ የታሰረው እና እስካሁን ድረስ ሰሚያታው ጋዜጠኛ ውብሸት ያለምንም የፍርድ ውስታኔ በፍትህ እጦት እስርቤት እየተሰቃየ ከመሆኑም በላይ ቤተሰቦቹንም ለማየት አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ይገልጻሉ ይህ ብቻም ሳይሆን በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም ላይ የዚሁ አይነት የሰበአዊ መብት እረገጣ መድረሱን በተከታታይ ሳምንት ሲዘገብ ቆይቶአል ። ጋዜጠና እስክንድር ነጋም በእስርቤት ከቆየ 4ኛ አመቱን ከማክበሩም በላይ በዛሬው እለት የተወለደባት የልደት ቀኑ እንደመሆኑ መጠን መልካም ልደት ፣ምንም ነጻንትህ ተነፍጎህ በእስር ጫንቃ ላይ ብትወድቅም ሁንልጊዘም ጀግናችን ነህ ፣የመልካም ስራህ እና ድንቅ ፈገግታህ ከሰዋዊው መልካም አክብሮትህ ጋር  እያስታወሱ ሁልጊዜም የማለዳ ታይምስ አዘጋጆች ያከብሩሃል። 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on November 7, 2015
  • By:
  • Last Modified: November 7, 2015 @ 10:13 am
  • Filed Under: AFRICA, Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar