www.maledatimes.com የሳውዲው ባለሃብት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ቅሬታ ማሰማት ጀመሩ ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሳውዲው ባለሃብት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ቅሬታ ማሰማት ጀመሩ   !

By   /   November 30, 2015  /   Comments Off on የሳውዲው ባለሃብት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ቅሬታ ማሰማት ጀመሩ   !

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 33 Second

የማለዳ ወግ …
=========================================
*  “በኢትዮጵያ  በደልና ዘረፋ ተፈጸመብን !”  ባለሃብቱ!
* ” ቅሬታ ውንጀላው መሰረት ቢስ ነው ” የኢትዮጵያ ዲፕሎማት

ህዳር 15 ቀን 2008 ዓም በወጣው ታዋቂው የሳውዲ ጋዜጣ አረብ ኒውስ የኢትዮጵያ መንግስት አንዳንድ ባለስላጣኖች መሬታቸውን እየተቀሙ በደልና ዘረፋ እየተፈጸመባቸው  መሆኑን ሞሀመድ አልሸህሪ የተባሉ ባለሃብት ለአረብ ኒውስ አስታውቀዋል።  እኒሁ ባለሃብቶችን መርተው ወደ አፍሪካና ወደ ኢትዮጵያ ከአመታት በፊት ወደ የዘለቁት ባለሃብት አንዳንድ የመንግስት ኃላፊዎች በኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ሀገሪቱ ያስገቡትን ንብረቶች ለመውረስ በእርሳቸውና በጓደኞቻቸው ላይ የወንጀል ክስ አንደተመሰረተባቸው  ማስታወቃቸውን አረብ ኒውስ ዘግቧል ። ቅሬታ አቅራቢው ሳውዲ ባለሃብት ሞሃመድ አልሸህሪ ለአረብ ኒውስ ጋዜጣ እንዳስታወቁት ሙስናው የከፋ እየሆነ መምጣቱን በመጠቆምሳውዲ ባለሃብቶች በማመሳሰል ( Forgery)  ወንጀል ሳይቀር ተወንጅለው ለስራ ያስገቧቸውን እቃዎች መመለስ እንዳልቻሉ አስረድተዋል ።

ከስድስት አመት በፊት ጀምሮ በእርሻ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሳውዲ ባለሃብቶች በመንግስት የተገባላቸው ቃል በተግባር ባለመፈጸሙ 50 % እጅ ያህሉ ባለሃብት ከኢትዮጵያ ለቀው መውጣታቸውን እኒሁ ቅሬታ አቅራቢ ሳውዲ ባለሃብት ተናግረዋል ። በደረሰባቸው በደል ተማረው ሀገሪቱን ለቀዋል ስላሏቸው ባለሃብቶች ሲያስረዱም ያቻሉት ሸጠው መውጣታቸውን አልደበቁም። መሸጥ ያልቻሉትና  ያልቻሉት እቃቸውን ትተው የወጡት ግን ተመልሰው እቃቸውን ቢጠይቁ ” በማናውቀው ወንጀል እንያዛለን !”  በሚል ስጋት ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ላይ ወረታቸውን በትነው መቅረታቸውን ሞሃመድ አልሸህሪ ለአረብ ኒውስ አስታውቀዋል ።

ከዚህ ቀደም ተሰምቶ የማይታወቀውን የሳውዲ ባለሃብቶች ቅሬታና ብሶት ለታዋቂው የሳውዲ ጋዜጣ ለአረብ ኒውስ በአደባባይ ያጋለጡት ባለሃብቱ ሞሃመድ አልሻህሪ ቅሬታቸውን ለሁለቱም ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቢያቀርቡም እስካሁን ምነም አይነት ምልሽ እንዳላገኙ ጠቁመዋል   !

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዜናውን ማስፈንጠሪያ በፊስ ቡል የፊት ገጼ ላይ እንደለጠፍኩ  ” እንዴት ይህን ያልተጨበጠ መረጃ ሊንክ Link ይዘህ ትለጥፋለህ? ” በማለት የጅዳ ቆንስል ዲፕሎማት ቆንስል ሸሪፍ በስልክ ቅሬታቸውን ግልጸውልኛል ።  ለሚሊዮኖች በአለም ዙሪያ የተሰራጨውን መረጃ ማስተላለፊን በአግራሞት የተመለከቱትና በጅዳ ቆንስል የኢኮኖሚ ኋላፊ አቶ ሸሪፍ ኼሪ በዜናው ዙሪያ ዘርዘር ባለ መልኩ አነጋግረውኛል ። እኔም ያቀረብኩት መረጃ ከአረብ ኒውስ ማግኘቴን ደግሜ በማስረዳት ማሰተባበያ ማቅረብ እንጅ የወጣውን መረጃ አታሰራጩ ፣ አለያም አትለጥፉ ማለት እንደ ሚከብድ አሳውቄቸዋለሁ  !

ቆንስል ሸሪፍ በመጨረሻም ” አረብ ኒውስ ጋዜጣ ዛሬ ያወጣው መረጃ የተዛባ በመሆኑ አስፈላጊው ሁሉ እርምጃ ይወሰዳል ” በማለት  “ፍጹም መሰረተ ቢስ ነው ! ” ላሉትን የተሰራጨ መረጃ ምላሽ ለመስጠት በሪያድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ በኩል አስፈላጊ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጸውልኛል  !

ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 15 ቀን 2008 ዓም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on November 30, 2015
  • By:
  • Last Modified: November 30, 2015 @ 10:12 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar